ጥቅምት 25 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በአንድ አባት እጅ የተቆፈረ የመቃብር ጉድጓድ፣ ዛሬ በውብ የሱፍ አበባዎች አብቦ የተስፋና የፍቅር ምልክት ሆኗል!
በፈረንጆች 2017 በቻይና ሲቹዋን ግዛት የሚኖረው ዣንግ ሊዮንግ የሁለት ዓመት ልጅ የሆነችው ትንዷ ዣንግ ሲንሌይ በፅኑ የደም ሕመም (Severe beta thalassemia) መጠቃቷን አወቀ።
ህመሟ ቀጣይነት ያለው የደም ልገሳ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ አባት ሊዮንግ ያለው ጥሪት በሙሉ እስከሚያልቅ ድረስ ቢታገልም የህክምና ወጪዋን መሸፈን ተሳነው።
ተስፋ የቆረጠው አባት አንድ ቀን ልጄን ባጣትስ ከሚል ስጋትና ፍርሃት የተነሳ በእርሻው አጠገብ ጉድጓድ ይቆፍራል። ከዚያም ትንሿን ሲንሌይ እዚያ ጉድጓድ ውስጥ ይዟት በመተኛት ሰማዩን እያዩ ይጫወቱ ነበር—ዓላማውም ልጁ አንድ ቀን የሞት ድቅድቅ ጨለማ ቢመጣ እንኳ እንዳትፈራና የደህንነት ስሜት እንዲሰማት ለማድረግ ነበር።
ሆኖም የዚህ አባት እና ልጅ ልብ የሚሰብክ ታሪክ በኢንተርኔትና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተሰራጭቶ የብዙዎችን ትኩረት ሳበ። በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ ርህሩህ ሰዎች የገንዘብ እርዳታ ያደረጉላቸው ሲሆን፣ የህክምና ወጪዋም ሙሉ በሙሉ ተሸፈነ።
በኋላም ታናሽ እህቷ ስትወለድ ከተገኘው የእምብርት ደም (Umbilical cord blood) በተደረገላት የሴል ሽግግር (Stem cell transplant) ህክምና ሲንሌይ ሙሉ በሙሉ ልትድና ቻለች! ዛሬ ላይ ያለምንም ተጨማሪ የደም ልገሳ ጤናዋ ተመልሶላት ትኖራለች።
በአሁኑ ወቅት ሲንሌይ ትምህርቷን እየተከታተለች፣ ስዕል በመሳልና በመጨፈር ደስተኛ ህይወቷን እየመራች ይገኛለች።
እናም ያ የተስፋ መቁረጥና የእናት-አባት ስቃይ ምስክር የነበረው የመቃብር ጉድጓድ ምን ሆነ? ቤተሰቦቿ በአፈር ሞልተውት ውብ የሱፍ አበባዎችን ዘሩበት፤ ስሙንም “የሲንሌይ ድንቅ አትክልት” (Xinlei’s Magical Garden) ብለው ሰየሙት።
አንድ ወቅት የአባት የከፋ ፍርሃትና ህመም የነበረ ቦታ፣ ዛሬ የህይወት ተስፋ፣ የተአምርና የጥልቅ ፍቅር ህያው ምስክር ሆኖ አብቧል
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ