መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከዛሬ ከመስከረም 15/2019 ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ከተማ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ። አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን መምሪያው ገልጻል። ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት እንደሚጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩ በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን የፖሊስ መረጃ አመላክቷል። ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15/2019 ዓ/ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እና ባለ ንብረቶች ህጉን እንዲያከብሩ ያሳሰበው ፖሊስ ማሳሳቢያውን በሚተላለፉት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጻል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ማረፊያ_እንግዳ
🔰‘‘ስራዬ መረበ’ሽ ነው፤ እሱን ደግሞ የማደርገው በቴአትር ነው!’’- ደራሲና ዳይሬክተር መዓዛ ወርቁ
ከደራሲና ዳይሬክተር መዓዛ ወርቁ ጋር የተደረገ ቆይታ 👉
https://youtu.be/Ik3kU3GWdgM
read more
አርሰናል ቤን ዋይትን ለመተካት ዓይናቸውን የሮማው ዌስሊ ፍራንካ ላይ መጣላቸው ተሰማ
መጋቢት 14 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቤን ዋይትን በሽያጭ ዝርዝር ውስጥ ሊያካትተው እንደሚችል የሚጠቁሙ ጭምጭምታዎች መደመጥ መጀመራቸውን ተከትሎ፣... read more
ሙስናን ለመከላከል ከተሰራው ይልቅ የተነገረው ያይላል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ገለጹ
ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ 21ኛው የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሚከበርበት መድረክ የክብር እንግዳ ሆነው በተገኙበት መድረክ... read more
በአፍንጫዎ ላይ የሚታየው መስመር ስለ ጤናዎ የሚናገረው ድብቅ ምስጢር
ግንቦት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ብዙ ሰዎች በአፍንጫቸው የታችኛው ክፍል ላይ አግድም የሆነ መስመር ወይም እጥፋት ሲኖር ይስተዋላል። ይህ ምልክት... read more
በህገ ወጥ መልኩ ከሃገር የወጡ 220 ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ
ጂቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር በህገ ወጥ መልኩ ከሃገር የወጡ 220 ፍልሰተኞችን በባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን... read more
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የኢ- ሰርቪስ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታወቀ
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋና ምቹ የሆነ አገልግሎትን ለመስጠትና እንደ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቂ የህግ ጥበቃ ለማድረግ የኢ- ሰርቪስ... read more
የሀገር ውስጥ የቡና ፍላጎት መጨመር ወደ ውጭ በሚላከው ምርት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ
ሚያዚያ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በቡና ምርቷ የምትታወቅ ሲሆን አሁን ላይ የሀገር ዉስጥ የቡና ፍላጎት መጠን በመጨመሩ ወደ... read more
አስተግባሪ ያጣው የትንባሆ ቁጥጥር
👉
https://youtu.be/e-KBshnYaRk
read more
እንደሃገር ካለፈ ታሪክ በመማር እና በመነጋገር የዜጎችን የመብት ጥያቄዎች መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ
በወርሃ የካቲት 1966 ዓ/ም በተቀሰቀሰው የኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ከተነሱ ዋነኛ ጥያቄዎች አንዱ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንደሆነ ይታወቃል። ይህንኑ ራስን... read more
በበጀት ዓመቱ ከ1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የቡና ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው ተባለ
ኅዳር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ አመት እንደ ሀገር ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የቡና ምርት ለመሰብሰብ በትኩረት... read more
ምላሽ ይስጡ