መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከዛሬ ከመስከረም 15/2019 ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ከተማ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ። አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን መምሪያው ገልጻል። ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት እንደሚጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩ በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን የፖሊስ መረጃ አመላክቷል። ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15/2019 ዓ/ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እና ባለ ንብረቶች ህጉን እንዲያከብሩ ያሳሰበው ፖሊስ ማሳሳቢያውን በሚተላለፉት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጻል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ የስነምግባር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአስረጂ መድረክ ሊካሄድ ነው
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአስረጂ... read more
የስኳር ወረርሽኝ በኢትዮጵያ፡ 2 ሚሊዮን ተጠቂዎች፣ አሳሳቢ የህክምና አቅርቦትና የግንዛቤ ክፍተት
በአለም አቀፉ የስኳር ፌድሬሽን የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የስኳር ህመም እንዳለባቸውና በዚህም ከአጠቃላይ ህዝቡ 3.3 በመቶ... read more
በኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን እንደመገበያያ መጠቀም የተከለከለ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትላንትናው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን እንደ መገበያያ... read more
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ደንብ በተላለፉ 280 በሚሆኑ አካላት ላይ የቅጣት እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
ጥር 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በገና በዓል የተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች... read more
የተቀቀለ ስጋን በስፋት ወደ ውጭ ሃገራት በመላክ የሚገኘውን የገቢ መጠን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርጋት የቁም እንስሳት ሃብት ቢኖራትም በገቢ ደረጃ ግን በሚፈለገው ልክ እንዳልተጠቀምንበት የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
የተቀቀለ ስጋን ወደ ውጭ... read more
የጤና ሚኒስቴር ለሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የአምቡላንስ ድጋፍ አደረገ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጤና ሚኒስቴር የማህበረሰቡን ጤና ለማሻሻል በተለይም የእናቶችን፣ ህጻናት እንዲሁም የጨቅላ ህጻናት ህመም እና ሞት ለመቀነስ... read more
ከቀጣይ አመት መጀመሪያ ወራት ጀምሮ ፓርቲዎች ፖሊሲያቸውን ማቅረብ ይጀምራሉ ተባለ
ፓርቲዎች ከቀጣይ አመት መጀመሪያ ወራት ጀምሮ ፖሊሲያቸውን ለህዝብና ለመገናኛ ብዙሃን ማቅረብ እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ... read more
በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ በእብድ ውሻ በሽታ ከ2ሺሕ 700 በላይ ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ
ሐምሌ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ በበሽታው ስርጭት ከአፍሪካ አንደኛ፤ በዓለም ደግሞ ከህንድ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በጥናት መረጋገጡን የአዲስ... read more
ህፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተረት ማንበብ እንዲችሉ በ10 አይነት ቋንቋ መፅሀፍ ቀረበ
ኢትዮጵያን ሪድስ ወይም ኢትዮጵያ ታንብብ ከተመሰረተ 22 አመታት ያቆጠረ ሲሆን አላማውም በኢትዮጵያ የንባብ ባህልን ማሳደግ ነዉ፡፡
ህፃናት ከልጅነታቸው የማንበብ ልምድ እንዲኖራቸው... read more
ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ምርት ማምረት ካቆመች እስከ 50 ቢሊየን ብር በዓመት እንደምታጣ ተጠቆመ
ሰኔ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ለአካባቢ ብክለት የሚዳርጉ እና አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ ምርቶች በሥነ ምህዳር ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት... read more
ምላሽ ይስጡ