ሕዳር 11 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው የንጉሥ አብዱላህ የፋይናንስ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኘው የሀገሪቱ የሕዝብ ኢንቨስትመንት ፈንድ (PIF) ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ትናንት ኅዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም በደረሰ የሚሳኤል ጥቃት ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ።
በየመን የሁቲ ታጣቂዎች ወደ ሪያድ የተተኮሰውን ሚሳኤል ለመመከት በተወሰደ እርምጃ ሳቢያ በወደቀ ፍርስራሽ በሕንፃው የተወሰኑ ፎቆች እና በአቅራቢያው በሚገኙ ሕንፃዎች ላይ ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን የሳዑዲ ሲቪል መከላከያና የሀገሪቱ የዜና ወኪል (SPA) አረጋግጠዋል። ሆኖም በጥቃቱ ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ታውቋል።
ክስተቱን ተከትሎ የፋይናንስ ዲስትሪክቱ መግቢያዎች በሙሉ ተዘግተው ሰዎች ከአካባቢው እንዲወጡ ሲደረግ፣ አምቡላንሶችና የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች በስፍራው መሰማራታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በሪያድ ረጅሙን ሕንፃ የሚያቅፈው ይህ የንጉሥ አብዱላህ የፋይናንስ ዲስትሪክት ጥቃት ሲደርስበት በዚህ ወር ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ከቀናት በፊትም በሁቲዎች ጥቃት በሳዑዲ አራምኮ ሕንፃ ላይ ተመሳሳይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
ይህ ፍንዳታ በሪያድ የተሰማው የሳዑዲ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን ከአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) አዛዥ አድሚራል ብራድ ኩፐር ጋር በወታደራዊ ግንኙነትና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያዩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መሆኑም ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማሽን ብልሽት ምክንያት አጋጥሞት የነበረውን የጨረር ህክምና አገልግሎት መስተጓጎል ማሻሻሉን ገለጸ
ጥር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለካንሰር ህሙማን አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ህክምናዎች አንዱ የጨረር ህክምና መሆኑን ተከትሎ በማሽን... read more
በግብዓት እጥረት ምክንያት የማምረት አቅሙ በግማሽ መቀነሱን የሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ገለጸ
በቀን ከ150 ሺህ ሊትር በላይ ወተት እና የወተት ተዋፅኦ የማቀነባበር አቅም ያለው የሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ በግብዓት እጥረት ምክንያት እስካሁን በቀን... read more
አውስትራሊያ ያረጁ ጎማዎችን ወደ ባቡር ሀዲድ አስደንጋጭ መምጠጫ በመቀየር የጥገና ወጪን እየቀነሰች ነው ተባለ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አውስትራሊያ የባቡር ሀዲድ ጥገና ወጪን ለመቀነስ እና የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ዘዴ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን... read more
የኢራን ባለስልጣናት 997 የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይት መሣሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን እና 163 ሰዎችን ማሰራቸውን አወጁ!
ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢራን ከፍተኛ የመንግስት አካላት በተደረገው መጠነ ሰፊ ክትትል ከግንቦት እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያኑ... read more
በሰሜን ዋዚሪስታን በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 13 የጸጥታ ኃይሎች ሲሞቱ 14 ንፁሃን ቆስለዋል
ሰኔ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በፓኪስታን ሰሜናዊ ምዕራብ በሚገኘው ሰሜን ዋዚሪስታን ክልል ውስጥ በተፈጸመ ከባድ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት 13... read more
በጋምቤላ ክልል ህጻናት በቤት እንስሳት እየተለወጡ ነው ተባለ
በጋምቤላ ክልል ህጻናትን በቤት እንስሳት የመለዋወጡ ልማድ አሁንም ድረስ አለመቀረፉ እንዳሳሰበው የገለጸው የክልሉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነው፡፡
ቢሮው አሁንም... read more
የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አባላት ሚሊሻዎች ተመጣጣኝ ያልሆኑ እርምጃዎችን እየወሰዱ ህዝቡን እያማረሩ ነዉ ሲሉ ተናገሩ
የካቲት 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት ቅዳሜ እና እሁድ መደረጉ ይታወቃል፡፡በምክር ቤት ዉሎም በክልሉ ያሉ የተለያዩ ችግሮች... read more
የሕግ ማዕቀፍ የሚሻው የማር ምርት
https://youtu.be/RkEjE2P7sok
read more
ኢትዮጵያ በቅርቡ የተቀላቀለችው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ለሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር ስኬታማነት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ
ጥር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ የተገለጸው በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በተመራውና ከ40 ኩባንያዎች የተውጣጡ 48 ተወካዮችን ባቀፈው... read more
ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስደት ተመላሾችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አሰልጥኖ ማስመረቁን ገለጸ
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ የፕሮጀክቱ ዋነኛ አካል በሆነው የፍልሰት ግንዛቤ ማስጨበጫና የሙያ ስልጠና መሰረት፣ ተመላሾችን በተለያዩ... read more
ምላሽ ይስጡ