በሀገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች አኗኗር ከቀን ወደ ቀን መልክ እና ሁኔታ እየቀያየረና እየተባባሰ ስለምጣቱ በርካታ ማሳያዎች አሉ። ለዚህም በምክንያትነት የሚነሳው የብሔር ተኮር የፖለቲካ ስርዓት ነው ።
ብሔር ተኮር የፖለቲካ ስርዓት መከተላችን ብዝሀውም ይሁን እናሳው የማህበረሰብ ክፍል ቋንቋውና ባህሉ እንዲያድግ እንዲሁም ነፃነት እንዲኖረው እድርጓል በማለት በአንድ በኩል ሀሳባቸውን የሚገልፁ አሉ በሌላ በኩል ደግሞ ለዜጎች ሰበዐዊ መብት መጣስ ዋነኛው ምክንያት እንደሆነና ከዚህ ቀደም ይህንን ስርዐት የሚከተሉ ሀገራት ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን በመረዳት የተውት መሆኑን እንዲሁም ለሀገር እድገትና ለዜጎች ነፃነት እንቅፋት እንደሚሆን ነው የሚገለፀው ።
በዛሬው የዳሰሳ ጥንቅራችንም ለበርካታ አመታት ስንከተለው የቆየነው ይህ የፖለቲካ ስርዓት አካሔድ በተጨባጭ ሁኔታ ምን ያህል የብሔር ብሔረሰቦችን መብት አስጠብቋል ስንል በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን ሀሳብ አሳፍረን በስፋት ተመልክተነዋል።
ምላሽ ይስጡ