መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በጃፓን የተጣሉ የመስታወት ጠርሙሶችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል ለመንገድ ግንባታ የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን ለማዘጋጀት የሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሥራዎች ከፍተኛ ትኩረት እያገኙ መሆናቸው ተገለጸ። ይህ የመልሶ መጠቀም ሂደት በቀላሉ የተጣሉ ጠርሙሶችን ወስዶ መንገድ ላይ መበተን ሳይሆን፣ ጥብቅ የቴክኒክ ደረጃዎችን ተከተሎ ወደ ግንባታ ቁሳቁስነት የሚቀየርበት አሰራር እንደሆነ ተመላክቷል። የሂደቱ የመጀመሪያ ደረጃ የተጣሉ የመስታወት ጠርሙሶችን የመሰብሰብ ሥራ ሲሆን፣ በመቀጠልም የተለያዩ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችና ተገቢ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ከመስታወቱ ይለያያሉ። መስታወቱ በበቂ ሁኔታ ከተጸዳ በኋላ ወደ ትናንሽ ቁርጥራጮች የሚፈጭ ሲሆን፣ ቁርጥራጮቹም በመጠናቸው ይመደባሉ። ይህም በመንገድ ግንባታው ሂደት ውስጥ የሚያስፈልገውን ዓይነትና መጠን በስርዓት ለመቆጣጠር ያስችላል። በሙያ አጠራር “glass cullet” በመባል የሚታወቀው ይህ የተፈጨ የመስታወት ቁሳቁስ፣ ከአስፋልትና ከሌሎች የመንገድ ግንባታ ጠጠሮች ጋር በተወሰነ መጠን ይደባለቃል። ይህም በተለምዶ ከተፈጥሮ ከመሬት የሚቆፈሩ የጥሬ ዕቃዎችን ፍላጎት በከፊል ለመተካት ያስቻለ ዘዴ ሆኗል። ነገር ግን ማንኛውንም ዓይነትና መጠን ያለው መስታወት በአስፋልት ውስጥ መቀላቀል እንደማይቻል ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የመስታወቱ መጠን፣ ቅርፅ፣ ንጽህና፣ እንዲሁም ከሌሎች ቁሳቁሶች ጋር የሚቀላቀልበት ትክክለኛ መጠን በመንገድ ኢንጂነሮች በጥንቃቄ የሚወሰን ነው። የዚህ አሰራር ዋና ዓላማ የመንገዱን ጥንካሬ፣ ደህንነት እና ዘላቂነት ሳይቀንሱ የተፈጥሮ ጥሬ ዕቃዎች አጠቃቀምን መቀነስ እንደሆነ ተገልጻል። መስታወትን በዚህ መልኩ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ከአካባቢ ጥበቃ አንፃርም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ወደ ቆሻሻ መጣያ ቦታዎች የሚጣሉ የመስታወት ጠርሙሶችን ወደ ኢንዱስትሪው ሂደት በመመለስ የቆሻሻ መጠንን ለመቀነስ የሚረዳ ሲሆን፣ በተጨማሪም አዳዲስ የግንባታ ጥሬ ዕቃዎችን ከተፈጥሮ የመቆፈር ፍላጎትን በከፊል ለመቀነስ እንደሚያስችል ተጠቁሟል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ፍይኖርዶች ሩበን ቫን ፐርሲን በአሰልጣኝነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል
የ41 አመቱ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ እና የአርሰናል የአጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ሮቨን ቫን ፐርሲ በኤርዲቪዝዬው እየተጫወተ የሚገኘው ኸረንቪን እያሰለጠነ እንደሚገኝ... read more
ሊቨርፑል ሚሎሽ ኬርኬዝን ሁለተኛ ፈራሚያቸው ለማድረግ ተቃርበዋል
ይሄ ሀንጋሪአዊ በ2023 ሰኔ ወር ላይ በርንማውዝን ከተቀላቀለ በኋላ በጣም አስደናቂ የግል አቅሙን እያስመለከተ ይገኛል። በዛ ላይ ገና 20 አመቱ... read more
ሞሀመድ ሳላህ ዘንድሮ ከሻምፒዮንስ ሊጉ ይበልጥ ፕሪሚየር ሊጉን ማሳካት እፈልጋለሁ ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል
ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ግብፃዊው ኮኮብ ፍርኦኑ ሞ ሳላህ ዘንድሮ አይቀመሴ አቋም ላይ ነው የሚገኘው። በወርሀ ታኅሳስ ብቻ በ7... read more
በክለቦች ትልቁ የውድድር መድረክ በሆነው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ቀሪ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በኢንተርሚላን እና ባርሴሎና መካከል ይከናወናል
👉ሁለቱ ቡድኖች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ካሳኩ 10 አመት እና ከዛ በላይ ያስቆጠሩ ቡድኖች ናቸው።
የ2010 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን በልዩው ሰው The... read more
245ኛው የመርሲሳይድ ደርቢ ዛሬ በጉዲሰን ፓርክ የሚከናወን ይሆናል
ኅዳር 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ምህረት አልባ መሆን አለብን ተጭነን ተጫውተን ውጤት ለማግኘት ነው የምንፈልገው ሲል አርን ሽሎት ዛሬ ከሚደረገው... read more
UFC የፍልሚያ ምሽት በለንደን ተከናውኗል
የአለማችን ትልቁ የፍልሚያ መድረክ የሆነው እና የሚክስድ ማርሻል አርት ክህሎት ያላቸው ተፋላሚዎች በየክብደት እርከናቸው ተከፋፍለው በሚያከናውኑት የፍልሚያ መድረክ ትላንት በእንግሊዝ... read more
ፊዮሬንቲና ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረቡ ተገለጸ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጣሊያኑ ክለብ ፊዮሬንቲና የ25 ዓመቱን የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም... read more
ከአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን የፊታችን ሃምሌ 22 እንደሚካሄድ ተገለፀ
ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ESCFE ይህ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌዴሬሽን በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአንድ... read more
ቡካዮ ሳካ የሻምፒዮንስ ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተሰይሟል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥቁሩ ፈርጥ ባሳለፍነው እሮብ በነበረው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ6ኛ ዙር ጨዋታ ሞኒኮ ላይ 2 ጎል... read more
ፍራንክ ጄምስ ላምፓርድ እና ማይክል ካሪክ የፕሪሚየር ሊጉ ከአሰልጣኝነት የመሰናበት እጣ ፋንታ የተደቀነባቸው 2 አሰልጣኞች መሆናቸው ተገልጿል
መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ዘመን ከተጀመረ አራት ሳምንት ወይም 40 ጨዋታዎች የተደረገ ቢሆንም፣ የእንግሊዝ የስፖርታዊ... read more
ምላሽ ይስጡ