ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ አዋጅ መዘጋጀቱን ተከትሎ፣ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት እንዳይዳከሙ መጠናከር እንደሚገባቸው በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት ለጣቢያችን ገልጸዋል።
በአገር ውስጥ ያለው የፋይናንስ አሠራር እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ አገር በቀል የሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ማደግ በሚገባቸው ልክ እንዳያድጉ ማድረጉን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢንተርፕራይዝ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ፍሥሐ ተስፋዬ ገልጸዋል። በአንጻሩ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በጋራና በጥምረት ሊሠሩባቸው የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት ማጠናከር እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ በርካታው የማኅበረሰብ ክፍል የሚገኘው በአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ እንደመሆኑ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የኅብረት ሥራ ተቋማት አቅማቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የኢንፊኒቲ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስክንድር መኩሪያ ይገልጻሉ። በተለይም ደግሞ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የሚስተዋለው የትብብር ማነስ፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረትና ተደራሽነት፣ እንዲሁም ጠንካራ ተቋማት ጥቂት መሆን ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ መጀመራቸው ለትልልቅ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እና ለውጭ ምንዛሬ አቅርቦት በጎ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል። ከሰሞኑ በኢንቨስትመንት ባንክ ሥራ ላይ የተሰማራው የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ በካፒታል ገበያ ላይ ሕጋዊ ፈቃድ ያገኘ ሲሆን፣ በቀጣይም በኢትዮጵያ በባንክ አገልግሎት ዘርፍም ሆነ በኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰማሩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፈቃድ አግኝተው ሥራ ሲጀምሩ ለኢኮኖሚው ጠቃሚ እንደሚሆኑና በአገር በቀል ባንኮች ላይ ጫና እንደማያሳድሩ አመላክተዋል።
የውጭ አገር ባንኮች በአገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚፈቅደው አዋጅ መጽደቁ የሚታወስ ሲሆን፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶች እንዲሠሩ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅም በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ባሳለፍነው አመት 52.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የህክምና ግብአቶች ግዢ መፈጸሙ ተገለጸ
ጥቅምት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በ2017 ዓ.ም 52.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የህክምና ግብአቶች ግዢ መፈጸሙን የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ለጣቢያችን... read more
በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በደብረብርሃን ከተማ በእሳት አደጋ የአንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል ተባለ
በተጨማሪም በሐረር ከተማ ዛሬ ሌሊት 8፡00 ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ነው የተባለው
በደብረ ብርሀን ከተማ በደረሰ... read more
ለሀገራዊ ምክክሩ ጉባኤ አጀንዳዎች ተለይተው መቅረባቸው ለውይይቱ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ
ሰኔ 19 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን መሠረታዊ ችግሮች በምክክር ለመፍታት ስታደርገው የነበረው ጥረት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ይታወቃል።
ሀገራዊ የምክክር... read more
በህገ ወጥ መንገድ 24 ሰዎችን ሲያጭበረብሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋም አካባቢ በመሆን አስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት መሰጠት ቆሟል እኛ እናሰራላችሁ በማለት ተቋሙ ለ5 ቀን 20 ሽህ የሚያስከፍለውን... read more
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አዲስ አበባ ገቡ
የካቲት 07 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ... read more
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ተማሪዎቻቸው ከተመረቁ በኋላ ወደ ሥራው ዓለም በቀጥታ እንዲገቡ የሚያስችሉ ትስስሮችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እየፈጠሩ መሆናቸውን ገለጹ
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተያዘው የሰኔ ወርና በመጪዎቹ ጊዜያት በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የሚያስመርቁ መሆኑን ተከትሎ፣ መናኸሪያ ሬዲዮ... read more
የባህር በር መነጠቅና ያልታከመ ቁስል
Ethiopia| የአፍሪካ ቀንድ አንጋፋና ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ሀገር ኢትዮጵያ፣ ለዘመናት ባለቤት የነበረችውን የባህር በር በማጣቷ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የጂኦፖለቲካዊ ችግሮች... read more
ጀርመን ሙሉ በሙሉ በሃይድሮጂን ኃይል የሚሰራ የባቡር መርከቦችን ስራ አስጀመረች
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ጀርመን በዓለም የመጀመሪያውን ሙሉ በሙሉ በሃይድሮጂን ኃይል የሚሰራ የባቡር መርከቦችን በማስጀመር በአረንጓዴ ትራንስፖርት አብዮት ግንባር... read more
ፈረንሳይ የራሷን የክሩዝ እና ባሊስቲክ ሚሳይል መከላከያ “ጋሻ” እየገነባች መሆኑ ተገለጸ
መጋቢት 14 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፈረንሳይ የአውሮፓን ወታደራዊ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እና የውጭ ጥገኝነትን ለመቀነስ የምታደርገው ጥረት አካል የሆነውን፣ የራሷን ብሔራዊ የአየር... read more
ከግብፅና ከሱዳን ከሚነሱ ውዝግቦች በተጨማሪ የሀገር ውስጥ የውሃ ሀብት አስተዳደር የግጭት መንስኤ እንዳይሆን ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ
ሐምሌ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሰሞኑ ባዘጋጀው በተፋሰስ ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ዙሪያ በተካሄደው የባለድርሻ አካላት የምክክር... read more
ምላሽ ይስጡ