ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የመኪና ባለቤቶች እና አሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው የሞተር ዘይት ሲገዙ ወይም ሲቀይሩ በዘይቱ መያዣ ላይ የተጻፉትን ቁጥሮች እና ፊደላት ትርጉም ማወቅ የሞተሩን እድሜ ለማራዘም ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። እነዚህ ምልክቶች የዘይቱን ውፍረትና ቅጥነት (Viscosity)፣ የአየር ንብረት ተስማሚነት እና የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የሚገልጹ መረጃዎች ናቸው።
ለአብነት ያህል SAE 5W-30 API SP የሚለውን የሞተር ዘይት ላይ ያለ ምልክት ብንመለከት ትርጉሙ እንደሚከተለው ይብራራል፦
የውፍረትና ቅጥነት መጠን (Viscosity Grade – SAE)
የመጀመሪያው 5W የሚያመለክተው ዘይቱ በብርድ ወይም በቅዝቃዜ ወቅት ያለውን የቅጥነት ደረጃ ነው። W የሚለው ፊደል Winter (ክረምት/ቅዝቃዜ) የሚለውን የሚያስረዳ ሲሆን ከ W በፊት ያለው ቁጥር አነስተኛ በሆነ መጠን ዘይቱ በቅዝቃዜ ወቅት በፍጥነት በመፍሰስ ሞተሩ ሲነሳ ወዲያውኑ የመጠበቅ አቅሙ ከፍተኛ ይሆናል።
ከዳሽ ( – ) በኋላ ያለው 30 ቁጥር ደግሞ ሞተሩ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ በሚሰራበት ወቅት የሚኖረውን የዘይት ውፍረት ያሳያል። ይህ ቁጥር ከፍ ባለ ቁጥር ዘይቱ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ውፍረቱን ሳይለቅ የመጠበቅ አቅሙ የጎላ ይሆናል።
በመቀጠል የሚገኘው API SP የሚለው ምልክት የሰሜን አሜሪካው የፔትሮሊየም ኢንስቲትዩት የጥራት ማረጋገጫ ነው። API ከሚለው ጽሁፍ ቀጥሎ የሚመጣው የመጀመሪያው ፊደል S ከሆነ ዘይቱ ለቤንዚን (Petrol) ሞተር የተሰራ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን C ከሆነ ደግሞ ለዲዘል (Diesel) ሞተር የሚያገለግል ነው።
ከ S ወይም C ቀጥሎ የሚመጣው ሁለተኛው ፊደል (ለምሳሌ SP) የቴክኖሎጂውን አዲስነትና የጥራት ደረጃ ያመለክታል። በፊደላት ቅደም ተከተል መሰረት ሁለተኛው ፊደል ወደ Z በጠጋ ቁጥር ዘይቱ ዘመናዊና ከፍተኛ የሞተር መከላከል አቅም ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።
በተጨማሪም በዘይቱ መያዣ ላይ Full Synthetic የሚል ጽሁፍ ካለ ዘይቱ በላቦራቶሪ የተሰራና ረጅም ርቀት የሚያስኬድ ሲሆን፤ Semi-Synthetic ከሆነ ደግሞ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ ዘይት ቅልቅል ነው። Mineral Oil የሚለው ደግሞ ከተፈጥሮ ድፍድፍ ነዳጅ የተጣራና በየአጭር ርቀቱ መለወጥ የሚኖርበት መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የሚሰጠውን የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ለማገድ በቀረበው ታሪካዊ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ሊመክር ነው
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የሚሰጠውን የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ሙሉ በሙሉ ለማገድ በቀረበው አዲስ... read more
ሀገራዊ ጥቅም ያላቸውን ትላልቅ ጥናቶችን ለማከናወን የበጀት #እጥረት ተግዳሮት ሆኖብኛል ሲል #የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ገለጸ
ኅዳር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሀገራዊ ጥቅም ያላቸውን ትላልቅ ጥናቶችን ለማከናወን የበጀት እጥረት ተግዳሮት እንደሆነበት የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
በበዓል ወቅት በሚከናወን እርድ ለቆዳ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጪው የገና በዓል በሚከናወን እርድ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ምርምር ልማት... read more
ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን በምክክሩ እየተሳተፉ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዜጎችን ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምክክር አስፈላጊ መሆኑን በኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ... read more
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የመፈተኛ ካርድ መለቀቁን የሚገልጽ ዜና
ግንቦት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች የመፈተኛ ክፍል... read more
የትራፊክ መጨናነቅን የሚቀርፍ የቻይና ፈጠራ
👉ተለዋዋጭ የመንገድ መስመሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የከተማ ትራፊክ መጨናነቅ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ትላልቅ ከተሞች ዋነኛ ፈተና ከሆኑት... read more
በግ እየጠበቀች የነበረችን የ9 ዓመት ህጻን አስገድዶ የደፈረ የ60 ዓመት አዛውንት በጽኑ እስራት ተቀጣ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ተከሳሽ አቶ እሳቱ ዳንጎረ የተባለው የ60 ዓመት አዛውንት ጽኑ እስራት የተወሰነበት... read more
ግብፅ በኢራን እና በዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) መካከል በኒውክሌር መርሃ ግብር ትብብር ላይ እያሸማገለች ነው ተባለ
ጥቅምት 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ግብፅ በኢራን እና በዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) መካከል በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ... read more
በመጪዉ የክረምት ወቅት ለጎርፍ አደጋ ስጋት የሚሆን ግድብ አለመኖሩ ተገለጸ
በተለያዩ የሐገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የውሃ ሀይል ማመንጫ ግድቦች መጪውን የክረምት ወቅት ተከትሎ ሞልተው የማስተንፈስ ስራ ከመከናወኑ አስቀድሞ ለማህበረሰቡ የጥንቃቄ መልዕክት... read more
ኮሚሽኑ ለጠቅላላ ጉባኤው የአመካካሪዎች ሥልጠና መስጠት ጀመረ
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አመካካሪዎች ሁለተኛ ዙር ሥልጠናን በአዲስ አበባ... read more
ምላሽ ይስጡ