የሰው ልብስ ቀድዳ የምትነድፈው እና ለሕይወት አስጊ የሆነችው የቻይናዋ “ኤዢያ ነድል አንት” አሜሪካን እያሸበረች ትገኛለች።
ሕዳር 19 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) መነሻዋን ከምስራቅ እስያ ያደረገችውና በከፍተኛ ንክሻዋ የምትታወቀው ወራሪዋ “ኤዢያ ነድል አንት” (Asian Needle Ant) በአሁኑ ወቅት ቢያንስ በ20 የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ መሰራጨቷ ተረጋገጠ። ይህች ጉንዳን በተለይም እንደ ፍሎሪዳ፣ ቴክሳስ፣ ኒውዮርክ እና ማሳቹሴትስ ባሉ ግዛቶች በስፋት እየታየች ሲሆን፣ ከሌሎች የጉንዳን ዝርያዎች በተለየ መልኩ በሰው ልጆች ጤና እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ አዲስ ፈተና እየደቀነች መሆኑን የዘርፉ ተመራማሪዎች ገልጸዋል።
እንደ ባለሙያዎች ገለጻ፣ ይህች ጉንዳን በብዛት የምትገኘው በወደቁ ቅጠሎች፣ በሚበሰብሱ እንጨቶች እና እርጥበት ባላቸው የአፈር ክፍሎች ውስጥ ነው። እንደ ተለመዱት የጉንዳን ዝርያዎች የሚታይ ክምር ወይም ጎጆ ስለማትሰራ፣ ሰዎች ሳያውቁት በመኖሪያ አካባቢያቸው እና በጫካ ውስጥ ለጥቃት ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። የጉንዳኗ ንክሻ ለሰዓታት የሚቆይ ከፍተኛ ስቃይ የሚያስከትል ሲሆን፣ ስል መርፌዋ እንደ ካልሲ እና ቲሸርት ያሉ ቀጫጭን ልብሶችን አልፎ ቆዳን የመንደፍ ብቃት አለው።
የአሜሪካ የግብርና መሥሪያ ቤት (USDA) ባወጣው መረጃ መሠረት፣ የዚህች ጉንዳን መርዝ በአንዳንድ ሰዎች ላይ “አናፊላክሲስ” (Anaphylaxis) የተባለውንና ለሕይወት አስጊ የሆነ ከፍተኛ የአለርጂ ምላሽ ሊቀሰቅስ ይችላል። ይህ ባህሪዋም ከንብ እና ተርብ መርዝ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል። ተቋሙ አክሎ እንደገለጸው፣ ጉንዳኗ ከአየር ንብረት ጋር ያላት የመላመድ ብቃት ከፍተኛ በመሆኑ በአሜሪካ ምድር ቋሚ ነዋሪ ሆና ልትቀጥል እንደምትችል ይገመታል።
ነዋሪዎች በጓሮ አትክልት ስራ እና መሰል እንቅስቃሴዎች ወቅት ወፍራም ጓንት እና ጫማ በመጠቀም እራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም ንክሻ አጋጥሟቸው የመተንፈስ ችግር ወይም ከፍተኛ እብጠት ካዩ በአስቸኳይ ወደ ህክምና ተቋም እንዲያመሩ ይመከራል። የተፈጥሮ አካባቢ ተመራማሪዎች በበኩላቸው፣ ይህች ጉንዳን ለአካባቢው ስነ-ምህዳር ጠቃሚ የሆኑ የሀገር በቀል ጉንዳኖችን እያጠፋች መሆኑ ከፍተኛ ጥናት እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ሰበር ዜና | ሰሜን ኮሪያ ባህር ኃይሏን በኒውክሌር ታጥቃለች፤ ግዙፍ የጦር መርከቦችንም ትገነባለች ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን አስታወቁ!
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው የባህር ኃይል ክፍሏን በታክቲካል የኒውክሌር መሳሪዎች ለማስታጠቅ እና ይበልጥ... read more
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለአማራ ክልል ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል በተከሰተው ድርቅ የከፋ ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ብር... read more
በሃይማኖት ስም በማህበራዊ ሚዲያ ምን እየተሰራ ነው?
https://youtu.be/T9Bwg-uIffs
read more
በመጪው ሰኔ ወር መጨረሻ 21 ባቡር ለተጨማሪ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰማሩ ተጠቆመ
ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ከታኅሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ተግባራዊ የሚደረግ... read more
ያንጎ ግሩፕ በኢትዮጵያ ለ12,500 በላይ ተማሪዎች የመንገድ ደኅንነት ሥልጠና መስጠቱን አስታወቀ
ሕዳር 05 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) መቀመጫውን በዱባይ ያደረገው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ያንጎ ግሩፕ፣ በመላው አፍሪካ እየተገበረ ያለውን “ደኅንነቱ የተጠበቀ የትምህርት ቤት... read more
በሱዳን ዳርፉር ክልል በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ1,000 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሱዳን ምዕራባዊ ዳርፉር ክልል ውስጥ በመራ ተራሮች አካባቢ ታራሲን በተባለች መንደር ላይ በደረሰ ከባድ የመሬት... read more
ቻይና የሰውን ልጅ እርዳታ የማይሹ ሮቦቲክ ነዳጅ ማደያዎችን አስተዋወቀች
ሐምሌ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና ከተሞች የሰውን ልጅ ጉልበት ሙሉ በሙሉ የሚተካ አዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ይፋ መሆኑ ተገለጸ። ይህ አዲስ... read more
ቻይና ጃፓንን አስጠነቀቀች፡ የታይዋን አቅራቢያ የሚሳኤል ማሰማራት እቅድ ‘በጣም አደገኛ’ ሆኗል ተብሏል
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና የታይዋን ደሴት አቅራቢያ የሚሳኤል ማሰማራት እቅድ ጋር በተያያዘ ጃፓንን በግልጽ አስጠንቅቃለች። የቻይና መንግሥት የውጭ ጉዳይ... read more
በትግራይ ክልል በ1 ሺህ 800 ሄክታር መሬት ላይ የዛፍ አንበጣ መንጋ መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
በትግራይ ክልል አዲስ መጤ ‹የዛፍ አንበጣ› የተባለ ተምች መከሰቱን እና እስከአሁንም በ1 ሺህ 800 ሄክትር መሬት ላይ እንደተሰራጨ በግብርና ሚኒስቴር... read more
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ጉዳይ…
https://youtu.be/URhz-qteg9A
read more
ምላሽ ይስጡ