ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ተግባራዊ በሆነው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ውስጥ የሀገር በቀል እውቀት ከጽሑፍ ያለፈ ለትግበራ የተዘጋጀ አካሄድ የለም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጤና መምህር እና በሀገር በቀል እውቀት ዙሪያ ምርምር የሚያደርጉት ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተጠና ጥናት ቢኖረውም ወደ ትግበራ አልገባም የሚሉት ባለሙያው፣ ሰነድ ማዘጋጀትና መተግበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ሌሎች ተቋማትም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ሀገር በቀል እውቀቶችን አካቶ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲተገበር ለማስቻል የማስፈጸሚያ ሰነድ እየተዘጋጀ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የሀገር በቀል እውቀትና የማህበረሰብ ትስስር ዴስክ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም አለሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፍኖተ ካርታው መተግበር ከጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረ እንደሆነ የተናገሩት ዳይሬክተሯ፣ ነገር ግን የሀገር በቀል እውቀትን አካቶ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ለማስቻል የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን አምነዋል።
ዳይሬክተሯ በሚመሩት የሀገር በቀል እውቀትና የማህበረሰብ ትስስር ዴስክ በኩል የማስፈጸሚያ መመሪያ ሰነድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ይህ ብቻም ሳይሆን አሁን ላይ በካሪኩለም ወይም በስርዓተ ትምህርት ክፍሉም በኩል እንዲሁ የማስፈጸሚያ መመሪያዎች መቀረጻቸውን ገልጸዋል። ስርዓተ ትምህርቱ ሙሉ በሙሉ የሀገር በቀል እውቀትን እንዲያካትት ለማስቻል ነው በቂ ቅድመ ዝግጅት ያስፈለገው ሲሉም አክለው ተናግረዋል።
አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መቅረጽ ያስፈለገው ሀገር በቀል እውቀቶችን ለማካተት እንደሆነ ካሁን ቀደም የትምህርት ሚኒስትሩ መናገራቸው ይታወሳል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በመስቀል ዋዜማ 19 የጉራጌ ዞን መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው በአቶ አንዋር አብራር በኩል ባወጣው ይፋዊ የሚዲያ... read more
መናኸሪያ #ሞግዚት
🔰ቅሬታ ያስነሱት የመዲናዋ ማሳጅ ቤቶች
በመዲኗ አሁን አሁን የማሳጅ አገልግሎት እንሰጣለን የሚሉ ማስታወቂያዎች ነዋሪዎች በስፋት በሚኖሩባቸው አከባቢዎች ላይ ሳይቀሩ መመልከት እየተለመደ... read more
የመንገድ አጠቃቀም መመሪያን ከተላለፉ 37 ሺህ እግረኞች መካከል 16 ሺህ የሚሆኑት ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ተገለጸ
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በ2018 በጀት ዓመት 11 ወራት ውስጥ ተገቢውን የመንገድ አጠቃቀም ደንብ በመተላለፋቸው ለቅጣት ከተዳረጉ 37 ሺህ... read more
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 1.5 ሚሊየን የሚጠጉ ጎብኚዎች ወደ ላሊበላ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ ባለንበት ወርሃ ታህሳስ መጨረሻ ላይ የሚከበረዉን የገና በዓል በስፋት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ የላሊበላ... read more
ዩናይትድ ስቴትስ የፍልስጤምን እውቅና በተመለከተ የፈረንሳይን ዕቅድ ‘በፅኑ እንደምትቃወም’ ገለጸች
👉ሳውዲ አረቢያ ግን 'ታሪካዊ ውሳኔ' ስትል አመሰገነች::
ሐምሌ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ ፍልስጤምን እንደ መንግስት እውቅና ለመስጠት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን... read more
የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭት ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ሊስፋፋ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭትን ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ለማስፋፋት ዝግጅት... read more
ኪም ጆንግ ኡን ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ያለው የጦር ድሮን ማልማት ‘ቀዳሚ ትኩረት’ ነው አሉ
መስከረም 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ሀገራቸው ሰው ሰራሽ አስታውሎትን ያካተተ የጦር ድሮኖችን ማልማት ወታደራዊ... read more
በአማራ ክልል ያለው ግጭት ከቀጠለ በርካታ ወገኖች ለአዕምሮ ጤና ችግር ይጋለጣሉ ተባለ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ከሕወሀት ጦርነት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያሉ ግጭቶች እና ውጥረቶች በተማሪዎች፣ በሴቶች፣... read more
ሙስናን ለመከላከል ከተሰራው ይልቅ የተነገረው ያይላል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ገለጹ
ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ 21ኛው የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሚከበርበት መድረክ የክብር እንግዳ ሆነው በተገኙበት መድረክ... read more
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) በታሊባን መሪና ዋና ዳኛ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ
ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በአፍጋኒስታን በሚገኙ የሴቶችና ልጃገረዶች መብቶች ላይ ከፍተኛ ጥሰት ፈጽመዋል በሚል በታሊባን... read more
ምላሽ ይስጡ