ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚኖሩ ህጻናትን ሁለንተናዊ ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል ፖሊሲ ሊጸድቅ መሆኑ ተገልጿል።
ፖሊሲው በቀጠናው ያሉ ህጻናት የሚያጋጥማቸውን ችግር በመፍታት ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን የሚዘረጋ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፤ ለፖሊሲው ግብዓት የሚሆኑ ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማሰባሰብ የህጻናት ረቂቅ ፖሊሲ ማዕቀፍ የቴክኒክ ሙያተኞች ጉባኤም በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ ቆይቷል።
ፖሊሲውን በማዘጋጀት ሂደት ከኢትዮጵያ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተወጣጡ የህጻናት ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት የላቀ ተሳትፎ ማድረጋቸውን የገለጹት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህጻናት ባለሙያ አቶ ዮሃንስ ሰንደቅ ናቸው፡፡
የትምህርት፤ የምግብ፤ የማህበራዊ ጥበቃ መሰረታዊ የህጻናት ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ሌሎች በቀጣው ሃገራት ባሉ ህጻናት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል በሚደረገው ጥረት ፖሊሲው ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
ፖሊሲውን የማዘጋጀት ሂደቱ የ2 ዓመታት ጊዜን የወሰደ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በመዲናችን አዲስ አበባ ከታህሳስ 2 ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው ጉባኤም ከአባል ሃገራቱ የተወከሉ፤ የዘርፉ ባለሙያዎች፤ የህጻናት ፓርላማ አባላት፤ አለም አቀፍ ተቋማት ለፖሊሲው ግብዓት የሚሆኑ ተጨማሪ ሃሳቦችን ማንሳታቸው ተገልጿል።
የኢጋድ ህጻናት ረቂቅ ፖሊሲው በዛሬው እለት በሚጠናቀቀው የኢጋድ የሚኒስትሮች ስብሰባ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ