ግንቦት 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ መተላለፍ ምክንያት የመራጮች ምዝገባ በታገደባቸው አካባቢዎች፣ በድምፅ መስጫው ዕለት የመራጮች ምዝገባ ተካሂዶ ሕዝቡ በምርጫው እንዲሳተፍ እንደሚደረግ አስታወቀ። ቦርዱ በተጨማሪም ለቅሬታና ጥቆማ ማቅረቢያ የሚሆን ነፃ የስልክ መስመር ማዘጋጀቱን ገልጿል።
የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ቦርዱ በድህረ-ምርጫ ወቅት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ ከቦርዱ ሕግ ውጪ የመራጮች ምዝገባ ሲያከናውኑ የነበሩ በርካታ ምርጫ ጣቢያዎች በክትትልና በደረሱ ጥቆማዎች መሠረት በጊዜያዊነት እንዲታገዱ ተደርጓል።
ይሁን እንጂ በእነዚህ የታገዱ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎች የመምረጥ መብታቸው እንዳይጣስ ለማድረግ ልዩ ዝግጅት መደረጉን ዋና ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው የድምፅ መስጫ ዕለት፣ በእነዚሁ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ በአንድ ላይ ተከናውኖ ሕዝቡ ቀጥታ በምርጫው እንዲሳተፍ ይደረጋል ብለዋል።
ለቅሬታ ማቅረቢያ “6214” የነፃ ስልክ መስመር ተዘጋጅቷል
ምርጫ ቦርድ የምርጫው ሂደት ግልጽና ፍትሐዊ እንዲሆን ለማገዝ፣ በምርጫው ዕለት ለሚያጋጥሙ ማንኛቸውም ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ማስተናገጃ የሚሆን 6214 የተሰኘ ነፃ የጥሪ መስመር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ያስታወቀ ሲሆን፣ ዜጎች በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዘቧቸውን ሕገ-ወጥ ድርጊቶችና ቅሬታዎች ይህንን የነፃ ስልክ መስመር በመጠቀም እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ያለውን ግጭት በሽምግልና ለመፍታት እየተሰራ ነው ተብሏል
ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ያለውን ግጭት በሽምግልና ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት በሰጠው... read more
ከውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9... read more
ከኒውክሌር ባሻገር፦ ዓለምን የሚያስበረግገው የአሜሪካ “የብረት ክንድ” ምስጢር ሲጋለጥ!
ግንቦት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሜሪካ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎቿን ባትጠቀም እንኳ፣ በሰዓታት ውስጥ የትኛውንም የዓለም ክፍል ማሽመድመድ የምትችልባቸው ግዙፍ ወታደራዊ... read more
የኮሪደር ልማቱ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን ገለጸ
የካቲት 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች የሚገነባው የኮሪደር ልማት ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ... read more
ሱዳን የዓባይ ወንዝ የውሃ መጠን እየጨመረ እንደሚሄድ እና የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥማት እንደሚችል አስታወቀች
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአባይ ወንዝ ከፍታው ሲጨምር የአገሪቱ መንግስት ለህዝቡ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ያስተላልፋል።
በመሆኑም አገሪቱ ትላንት ማክሰኞ በአባይ ወንዝ... read more
ከካንሰር የተሳሳተ ምርመራ ጀርባ የተገኘው አስደንጋጭ እውነት፦ በሰውየው አእምሮ ውስጥ ምን ተገኘ?
ሐምሌ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በስፔን ሀገር የሚኖር አንድ የ60 ዓመት አዛውንት፣ ከቀን ወደ ቀን እየበረታ የመጣ የራስ ምታት ሕመም... read more
አስተግባሪ ያጣው የትንባሆ ቁጥጥር
👉
https://youtu.be/e-KBshnYaRk
read more
“አሜሪካኖች ዲሞክራሲያቸውን ለማዳን 400 ቀናት ቀርቷቸዋል”👉 አነጋጋሪው የፖለቲካ ትንተና
መስከረም 07 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)"አሜሪካኖች ዲሞክራሲያቸውን ለማዳን 400 ቀናት ቀርቷቸዋል" የሚለው አባባል በፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ ሰፊ ትኩረት አግኝቷል። ይህ አነጋገር... read more
አርሰናል የሀቨርትዝን ጉዳት ተከትሎ የቶተንሀምን ዝውውር በመጥለፍ ኤብሬቺ ኤዜን ማስፈረማቸው ተረጋገጠ
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዋናነት የተውትን ዝውውር ነው በድጋሜ እየተመለሱበት የሚገኘው ተብሏል።
እንደሚታወቀው አርሰናል ባለፈው ሀምሌ ወር ከተጫዋቹ ጋር በግል... read more
ከ500 በላይ የሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ከነበሩበት ትምህርት ቤት ወደ ሌላ እንዲዘዋወሩ ተደረገ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቀበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ ከ500 በላይ የሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ እንዲወጡ... read more
ምላሽ ይስጡ