ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አገልግሎቱ 100 የከባድ ጭነት ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ሀገሪቱ የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን የከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ለመዘርጋት የ5 ዓመት ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
የአገልግሎቱ የማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊና ተወካይ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ፤ በመርከብ፣ በከባድ ተሽከርካሪዎችና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታቅዶ በዚህ ዓመት ብቻ 100 የከባድ ተሽከርካሪዎችን በመግዛት አጠቃላይ ቁጥሩን ወደ 6 መቶ 52 ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎቷን ለማሟላት በርካታ ሥራዎችን እየሠራች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፤ ፈጣን፣ ዘመናዊና በተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች የተሳሰሩ አሰራሮችን መዘርጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ አሁን ላይ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት በሂደት ላይ መሆናቸውን አቶ ደምሰው ተናግረዋል፡፡
የባህር ትራንስፖርት ዘርፉ በሰው ሀብት ማብቃት፣ በዘመናዊ አሠራርና በመሣሪያ አቅርቦት ረገድ በሚጠበቀው ልክ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ እነዚህን ክፍተቶች ለማሟላት የ5 ዓመት ዕቅድ ተነድፎ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠትና አሠራሩን ለማቀላጠፍ በርካታ የማሻሻያ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የአሜሪካ መንግሥት ሥራ መቋረጥ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል ዋይት ሃውስ አስታወቀ
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዩናይትድ ስቴትስ ዋይት ሃውስ፣ የፌዴራል ሴኔት የፌዴራል ኤጀንሲዎች ወጪ የሚሸፍነውን ረቂቅ ሕግ (Spending Bill) በጊዜው... read more
አውስትራሊያ የፍልስጤምን መንግስት እውቅና ለመስጠት ማቀዷን ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኔዝ ተናገሩ
ነሐሴ 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ሀገራቸው የፍልስጤምን መንግስት እውቅና እንደምትሰጥ አስታወቁ። ይህ ውሳኔ በመጪው መስከረም... read more
15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ የጥናት እና ምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ነው
ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ 15ኛውን አለም አቀፍ... read more
81 በመቶ የሚሆኑ የንግድ ባንክ ደንበኞች የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ዲጂታል ፋይናንስን ለማስፋፋት ካቀደው እቅድ ቀድሞ ማሳካት መቻሉን አመላክቷል፡፡
የዲጂታል ስርዓቱ መስፋፋት በአገልግሎት አሰጣጥ ሒደት... read more
የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶችን የማጠናከሪያ ትምህርት ከመስጠት ባለፈ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን መፈተሸ ይገባል ተባለ
ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ምንም ተማሪ ለማያሳልፉ 700 ያህል... read more
ባለፉት 2 ዓመታት ከ100 በላይ ሰራተኞች ከኮሚሽኑ ስራ መልቀቃቸው ተገለጸ
ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጊዜያት ከ100 በላይ ሰራተኞች ኮሚሽኑን ለቀው መውጣታቸውን የፌዴራል የሥነ ምግባር እና... read more
በያዝነው የክረምት ወር እና በመጪው አዲስ አመት ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ጥሪ እንደሚደረግ ተገለፀ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በተለያዩ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ እንዲሁም... read more
ኢትዮጵያ በቅርቡ የተቀላቀለችው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ለሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር ስኬታማነት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ
ጥር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ የተገለጸው በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በተመራውና ከ40 ኩባንያዎች የተውጣጡ 48 ተወካዮችን ባቀፈው... read more
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተጨመረለት የ1 ዓመት የስራ ቆይታ አጀንዳዎችን የመቅረፅ እና ይፋ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ገለጸ
ሰሞኑን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ... read more
ምላሽ ይስጡ