ጥቅምት 27 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቀድሞው የኋይት ሀውስ የጦርነት አማካሪ እና የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሮበርት ፔፕ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላለፉ።
እንደ ኤክስፐርቱ ገለፃ ከሆነ አሜሪካ እና አለማችን በጥልቅ «የግጭት መባባስ ወጥመድ» ውስጥ እየገቡ ይገኛሉ።
ይህንን አለም አቀፍ ስጋት ከጫፍ ያደረሱት ሶስት ዋና ዋና አደገኛ ሁኔታዎች በአንድ ላይ መገናኘታቸው ተገልጿል።
የመጀመሪያው በከፍተኛ ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ የሚከናወነው የስልጣን ሽግግር እና የአገር ውስጥ አለመረጋጋት ነው። ሁለተኛው ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ከኢራን ጋር እንዲሁም በምስራቅ አውሮፓ ከሩሲያ እና ዩክሬን ጋር የተያያዙ ወታደራዊ ግጭቶች ወደ ከፋ የክልላዊ እና አለም አቀፋዊ ጦርነት የመሸጋገር ከፍተኛ ስጋት ናቸው።
በሶስተኛ ደረጃ፣ በሀያላን ሀገራት የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃቶች አለም አቀፍ ወታደራዊ ግጭትን በቀላሉ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ ተብሎ ይታመናል።
ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በታዋቂው «The Diary Of A CEO» ፖድካስት ላይ በተደረገ ቃለ-መጠይቅ ሲሆን፣ የጂኦ-ፖለቲካ ተንታኞች ሁኔታውን በጥብቅ እየተከታተሉት ይገኛሉ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ