መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በየመን ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ በየመን መንግሥት ኃይሎችና በኢራን በሚደገፉት የሑቲ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ዜጎች ከየመን ወደ ጅቡቲ እየተሰደዱ መሆናቸውን የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ መረጃም በሀገሪቱ ከሚገኙና ከተመዘገቡ ስደተኞች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን በርካታ እንደሆኑ ገልጿል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ የእስያና ፓሲፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ደዋኖ ከድር ሚኒስቴሩ በየመን በሥጋት ውስጥ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በአካባቢው ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ ቢሆንም በተቻለ መጠን ለዜጎች ለመድረስ እየተሞከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ባሉበት እንዲቆዩና እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የማድረግ፣ እንዲሁም ድጋፍ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ በየመን የሚገኙ የተወሰኑ ነዋሪዎችን በሚኒስቴሩ በኩል እንደሚያገኟቸው የተናገሩት አምባሳደር ደዋኖ፣ ሌሎቹንም ያሉበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ በየመን እየተካሄደ ባለው ጦርነት በርካታ ዜጎች በቀይ ባሕር በኩል ወደ ጅቡቲ እየገቡ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የሰራተኛ ደመወዝ ግብር የማይከፍሉ በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኤንባሲዎች ወደ ክፍያ ስርዓቱ እንዲገቡ እየተደረገ ነው ተባለ
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከተማዋ የሰራተኛ ደመወዝ ግብር የማይከፍሉ የተለያዩ ሀገራት ኤንባሲዎች ወደ ክፍያ ስርዓት እንዲገቡ እያደረገ መሆኑን የአዲስ... read more
የታላላቅ ኃያላን ፍልሚያ በቤጂንግ፦ ሺ ጂንፒንግ ዶናልድ ትራምፕን ካስተናገዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ቭላድሚር ፑቲንን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተቀበሉ!
ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም ፖለቲካ ትኩረት አሁንም በቻይና መናገሻ ከተማ ላይ ያረፈ ሲሆን የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የአሜሪካውን... read more
ራሱን “መከላከያ ነኝ” በማለት ጤፍ የሰረቀው ግለሰብ በህብረተሰብ ክትትል ተይዞ በ5 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሸዋሮቢት ከተማ፣ የ10 ዓመት ህፃንን "የመከላከያ ሰራዊት አባል ነኝ" በማለት አታልሎ 80 ኪሎ ግራም ጤፍ የሰረቀ... read more
ቼልሲዎች ለማይክ ሜኞ ያቀረቡት የመጀመሪያ ዙር ጥያቄ ውድቅ የተደረገ ሲሆን፥ ሚላኖች እስከ 45 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚጠብቁ አሳውቀዋልቼልሲ እና ማይክ ሜኞ ስማቸው በድጋሚ እየተያያዘ ይገኛል።
ሰኔ 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቼልሲዎች ግብ ጠባቂ ፍለጋ ወደ ገበያው መውጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ዋና ትኩረታቸው የሆነውን ማይክ ሜኞን ለማስፈረም... read more
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የክህሎት ማኅበር አባል መሆኗን ተከትሎ፣ በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ የክህሎት ውድድሮች ደረጃቸውን ጠብቀው እስከ ዓለም አቀፍ መድረኮች የሚዘልቁበት ግልጽ አሠራር መዘርጋቱ ተገለጸ
ሰኔ 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ የዓለም የክህሎት ማኅበር አባል መሆኗን ተከትሎ፣ በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ የክህሎት ውድድሮች ደረጃቸውን ጠብቀው እስከ ዓለም... read more
የመሬት መንቀጥቀጡ በከሰም ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ጉዳት አደረሰ
ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዋሽ ፈንታሌ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በከሰም ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
በአፋር ክልል... read more
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት ሆነው ተመደቡ
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ... read more
ማንቸስተር ዩናይትድ በአዲስ ባለሀብት እጅ ሊወድቅ መድረሱን ቱርኪ አል-ሼክ ፍንጭ ሰጡ
መስከረም 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሳዑዲ ዓረቢያ የስፖርት እና የመዝናኛ ባለሥልጣን እንዲሁም ታዋቂው የቦክስ ፕሮሞተር ቱርኪ አል-ሼክ የእንግሊዙን ታላቅ ክለብ ማንቸስተር... read more
በጅማ ከተማ የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት ተከትሎ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ለመጎብኘት የሄዱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባረፉበት ሆቴል... read more
ምላሽ ይስጡ