መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን (Tigray TV) ላይ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እገዳ መጣሉን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። ባለሥልጣኑ በመግለጫው እንዳስታወሰው፣ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሬቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ባደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነት መሠረት ቀደም ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ መመለሱ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የሰላም ግንባታና የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሚዲያው ወደ ሕገ-መንግሥታዊና ሙያዊ መስመር እንዲመለስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ቴሌቪዥን በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ እና የሙያ ሥነ-ምግባር አክብሮ አገልግሎት መስጠት ሲገባው፣ የሀገርንና የሕዝብን ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ እየተላለፉበት እንደሚገኝ በተደረገው የሚዲያ ይዘት ክትትልና ግምገማ ማረጋገጡን ባለሥልጣኑ ገልጻል። በመሆኑም በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ጣቢያው ላይ ይህንን እገዳ ለመጣል መወሰኑን አስታውቋል። በመጨረሻም ማንኛውም ዲጂታል፣ ብሮድካስትም ሆነ የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያው በሕገ-ወጥ መንገድ የሚያሰራጫቸውን ይዘቶች አሰራጭቶ ወይም አስተጋብቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳስቧል። ይህንን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም ሚዲያ ላይ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች የሚወስድ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በሰራተኞች አድማ ምክንያት አየር መንገዱ በረራዎቹን ለጊዜው አቋረጠ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የካናዳ አየር መንገድ(Air Canada)በአድማ ላይ ያሉ የበረራ አስተናጋጆች ወደ ስራ እንዲመለሱ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ባለመቀበላቸው... read more
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር እየተዘጋጀሁ ነው አለ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማርና ሌሎች ተግባራትን በላቀ ደረጃ ለመፈፀምና ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ... read more
የምድር ህልውና አደጋ ላይ ነው
🔰ሳይንሳዊ ግኝቶች ምን ይላሉ?
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ናሳ እና ቶሆ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት የቅርብ ጊዜ ጥናት፣ ምድር ለዘለቄታው የመኖሪያ ምቹነት... read more
ሩሲያ የድሮን ስጋትን የሚቀይር አዲስ ጥይት ሰራች
👉ከአውቶማቲክ ጠመንጃ ሲተኮስ ወደ ሦስት ተከፍሎ ድሮኖችን የሚያሳድደው “ምኖጎቶቺዬ” በጦር ሜዳ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው! ሐምሌ 03 ቀን... read more
ድሪቤ ወልተጂ የመጀመሪያው የግራንድ ስላም ክብርን ካሸነፉ አትሌቶች መካከል አንዷ መሆኗ ተረጋግጧል
በትራክ ውድድሮች ታሪክ ከፍተኛውን የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኘው የግራንድ ስላም ውድድር በጃማይካዋ ኪንግስተን ከተማ እየተከናወነ ይገኛል።
በቅርብ አመታት በውድድር ቁጥር ማነስ ምክንያት... read more
ኤጀንሲው ከፍርድ ቤቶች ጋር በጀመረው የጋራ ስራ በዓመት 1ሺሕ 598 የፍቺ ውሳኔዎችንና 127 የጉዲፈቻ አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል
ሐምሌ 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተጀመረው ከፍርድ ቤቶች ጋር የመስራት ሂደት በአመት 1ሺሕ 598 የፍቺ ውሳኔዎችንና 127 የጉዲፈቻ... read more
አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ
አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።
ሀገረ ስብከቱ... read more
ቬትናም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚሰሩ የትራፊክ ካሜራዎችን ልትጠቀም ነው
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቬትናም የትራፊክ ፍሰትን እና የህግ ጥሰቶችን ለመቆጣጠር በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ካሜራዎችን ለመትከል በዝግጅት ላይ... read more
በኢትዮጵያ በኩላሊት በሽታ ላይ በቂ ጥናት እየተደረገ እንደማይገኝ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ተናገረ
ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) እንደ ሀገር በገዳይነቱ እየታወቀ የመጣው የኩላሊት በሽታ ትኩረት ተሰጥቶት በቂ ጥናት እየተደረገበት አለመሆኑን የኩላሊት... read more
በቤትዎ ውስጥ የሚያዩት ግዙፍ ሸረሪት ጥቃት አድራሽ ሳይሆን የቤቶ ዘበኛ ሊሆን ይችላል ተባለ
ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በክፍልዎ ግድግዳ ላይ ግዙፍ ሸረሪት ተንጠልጥሎ ሲያዩ የመጀመሪያ ምላሽዎ በጫማ መምታት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን... read more
ምላሽ ይስጡ