ጥቅምት 28 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሰሜን ኮሪያ በአውሮፓ ኅብረት የቀረበለትን የሰብአዊ መብት ውንጀላ ውድቅ አድርጋለች።
የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች ኅብረቱ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ እና ከንቱ ውንጀላዎችን ማቆም እንዳለበት በጥብቅ አሳስበዋል።
ይህ በየዓመቱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መድረክ ላይ የሚስተዋለው እና ኅብረቱ አዳዲስ የውሳኔ ሃሳቦችን በማቅረብ የሚጫነው ጫና አዲስ ጉዳይ አይደለም።
ሰሜን ኮሪያ በየዓመቱ ከሚቀርቡላት ተመሳሳይ ውንጀላዎች ጋር በተያያዘ የለመደችውን ጠንካራ ምላሽ የሰጠች ሲሆን፤ ይሄኛው ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫም ከወትሮው የተለየ አዲስ የጦርነት ዝግጅት ማሳያ ሳይሆን መደበኛ የረጅም ጊዜ የቃላት ጦርነት መሆኑ ታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ