መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ለዓመታት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የታይሰን ፊዩሪ እና አንቶኒ ጆሹዋ የከባድ ሚዛን የቦክስ ውድድር የሚካሄድበት ቦታ መታወቁና ስምምነት መፈረሙ ተገልጿል። የፊታችን ታህሳስ ወር በዌልስ ካርዲፍ ስታዲየም ለብዙ ዓመታት ሲጠበቅ እና ሲጠየቅ የነበረው የቦክስ ፍልሚያ ጥያቄ መልስ ያገኛል። “የብሪታንያ ፍልሚያ” ተብሎ የተሰየመው ይህ ታላቅ ግጥሚያ በታህሳስ ወር በዌልስ ካርዲፍ ከተማ በሚገኘው የፕሪንሲፓሊቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ መወሰኑን አዘጋጆቹ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። ሁለቱ የብሪታንያ ከባድ ሚዛን ቦክሰኞች በሳዑዲ አረቢያ ውሉን የተፈራረሙ ሲሆን፣ ግጥሚያው በብሪታንያ የቦክስ ታሪክ ትልቁ እንደሚሆን ይጠበቃል። የ38 ዓመቱ ታይሰን ፊዩሪ በ2024 መጨረሻ ላይ ከቦክስ ስፖርት ጡረታ መውጣቱን አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ በ2026 ጥር ወር ላይ ዳግም ወደ ስፖርቱ መመለሱን ይፋ አድርጓል። ፊዩሪ በሙያዊ የቦክስ ህይወቱ 39 ፍልሚያዎችን አድርጎ 36 ድሎችን ያስመዘገበ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ 25ቱን በዝረራ ያሸነፈ ነው። ብቸኛ 2 ሽንፈቶቹ የተመዘገቡትም በ2024 ከዩክሬናዊው ኦሌክሳንደር ኡሲክ ጋር ባደረገው ጨዋታ ነው። አንቶኒ ጆሹዋ ባደረጋቸው 34 ፕሮፌሽናል የቦክስ ፍልሚያዎች 30ውን ያሸነፈ ሲሆን፣ ከእነዚያ መካከል 27ቱን በዝረራ መርታት የቻለ ቡጢኛ ነው። በቦክስ ታሪኩ 4 ጊዜ ብቻ የተሸነፈ ሲሆን፣ ዩክሬናዊው ኡሲክ 2 ጊዜ አሸንፎታል። ሁለቱንም ተፋላሚዎች መርታት የቻለ ብቸኛው ሰው ዩክሬናዊው ኡሲክ ሲሆን፣ ከእሱ ውጪ አንዲ ሩዊዝ እና ዳንኤል ዱቧም የጆሹዋን የሽንፈት ጽዋ እንዲጎነጩ ያደረጉ ሌሎች ቡጢኞች ናቸው። ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም በ2021 ሁለቱ ቦክሰኞች እንዲፋለሙ ጥረት ተደርጎ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ ቢቀርም፣ የአሁኑ ስምምነት ግን ለዓመታት የቆየውን ጥበቃ የሚያበቃ ሆኗል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ለአትሌቲክስ ልኡክ ቡድን የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት መርሀግብር ተከናወነ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በናይጄሪያ አቡኩታ በተካሄደው የአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ... read more
ቡካዮ ሳካ የሻምፒዮንስ ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተሰይሟል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥቁሩ ፈርጥ ባሳለፍነው እሮብ በነበረው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ6ኛ ዙር ጨዋታ ሞኒኮ ላይ 2 ጎል... read more
ጀማል ሙሲያላ የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የወንዶች ምርጡ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለባየር ሙኒክ እየተጫወተ የሚገኘው ጀማል ሙሲያላ 56 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነው የአመቱ ምርጥ የጀርመን ብሄራዊ... read more
ኪሊያን ምባፔ 10 ቀን ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፈረንሳዊው ኮኮብ ኪሊያን ምባፔ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 6ኛ ጨዋታ ጣልያን ቤርጋሞ ላይ ሪያል ማድሪድ... read more
የእንግሊዝ ክለቦችን የሚያፋጥጠው የዩሮፓ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ ዳሰሳ
በክለቦች የውድድር መድረክ ላይ ሁለተኛ እርከን የሚሰጠው የዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በሁለት እጅግ አስከፊ የውድድር ዘመንን ባሳለፉ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች... read more
አሪያና ሳባሌንካ እና ያኩፕ ሜንሲክ የማዬሚ ኦፕንን አሸነፉ
ዘንድሮ ለ40ኛ ጊዜ በተከናወነው አመታዊው የማዬሚ ኦፕን ሜዳ ቴኒስ ውድድር በአሜሪካ ማዬሚ ግዛት ላይ ሲከናወን በሴቶች የአለም ቁጥር አንዷ አሪና... read more
ማንቸስተር ዩናይትድ በአማዞን ዶኩመንተሪ ሊሰራ የታሰበው ዘጋቢ ፊልም እንዲቋረጥ አድርገዋል ተብሏል
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዋናው ምክንያት ሩበን አሞሪም መልበሻ ክፍል ውስጥ ካሜራ እንዳይቀመጥ መፈለጉን ተከትሎ ነው ተብሏል።
Prime amazon የየክለቦች... read more
ቲዮ ኸርናንዴዝ ሚላኖች እሱን ባስተናገዱበት መንገድ ደስተኛ አለመሆኑን ለወኪሉ አሳውቋል ተብሏል
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ ፈረንሳዊ የቡድኑ አምበል የኮንትራት ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ይታወቃል። በ2026 ውሉ ይጠናቀቃል ስለዚህ ውሉን እንዲያድስ... read more
የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለብ አልሂላል የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ኦሊ ዋትኪንስን ከአስቶን ቪላ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተሰማ።
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዝውውር ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራው ታዋቂው ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደገለጸው፣ ሁለቱ ክለቦች በ58.4 ሚሊዮን... read more
ማንቸስተር ሲቲዎች ኢሊማን ንዲያዬን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ሲቲዎች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የኤቨርተኑን ኢሊማን ንዲያዬን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ጋዜጠኛ ቤን... read more
ምላሽ ይስጡ