ሕዳር 17 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (ኢ.ሴ.ማ.ቅ) ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የ2019 ዓ.ም የ16ቱ ቀናት የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ንቅናቄ ዘመቻን በይፋ ጀምሯል።
«ለተጎጂዎች ፍትሕ፤ ለወንጀለኞች ተጠያቂነት፤ ለሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ደህንነት» በሚል ሀገር አቀፍ መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ዘመቻ፣ የሴቶች ድምጽ እንዲሰማና የተቋማት ተጠያቂነት እንዲጠናከር ያለመ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገ/መድህን ተናግረዋል። ከኅዳር 16 እስከ ታኅሣሥ 1 ቀን 2019 ዓ.ም በሚቆየውና «ትሰማ» በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ዘመቻ፣ የሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ብሔራዊ አጀንዳ እንዲሆንም ጠይቀዋል።
ሴቶች ለአካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲጂታል ጥቃቶች እንዲሁም ለልጅነት ጋብቻና ግርዛት ተጋላጭ ሲሆኑ፣ በፍርሃት፣ በማኅበራዊ መገለልና በቂ አገልግሎት ባለመኖሩ አብዛኞቹ ጥቃቶች ሪፖርት ሳይደረጉ በመቅረታቸው ተጎጂዎች ፍትሕ እያጡ መሆኑ ተገልጿል።
ሴት ተኮር ግድያን በይፋ የሚገልጽ ዲጂታል የመረጃ ሥርዓት እንዲዘረጋ እና ጥቃቱን በሕግ ለይቶ የሚቀጣ ማሻሻያ እንዲታሰብ ጥሪ ያቀረቡት ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ፌቨን አርአያ ናቸው።
ለተጎጂዎችም የመጠለያ፣ የሕግ፣ የሕክምናና የሥነ ልቦና አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል ተስፋፍተው በቂ በጀት እንዲመደብላቸው፣ የጥበቃ ማዘዣዎች እንዲተገበሩ እንዲሁም የፍትሕና የጸጥታ አካላት ሪፖርቶችን ወዲያው ተቀብለው ፈጣን እርምጃ እንዲወስዱ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። መገናኛ ብዙኃን የተጎጂዎችን ክብር ጠብቀው በኃላፊነት እንዲዘግቡ፣ የሥራና የትምህርት ተቋማት ከጥቃት ነጻ እንዲሆኑ፣ የሃይማኖትና የማኅበረሰብ መሪዎች፣ ወንዶች፣ የልማት አጋሮች እና መላው ማኅበረሰብ ጥቃትን በማውገዝ ተጎጂዎችን እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።
ሴቶች እና ሴት ልጆች በደህንነት፣ በክብር እና በእኩልነት የመኖር መብት ያላቸው መሆኑን በማስገንዘብ፣ የመንግሥት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ እና የእያንዳንዳችን የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ ጾታዊ ጥቃትን በጋራ ለመከላከል እና ለተጎጂዎች ድምጽ መሆን እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
#Ethiopia #WomenRights #16DaysOfActivism #GenderEquality #BreakingNews #ኢትዮጵያ #የሴቶችመብት #ጸረጾታዊጥቃት #ዜና #ማኅበራዊጉዳይ
Related Posts
የኢትዮጵያ ሚዲያ ዳሰሳ፡ በነፃነት፣ በኢኮኖሚ እና በፀጥታ ተግዳሮቶች መካከል
ሙሉ ዘገባውን ለመስማት ሊንኩን ይጫኑ
በተጠናቀቀው የበጀት አመት መገናኛ ብዙሃን መረጃ ለህዝቡ በተለያዩ አማራጮች ከማሻገር ባለፈ የነበራቸው አዎንታዊ እና አሉታዊ ሚና... read more
38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን... read more
ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦችን እንዳስወገደ የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ
ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ 6 ሚሊየን 44ሺህ 402 ብር የሚያወጣ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦች ናቸው... read more
ጊዜዉ ያለፈበት መድሃኒት ቀላቅለዉ ሲሸጡ በተገኙ 105 የመድሃኒት መሸጪያ መደብሮች ላይ አስተዳደረዊ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ መድኃኒት መደብሮች የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ቀላቅለው ይዘው የተገኙና አላግባብ ያስቀመጡ 105 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ... read more
“ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን እኩል የመጠቀም መብት አላት!”
👉
https://youtu.be/9k5xPB890Bg
read more
ጅቡቲያዊው የ60 ዓመቱ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር
ፈረንሳይኛ ፣ እንግሊዘኛ ፣ አረበኛ ፣ አፋረኛና ሱማለኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ባለፉት ሃያ አመታትም በእነዚህ ቋንቋዎች የዲፕሎማሲ ስራውን አሳልጠዋል ።
መሀሙድ የሱፍ... read more
ትንታኔተመድ በሩዋንዳ ላይ ያወጣው አነጋጋሪ ዘገባትንታኔ
👉
https://youtu.be/F8xA6MAmRB0
read more
ስዊድን ለደም ለጋሾች የምትልከው ልዩ መልዕክት ለጋሾቹን ይበልጥ እያበረታታ ነው ተባለ
ነሐሴ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በስዊድን የደም ለጋሾች የሚያገኙት ምስጋና ደም በሰጡበት ወቅት ብቻ የተገደበ አይደለም ። የሰጡት ደም አንድን... read more
ቻይና በ110 ቀናት ውስጥ የአለማችን ሰፊውን የውሃ ውስጥ ዋሻ በመገንባት ክብረወሰን አስመዘገበች
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቻይና በ110 ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የአለማችንን እጅግ ሰፊ የውሃ ውስጥ ዋሻ በመገንባት አዲስ ክብረወሰን... read more
በልደታ ክ/ከተማ በተደረገ የሌባ ጥናት የተለያዩ የተሠረቁ የመኪና ዕቃዎችን ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር መያዙን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሌባ ተቀባዮች ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ የመኪና ዕቃዎችን በማከማቸት ዕቃዎቹን ለማስመለስ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠየቅባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ... read more
ምላሽ ይስጡ