ታህሳስ 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከ60 ዓመታት በላይ ገላቸውን ሳይታጠቡ በመቆየት “የዓለማችን ቆሻሻው ሰው” የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷቸው የነበሩት ኢራናዊው አሙ ሀጂ በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አሙ ሀጂ በኢራን ገጠራማ አካባቢ እራሳቸውን ከሰው አግልለው ለበርካታ አስርት ዓመታት የኖሩ ሲሆን፣ “ሳሙና እና ውሃ ያሳምሙኛል” በሚል እምነት ገላቸውን ከመታጠብ ተቆጥበው ቆይተዋል።
ከዓመታት ሙከራ በኋላ፣ በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች አሙ ሀጂን አሳምነው ለመጀመሪያ ጊዜ ገላቸውን እንዲታጠቡ አድርገዋቸው ነበር። ሆኖም ግን ገላቸውን ታጥበው ብዙም ሳይቆዩ ጤናቸው እየተዛባ በመሄዱ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።
የአሙ ሀጂ ህይወት እና አመጋገብ እጅግ ያልተለመደ የነበረ ሲሆን፣ ይህ አኗኗራቸውም በዓለም ዙሪያ የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ቆይቷል። የእሳቸው ታሪክ የግል እምነት በሰው ልጅ ምርጫ እና ህይወት ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል እንደ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል።
ምላሽ ይስጡ