ግንቦት 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ መተላለፍ ምክንያት የመራጮች ምዝገባ በታገደባቸው አካባቢዎች፣ በድምፅ መስጫው ዕለት የመራጮች ምዝገባ ተካሂዶ ሕዝቡ በምርጫው እንዲሳተፍ እንደሚደረግ አስታወቀ። ቦርዱ በተጨማሪም ለቅሬታና ጥቆማ ማቅረቢያ የሚሆን ነፃ የስልክ መስመር ማዘጋጀቱን ገልጿል።
የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ቦርዱ በድህረ-ምርጫ ወቅት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ ከቦርዱ ሕግ ውጪ የመራጮች ምዝገባ ሲያከናውኑ የነበሩ በርካታ ምርጫ ጣቢያዎች በክትትልና በደረሱ ጥቆማዎች መሠረት በጊዜያዊነት እንዲታገዱ ተደርጓል።
ይሁን እንጂ በእነዚህ የታገዱ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎች የመምረጥ መብታቸው እንዳይጣስ ለማድረግ ልዩ ዝግጅት መደረጉን ዋና ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው የድምፅ መስጫ ዕለት፣ በእነዚሁ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ በአንድ ላይ ተከናውኖ ሕዝቡ ቀጥታ በምርጫው እንዲሳተፍ ይደረጋል ብለዋል።
ለቅሬታ ማቅረቢያ “6214” የነፃ ስልክ መስመር ተዘጋጅቷል
ምርጫ ቦርድ የምርጫው ሂደት ግልጽና ፍትሐዊ እንዲሆን ለማገዝ፣ በምርጫው ዕለት ለሚያጋጥሙ ማንኛቸውም ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ማስተናገጃ የሚሆን 6214 የተሰኘ ነፃ የጥሪ መስመር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ያስታወቀ ሲሆን፣ ዜጎች በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዘቧቸውን ሕገ-ወጥ ድርጊቶችና ቅሬታዎች ይህንን የነፃ ስልክ መስመር በመጠቀም እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በኢትዮጵያ በመገኛ ቦታቸው ተለይተው የሚታወቁ ጥራት ያላቸው ምርቶች በመልክዓ ምድራዊ አመላካች ሥርዓት በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ ለማድረግ የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተገለፀ
አንድን ምርት የተመረተበት አካባቢ በሚሰጠው ጥራት ወይም ልዩ ባህሪ መሰረት አድርጎ ለሸማቾች እንደሚያቀርቡ ይታወቃል፡፡ በዘመናዊው የንግድ ስርዓት ውስጥም የተለያዩ ምርቶች... read more
ኢትዮጵያ በከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ቀውስ ውስጥ—ዋና መንስኤዎች እና መፍትሄዎች
👉የስነ-ልቦና ቀውስም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል
በኢትዮጵያ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚጠፋው የዜጎች ሕይወትና የሚደርሰው አካል ጉዳት ቁጥር ከምንጊዜውም በላይ አሳሳቢ... read more
ፓርቲው ከተሰረዘ በኋላ የሚያደረጋቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ኢ-ህገ መንግስታዊ እንደሚሆን ተገለጸ
አንድ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅናውን ካጣ በኋላ የሚያደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴ ኢ-ህገ መንግስታዊ ይሆናል ሲሉ የህግና የፌዴራሊዚም ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
አፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን በ33 ዓመታት ጉዞው የአህጉሪቱን የልማት አቅም በማጎልበት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ተባለ
መስከረም 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን (Africa Capacity Building Foundation - ACBF) ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ለ33 ዓመታት... read more
ኪም ጆንግ ኡን ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ያለው የጦር ድሮን ማልማት ‘ቀዳሚ ትኩረት’ ነው አሉ
መስከረም 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ሀገራቸው ሰው ሰራሽ አስታውሎትን ያካተተ የጦር ድሮኖችን ማልማት ወታደራዊ... read more
ሀገራዊምክክር ኮሚሽን ለውይይት የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ዛሬ ለሕዝብ ይፋ ሊያደርግ ነው
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ላለፉት አራት ዓመታት አጀንዳዎችን በማሰባሰብና በተለያዩ ምዕራፎች በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣... read more
የተፈናቃዮች ሃሳብ እንዲደመጥ እና መፈናቀልም እንዲቆም አሳታፊ አጀንዳ እየተሰበሰበ መሆኑን የሃገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ገለጸ
ታኅሳስ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የተፈናቃዮች ሃሳብ እንዲደመጥ አካታች አጀንዳ የማሰባሰብ ኃላፊነት እንዳለበት ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
እስካሁን በ971ዱም... read more
በሀገራችን ሰላም ሰፍኖ የሚጠበቀው አንድነትና ዕድገት እንዲመጣ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይገባዋል ሲል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ
ኅዳር 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጉባኤው በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር የፀሎት መርኃ ግብር ባከናወነበት ወቅት ነው ይህን ያለው። በመርኃ ግብሩ... read more
የቻይናው Z-19 የጦር ሄሊኮፕተር በውጊያ ሜዳ የሰው አልባ ድሮኖች መቆጣጠሪያ ማዕከል ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ
ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የቻይና ህዝብ ነፃ አውጪ ጦር በዘመናዊ የጦር አቪዬሽን ስልቱ «Manned-Unmanned Teaming» (MUM-T) በመባል የሚታወቀውን... read more
ቀጠናዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ዘገባዎች ሲሰሩ የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም መሰረት በማድረግ መሆን እንዳለበት ባለሙያዎች ገለጹ
በውጭ ቋንቋዎችም ሆነ በሀገር ውስጥ ቋንቋ የሚሰሩ ዘገባዎች የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ባከበረ መልኩ መሆን እንደሚገባው የሚዲያና የጥናት ተቋማት ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
ምላሽ ይስጡ