ሰኔ 18 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) 42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን የፊታችን እሁድ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ከተማ በድምቀት እንደሚካሄድ ተጠቆመ። ከደቂቃዎች በፊት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል።
ይህ ታሪካዊ የሩጫ ውድድር በ12 ክለቦች እና በ4 የክልል ቡድኖች በድምሩ በ16 ክለቦች መካከል የሚከናወን ሲሆን፥ በሴት 74 እና በወንድ 249 በአጠቃላይ 323 አትሌቶች የሚሳተፉበት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ለአንጋፋ አትሌቶች በተዘጋጀው ልዩ ምድብ ውስጥ እስከ 50 የሚጠጉ ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ውድድሩን በበላይነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች የሜዳሊያ እና ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፥ በዚህም መሠረት አንደኛ ለሚወጡ 50 ሺህ፣ ሁለተኛ ለሚወጡ 25 ሺህ እንዲሁም ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ለሚያጠናቅቁ 20 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከት ታውቋል። ፌዴሬሽኑ ለአጠቃላይ የገንዘብ ሽልማት ብቻ ከ400 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የመደበ መሆኑም በመግለጫው ላይ ይፋ ሆኗል።
ይህ ውድድር በየዓመቱ የሚከናወን እና ለአገሪቱ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት ትልቅ የውድድር ምዕራፍ መሆኑን የፌዴሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐሪ ጠቁመዋል። በፌዴሬሽኑ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከሚዲያ አካላት ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ከተሰጠበት በኋላ ፍጻሜውን አግኝቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የአድዋ ድል ታሪክ በአራቱም የሀገራችን ማዕዘን፣ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን አንደበት የሚዘከር መግባቢያ ቋንቋ ነው ሲሉ ክልሎች ገለጹ
የአድዋ ድል ታሪክ በማዕከል ደረጃ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎችና በኢትዮጵያዊያን አንደበት የሚዘከር መግባቢያ ቋንቋ ነው ሲሉ መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው... read more
በጸጥታ ችግር ምክንያት ከ7 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም
በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ7 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ... read more
በ80 ዓመት አዛውንት እናት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ10 ዓመት ፅኑ... read more
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኔቶ አንቀጽ 5 ቁርጠኝነትን እና የ5% የመከላከያ ወጪን አደነቁ
ሰኔ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኔዘርላንድስ ሄግ በተካሄደው የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ የኔቶን የጋራ... read more
በእርዳታ የሚገቡ የምግብና የህክምና መሳሪያዎች ሁሉ ችግር የሌለባቸዉ አድርጎ የማሰብ የገንዛቤ ክፍተት እንዳለ ባለስልጣኑ አስታወቀ
ለእርዳታ ከውጭ የሚገቡ የምግብና የህክምና መሳሪያዎችን የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ቢሆንም ሁሉም የእርዳታ መሳሪያዎችና የምግብ ድጋፎች... read more
በጎረቤት ሀገራት ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ስደተኞች በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ተገለጸ
ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ለበርካታ ዓመታት የሚሰጡት የአጭር ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታና የሕይወት አድን... read more
የአሜሪካው 82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመዝመት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) በዓለም ላይ በፈጣን ደራሽነቱ የሚታወቀው 82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር (82nd... read more
በቤትዎ ውስጥ የሚያዩት ግዙፍ ሸረሪት ጥቃት አድራሽ ሳይሆን የቤቶ ዘበኛ ሊሆን ይችላል ተባለ
ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በክፍልዎ ግድግዳ ላይ ግዙፍ ሸረሪት ተንጠልጥሎ ሲያዩ የመጀመሪያ ምላሽዎ በጫማ መምታት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን... read more
በስፔን ከ39,000 ሄክታር በላይ መሬት በሰደድ እሳት ተቃጥሏል ተባለ
👉በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሰደዳቸውም ተመላክቷል
ነሐሴ 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ስፔን ውስጥ ከ39,000 ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት በሰደድ እሳት መቃጠሉን የሀገሪቱ... read more
አርሰናል ከሪያል ማድሪድ የጨዋታ ዳሰሳ
አለም በጉጉት እየጠበቀው የሚገኘው የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ ማክሰኞ ምሽት ይከናወናል።
ሻምፒዮኖቹ ሪያል ማድሪዶች ክብራቸውን ለማስጠበቅ በወሳኝ ምዕራፍ ፤ እና አጓጊ... read more
ምላሽ ይስጡ