መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነቡ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተጽዕኖ ቢኖራቸውም፣ በትብብር ከተመሩ ለቀጠናው ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገልጸዋል። ውሳኔው የኢትዮጵያን ሀገራዊ የኃይል አቅርቦት ለማስፋፋት፣ የኤሌክትሪክ ተዳራሽነትን ለማረጋገጥ እና ትርፍ ኃይልን ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ይናገራሉ። ደቡብ ሱዳን በላይኛው ናይል ተፋሰስ ላይ ግድብ ለመገንባት የምታደርገው እንቅስቃሴ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን (CFA) መሠረት ያደረገ መሆኑን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡ ውሳኔው እስካሁን በግብፅ በኩል የነበረውን የውኃ አጠቃቀም የበላይነትና ጫና በጋራ ለመጋራት እንዲሁም ፍትሐዊ አጠቃቀምን ለማስፈን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ በዲፕሎማሲና በልማት ዘርፍ ድጋፍ የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ፣ ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትም ወደ ተመሳሳይ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲገቡ መንገድ የሚከፍት በመሆኑ ለቀጠናው ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የወሰደችው ውሳኔ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስጠብቅና የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚያረጋግጥ መሆኑን የዲፕሎማሲ ባለሙያው አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ገልጸዋል። ውሳኔው ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የጋራ ስምምነት ጋር የሚጣጣም መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ ግድቡ መገንባቱ ሀገራት የተፈጥሮ ሀብታቸውን በሉዓላዊነት የመጠቀም መብታቸውን የሚያጠናክር እና የጋራ ተጠቃሚነት መርሕን የሚያጎለብት ነው ብለዋል። የግድቡ መገንባት የደቡብ ሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትንም በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ታይቶ የማይታወቅ የጠፈር ውዝግብ፦ በምሽት “ፀሐይን ለመግዛት” የሚደረገው የቢሊዮን ዶላር እቅድ እና ያስከተለው ስጋት!
ሰኔ 10 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፀሐይ ብርሃን ጠልቆ ጨለማ በሰፈነበት የምሽት ሰዓት፣ እንደ ልብ የፀሐይ ኃይል ማመንጨት የሚቻልበት ዓለም ቢፈጠር... read more
ፒዬሮ ሂንካፒዬ ለሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዝግጁ ነው
ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተከላካዩ ፒዬሮ ሂንካፒዬ ለዛሬው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን... read more
በጎረቤት ሀገራት ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ስደተኞች በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ተገለጸ
ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ለበርካታ ዓመታት የሚሰጡት የአጭር ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታና የሕይወት አድን... read more
ከታቀደለት ሰዓት 35 ሰከንድ የዘገየው የባቡር ሹፌር ለተሳፋሪዎች የጉዞ ክፍያን ተመላሽ ማድረጉ እያነጋገረ ነው
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጃፓን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ሰዓት አክባሪነትን ምን ያህል እንደሚያስከብሩ የሚያሳይ አንድ ያልተለመደ ክስተት ተመዝግቧል።
ከቅርብ... read more
ባንኮች እስከ ምሽት 3፡30 ሰዓት ድረስ ክፍት እንዲሆኑ የሚያስገድደዉ ደንብ ከባንኮች አሰራር ጋር የማይጣጣም ነዉ ሲል የባንኮች ማህበር አስታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣው ባንኮች እስከ ምሽት 3:30 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ከባንኮች አሠራር ጋር የማይጣጣም መሆኑን... read more
ከሰል የማክሰል ሂደቱ በሳይንሳዊ መልኩ ባለመደገፉ ተፈጥሯዊ የአደጋ ስጋቶች እየጨመሩ መሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ የከሰል ምርትን በስፋት ከሚጠቀሙ 5 ሀገራት አንዱዋ ስትሆን ምርቱን ለአለም አቀፍ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ በማቅረብ የሚታወቁ 5 ሀገራት እንዳሉም... read more
ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የኢራን ጦርነት፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀውሱን ለማረጋጋት የሚያደርጉት ጥረት ከሽፏል?
ሰኔ 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዩናይትድ ስቴትስ፣ በታሪክ ትልቁ የተባለውና በኦፕሬሽን “ኤፒክ ፉሪ” (Operation Epic Fury) የጀመረው የኢራን ጦርነት፣ ከፕሬዝዳንት... read more
የዓለማችን ብቸኛዋ ሰው አልባ አህጉር አንታርክቲካ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአለማችን ላይ ብቸኛዋ ቋሚ ነዋሪ የሌላት አህጉር አንታርክቲካ መሆኗ ተገለጸ። ይህች በበረዶ የተሸፈነች አህጉር ምንም እንኳን... read more
ሲፈን ሀሰን ነሀሴ ወር ላይ በሚደረገው የሲድኒ ማራቶን ላይ እንደምትካፈል አሳወቀች
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰኝ በመጪው መስከረም ወር ላይ በሀገረ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ላይ በሚከናወነው... read more
በእግረኞች መንገድ በተሽከርካሪ የሄደው ግለሰብ 100 ሺህ ብር መቀጣቱ ተገለፀ
ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በአቃቂ ክፋለ ከተማ በእግረኞች መንገድ ላይ በኮድ 4... read more
ምላሽ ይስጡ