መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ የፕሮጀክቱ ዋነኛ አካል በሆነው የፍልሰት ግንዛቤ ማስጨበጫና የሙያ ስልጠና መሰረት፣ ተመላሾችን በተለያዩ የሙያ መስኮች አሰልጥኖ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት ማስመረቁን አስታውቋል። በ10ኛው ዙር የስልጠና መርሃ ግብሩ ለ30 ወጣቶች ስልጠና ሰጥቶ ማስመረቅ መቻሉን የንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል መለሰ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። ከስደት ተመላሽ ወጣቶቹ በምግብ ዝግጅት፣ በውበት ሳሎን፣ በቤት አያያዝና ላውንደሪ፣ እንዲሁም በልጆች እንክብካቤ የሙያ መስኮች ላይ ስልጠና መውሰዳቸውንም ገልጸዋል። ተቋሙ ከተቋቋመ ገና ሁለተኛ ዓመቱ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ወጣቶች በሀገራቸው የሥራ እድል ፈጥረው እንዲሰሩና በፍልሰት ዙሪያ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ የሚያግዙ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ አብራርተዋል። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ 30 ወጣቶችን አሰልጥኖ ቢያስመርቅም፣ ወደፊት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሰልጣኞችን በተለያየ የሙያ ስብጥር አስመርቆ ሥራ ለማስቀጠር እንደሚሰራ ተገልጿል። አሁን ላይ ከተመረቁት 30 ከስደት ተመላሽ ወጣቶች መካከል 11ዱ ሥራ መጀመራቸውን አቶ ዳንኤል ተናግረዋል። ቀሪዎቹ ሰልጣኞችም በቅርቡ ሥራ እንደሚያገኙ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሰብሃዲን ሱልጣን አስታውቀዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በያዝነው የክረምት ወር እና በመጪው አዲስ አመት ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ጥሪ እንደሚደረግ ተገለፀ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በተለያዩ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ እንዲሁም... read more
የጥምቀት ኤክስፖ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ ነው ተባለ
ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በመዲናችን አዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚካሄደው ኤክስፖው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ፤ ከሙዚቃ እና ከአልኮል... read more
የፌዴራል መንግሥት ባስፈለገ እና በተገደበ ሁኔታ በክልሎች ጣልቃ እንዲገባ የሚያስችለው አዋጅ መጽደቁ የዜጎችን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋግጥ ያግዛል ተባለ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የአዋጁ... read more
በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የገንዘብ እና የመሥሪያ ቦታ እጥረት ለዘርፉ ዋነኛ ተግዳሮቶች መሆናቸው ተገለ
ነሐሴ 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአገራችን እየተከናወኑ ባሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎች ውስጥ የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት እና ተስማሚ... read more
በክልሉ በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የተሃድሶ ኮሚሽን ስልጠና ዳግም መጀመሩ ተገለጸ
በትግራይ ክልል ከ75,000 በላይ የሚገመቱ የቀድሞ ታጋዮችን ትጥቅ የማስፈታትና በዘላቂነት ወደ መደበኛ ሕይወት ለማስገባት የታቀደው የተሃድሶ ሥልጠና በክልሉ በተፈጠረው የፖለቲካ... read more
የህጻናት ፍትህ የማግኘት መብት ተገቢ ትኩረት እያገኘ አለመሆኑ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ
ህጻናት ለሚገባቸው ፍትህ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ረገድ የሚመለከታቸው አካላት በቅጡ እየሰሩ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
ዛሬም... read more
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች ዩቲዩብን ከለከለች
ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአውስትራሊያ መንግስት ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ዩቲዩብ አካውንት እንዳይኖራቸው የሚያግድ አዲስ ህግ ይፋ አድርጓል። ይህ... read more
ቻይና ስታርሊንክን በልጣ በ2 ዋት ሌዘር እጅግ ፈጣን ኢንተርኔት ማስተላለፏ ተዘገበ
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና በህዋ ላይ ባደረገችው አስደናቂ ግኝት፣ ከስታርሊንክ (Starlink) በአምስት እጥፍ የሚበልጥ ፈጣን የኢንተርኔት ፍጥነት ማግኘት... read more
ቪኒሲየስ ጁኒየር በሪያል ማድሪድ እስከ 2030 የሚቆይበትን አዲስ ውል ተስማማ
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሪያል ማድሪድ እና ብራዚላዊው ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር በኮንትራት ማራዘሚያ ጉዳይ ላይ ከረጅም ጊዜ ድርድር በኋላ ስምምነት... read more
ጀርመናዊ ሐኪም 15 ታካሚዎችን በመድኃኒት ድብልቅ ገደለ በሚል ክስ ለፍርድ ቀረበ
ሐምሌ 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጀርመን ውስጥ አንድ ሐኪም 15 የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን (palliative care) ታካሚዎችን በመድኃኒት ድብልቅ በመግደል ወንጀል... read more
ምላሽ ይስጡ