ሕዳር 02 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከኢራን ጋር የተያያዘ የደህንነት ስጋት መደቀኑን የሚያሳይ መረጃ በመድረሱ ምክንያት የአሜሪካ ጦር ቢያንስ 13 የሚሆኑ የጦር አውሮፕላኖችን በምስራቅ እንግሊዝ ከሚገኘው የሮያል ኤር ፎርስ (RAF) ሚልደንሆል ጦር ሰፈር ማስወጣቱ ተገለፀ።
ከተዛወሩት አውሮፕላኖች መካከል የ KC-135 የአየር ላይ ነዳጅ ፑል አውሮፕላኖች እና የ CV-22 ኦስፕሬይ ወታደራዊ ማጓጓዣዎች የሚገኙበት ሲሆን፤ ወደ ጀርመን፣ እስፓንያ፣ ስኮትላንድ እና አቅራቢያ ወደሚገኘው ሌላ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ተበታትነው እንዲያርፉ መደረጉ ተጠቅሷል።

ይህንን ተከትሎ አሜሪካ በሚልደንሆል እና ሌከንሂዝ የጦር ሰፈሮቿ ላይ ያለውን የደህንነት ጥበቃ ደረጃ ሁለተኛው ከፍተኛ ወደሆነው የጥንቃቄ ደረጃ (FPCON Charlie) ማሳደጓ ተገልጿል።
ይህ እርምጃ አሜሪካ ባለፈው መስከረም ወር ከኢራን የስለላ መረብ ጋር በተያያዘ ከተጠረጠረ የደህንነት ስጋት በኋላ B-1 የቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቿን ከፌርፎርድ ጦር ሰፈር ካስወጣች በኋላ የተወሰደ ሁለተኛው ተመሳሳይ እርምጃ ነው።
የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣናት እርምጃውን የጥንቃቄ ስራ እንደሆነ ሲገልጹ፣ የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ለስራ ስትራቴጂ ሲባል በየጊዜው በጦር ሰፈሮች መካከል እንደሚዘዋወሩ አስታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ