መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ፅህፈት ቤት በቀጠናው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን አስታወቀ። ፅህፈት ቤቱ ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመግታትና በሰብል ላይ የሚያደርሰውን ውድመት ለመከላከል ያለመ አስቸኳይ የኬሚካል ርጭት ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነገ የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል። በዚሁ መሠረት የመከላከያ ርጭቱ ዛሬ ምሽት ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚከናወን ሲሆን፣ ርጭቱ በሚካሄድባቸው ቦታዎች ላይ ኬሚካሉ ለጤና አደገኛ ሊሆን ስለሚችል አካባቢዎቹ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት ንክኪ ሙሉ በሙሉ ነፃ መደረግ እንዳለባቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። በተጨማሪም ዘመቻው የተሳካ ይሆን ዘንድ ህብረተሰቡ ከግብርና ባለሙያዎች ጎን በመቆም ወፎቹ የሚያድሩበትን ትክክለኛ ቦታ በመለየት፣ መረጃ በመስጠትና አሰሳ በማድረግ ንቁ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ተ አስተላልፏል። የአካባቢውን ግብርና ከጥፋት ለመታደግ ከተማ አስተዳደሩ ያስተላለፈውን ይህንን አጣዳፊ መረጃ ነዋሪዎች እርስ በርሳቸው በማጋራትና ላልሰሙት በማድረስ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠይቋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ተማሪዎች ለሱስ ተጋለጭ እንዳይሆኑ ወላጆች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ
መስከረም 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ/ም ሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ መጀመራቸው ይታወቃል። ከዚህ ጋር... read more
በቤትዎ ውስጥ የሚያዩት ግዙፍ ሸረሪት ጥቃት አድራሽ ሳይሆን የቤቶ ዘበኛ ሊሆን ይችላል ተባለ
ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በክፍልዎ ግድግዳ ላይ ግዙፍ ሸረሪት ተንጠልጥሎ ሲያዩ የመጀመሪያ ምላሽዎ በጫማ መምታት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን... read more
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 1.5 ሚሊየን የሚጠጉ ጎብኚዎች ወደ ላሊበላ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ ባለንበት ወርሃ ታህሳስ መጨረሻ ላይ የሚከበረዉን የገና በዓል በስፋት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ የላሊበላ... read more
በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተጣራባቸው አሥራ አንድ ተጠርጣሪዎች ክስ ተመስርቶባቸዋል – የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ሕዳር 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተጣራባቸው አሥራ አንድ ተጠርጣሪዎች ክስ እንደተመሰረተባቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ክስ የተመሰረተባቸውም1ኛ ተከሳሽ... read more
15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ የጥናት እና ምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ነው
ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ 15ኛውን አለም አቀፍ... read more
ቼልሲ ወሳኝ ክህሎት ያለውን ተጫዋች ለረጅም አመት አራዝመዋል
ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ጆሽ አቼምፖንግ በሪያል ማድሪድ እንዲሁም በሌሎች ሊጎች በጥብቅ ሲፈለግ የቆየ ተጫዋች እንደነበር አይዘነጋም። ይህ ተጫዋች ውሉ... read more
ጎንደር ለጥምቀት በዓል ከመላው ዓለም የሚመጡ ታዳሚዎችን ለመቀበል ዝግጅቷን አጠናቃ በመጠባበቅ ላይ ነች👉የጎንደር ከተማ አስተዳደር
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የጥምቀት በዓልን ለማክበር ወደ ጎንደር የሚመጡ ታዳሚዎችን ለመቀበል ከተማዋ ዝግጁ መሆኗን የጎንደር ከተማ... read more
#አዲስ_ጥናትየቴሌቪዥን ስርጭት ዘመን ሊያበቃ ነው? ወጣቱ ትውልድ ዜና የሚያይበት አስገራሚ መንገድ ይፋ ሆነ!
ሰኔ 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለማችን ላይ የመደበኛ ቴሌቪዥን ስርጭት (Broadcast TV) ዘመን በፍጥነት እያከተመለት መሆኑንና የዜና ፍጆታ ወደ ማህበራዊ... read more
ተቃዋሚ ፓርቲ በምርጫ ተቃውሞ ወደ 700 የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል አለ
ጥቅምት 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታንዛኒያ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ በምርጫው ውጤትና ሂደት ላይ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ፣... read more
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ በማሰባሰብ ላይ መሆናቸውን ክልሎች ገለጹ
ነሐሴ 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በክረምቱ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ... read more
ምላሽ ይስጡ