“መጀመርያ ኢትዮጵያን የቀይ ባህር አክሰስ ያሳጣው ውሳኔ ማን ወሰነው? ካቢኔው ይሆናል ብለን የካቢኔውን ዶክመንት ብናገላብጥ የለም።
ካቢኔው አያውቀውም። አይ የለም ምክር ቤት ይሆናል የወሰነው ብለን ብንወስን ምክር ቤቱ አልነበረም፣ ምክር ቤት አያውቀውም ውሳኔውን። የለም የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈረንደም ወስኖ እንዳይሆን እንዳይባል እኛም ነበርን…። የኢትዮጵያ ህዝብ ያልወሰነው፣ ተወካዮቹ ያላዩት ቢያንስ ቢያንስ ካስፈፀመው ካቢኔ ያላየው ውሳኔ ማን ወሰነው?
ማጣትን የሚያክል ነገር፣ ያጣንበት መንገድ ህጋዊነት ችግር እንዳለው ማሳያ፣ ተቋሞች አልገቡበትም፣ ካቢኔው አያውቀውም። አንድ ገፅ ወረቀት ማግኘት አልቻልንም። እንዴት እንዳጣነው የሚያስረዳን፣ ህዝብም የማያውቀው፣ ፓርላማ የማያውቀው፣ ካቢኔው የማያውቀው የኢትዮጵያ የቀይ ባህር አክሰስ ውሳኔ የሚያሳጣ ነገር የወሰነው ማነው የሚል ጥያቄ ማንሳት እንዴት ስህተት ሊሆን ይችላል? ካለ ይነገረን፤ከሌለ ግን ይሄን ውሃ አንስቶ፣ እንደመድፋት አይደለም፣ የህልውና ጉዳይ ነው፣ ማን ወሰነው?”
— ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ