መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ አመላክቷል። የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ በድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ የውጭ እርዳታ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ በሀገር ውስጥ አቅም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በአዋጅ የተቋቋመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል። ፈንዱ ከቴሌኮም እና ባንክ አገልግሎቶች ክፍያ፣ ከሎተሪ አገልግሎት፣ ከአክስዮን ክፍፍል፣ ከኬሚካል ሽያጭ፣ ከፓስፖርት፣ ቪዛ፣ ንግድ ፈቃድ አገልግሎቶች እና ከሌሎችም አማራጮች የሚሰበሰብ ነው። በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ስር በሚተዳደረው በዚህ “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” በ6 ወር ውስጥ 15.5 ቢሊየን ብር እንደተሰበሰበ ኮምሽኑ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገልጿል። ከተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ውስጥ 4.9 ቢሊየን ብር ለአደጋ ጊዜ ምግብ ግዢ እንደዋለም ተገልጿል። በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች ያሉ ሲሆን፣ በአደጋ ስጋት ምላሽ የሚሰበሰበው ፈንድ እነርሱን ለመደገፍ አገልግሎት ይውላል ተብሏል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የአገር ውስጥ እና የውጭ ድርጅቶች የግል ጥቅማቸውን ማዕከል በማድረግ በኢትዮጵያ ያሉትን የተረጂዎች ቁጥር አጋነው እንደሚያቀርቡ ተመላክቷል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠቃሚ ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች:- የእለት ደራሽ እርዳታ ፈላጊዎች፣ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች፣ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተፈናቀሉ፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችና በየቦታው የሚኖሩ ዜጎች፣ የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች እንዲሁም የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው የስደት ተመላሾች መሆናቸው ተገልጿል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
እስራኤል እና ሃማስ በዩናይትድ ስቴትስ የተደገፈውን የተኩስ አቁም ሁለተኛ ምዕራፍ በቅርቡ ይጀምራሉ
ሕዳር 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል እና የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስ የረዥም ጊዜ የሰላም ዕቅድ... read more
ሰማያዊ ታክሲዎች ላይ የተወሰነው የመጨረሻው ውሳኔ 👉
https://youtu.be/s1Yc6kecpJk
read more
በዘረኝነት ጥቃት ምክንያት የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር በቤንፊካ ላይ ቅጣት አስተላለፈ
መጋቢት 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር (UEFA) የፖርቹጋሉ ክለብ ቤንፊካ በዘረኝነት ጥቃቶች ጋር በተያያዘ ቅጣት እንደተላለፈበት አስታውቋል። ማኅበሩ... read more
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አዲስ አበባ ገቡ
የካቲት 07 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ... read more
ባለፉት አስር ቀናት ብቻ ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ ለስርቆት መዳረጉ ተገለጸ
ባለፉት አስር ቀናት ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የኦ.ፒ.ጂ ደብሊው ፋይበር መስመር... read more
በዋግኽምራ ዞን እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በዳስ የሚማሩ ተማሪዎች አሉ ተባለ
👉ተማሪዎች #በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆነው እንደሚማሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል
በዋግኽምራ የሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃውን ወደ ጠበቁ መማሪያ ክፍሎች... read more
ባሳለፍነው አመት 52.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የህክምና ግብአቶች ግዢ መፈጸሙ ተገለጸ
ጥቅምት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በ2017 ዓ.ም 52.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የህክምና ግብአቶች ግዢ መፈጸሙን የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ለጣቢያችን... read more
የሲቪል ምዝገባ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፍርድ ቤት ተጀመረ
ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና... read more
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚፈጠሩ ሃይቆች በ72 ማህበራት ተደራጅተው የአሳ ማስገር ስራ እንደሚሰሩ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አስታወቀ
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫነት ባሻገር፤ ተጨማሪ ግድቦችንና ሐይቆችን በመፍጠር በዓሳ ሃብት ላይም... read more
በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተከሰሱ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል... read more
ምላሽ ይስጡ