በእንግሊዝ የሊግ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ አርሰናል በሜዳቸው ኤምሬትስ ስቴዲየም ክሪስታል ፓላስን አስተናግደው መደበኛው 90 ደቂቃ 1 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት በማምራት መድፈኞቹ 8-7 ለማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
በጨዋታው ከእረፍት መልስ ማክስዌል ላክሯ ራሱ ላይ ያስቆጠራት ጎል አርሰናል መሪ መሆን ቢችሉም የኋላኋላ መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ በተጨመሩት 5 ደቂቃዎች የፓላሱ የተከላካይ መስመር ተጫዋች እና የቡድን አምበል ማርክ ጌሂ ባስቆጠራት ጎል ፓላሶችን ወደ ጨዋታ የመለሰች እና በመለያምቱም ትልቅ ተስፋ እንዲሰንቁ ምክንያት የሆነች ጎል ቢያስቆጥርም በመለያ ምቱ 8-7 ተሸንፈው ከውድድሩ ተሰናብተዋል።
መለያምቱን ያመከነው የክሪስታል ፓላሱ ተከላካይ ማክስዌል ላክሯ ሲሆን የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ አምክኖበት ቡድኑ ግማሽ ፍፃሜውን እንዲቀላቀሉ አስችሏል።
የሚኬል አርቴታው ቡድን በቀጣይ በካራባኦ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ከኤንዞ ማሬስካው ቡድን ቼልሲ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
ምላሽ ይስጡ