መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና በቅርቡ በሥራ ላይ የዋለው አዲሱ የፍትሐ ብሔር ሕግ፣ በትዳር ዘመን የተፈራ ንብረት በፍቺ ወቅት እኩል ለሁለት የመከፈል (50/50) የቆየ አሰራርን በይፋ አብቅቶለታል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ማንኛውም ንብረት የሚከፋፈለው ግለሰቡ ለንብረቱ ግዥ ባደረገው ቀጥተኛና በሰነድ የተረጋገጠ የገንዘብ አስተዋጽኦ ላይ ተመስርቶ ብቻ ይሆናል።
ይህ ማለት ለምሳሌ አንድ መኖሪያ ቤት በባልየው ስም የተመዘገበ ከሆነ፣ ሚስትየዋ በቤቱ ላይ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራት የባንክ የክፍያ ሰነዶችን ወይም የቤት ብድር (Mortgage) የከፈለችበትን ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባታል። ይህ ካልሆነ ግን ቤቱ ሙሉ በሙሉ በስሙ ለተመዘገበው አካል የሚሰጥ ይሆናል።
የሕግ ባለሙያዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይህ አሰራር በተለይ የቤት እመቤት የሆኑ እናቶችን ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር እንደሚያጋልጥ እየገለጹ ይገኛሉ። ምክንያቱም እንደ ቤት ውስጥ ሥራ፣ የልጆች አስተዳደግ እና ቤተሰብን የመንከባከብ ያሉ “ገንዘብ ነክ ያልሆኑ” ግዴታዎች እንደ ቀጥተኛ የሀብት ማፍሪያ አስተዋጽኦ ተቆጥረው ድርሻ አያስገኙም።
በተጨማሪም ሕጉ ባለትዳሮች የፍቺ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ ለ30 ቀናት የሚቆይ “የመረጋጊያ ጊዜ” (Cooling-off period) እንዲያሳልፉ ያስገድዳል። በዚህ የ30 ቀናት ቆይታ ውስጥ አንዳቸውም ወገን ሃሳባቸውን ከቀየሩ የፍቺ ጥያቄው ወዲያውኑ ይሰረዛል። ይህ አዲስ የ30 ቀናት የግዴታ ቆይታ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ በቻይና የፍቺ መጠን በ70 በመቶ (70%) ዝቅ ማለቱ ተመልክቷል።
ምንም እንኳን የቻይና መንግስት ይህ ሕግ የቤተሰብ መፍረስን ለመቀነስ እና ትዳርን ለማዳን የታለመ ነው ቢልም፣ ብዙዎች ግን ሕጉ የሴቶችን የንብረት ባለቤትነት መብትና የኢኮኖሚ ዋስትና የሚነካ ነው በማለት እየተቹት ይገኛሉ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ