መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ዩናይትድ ቀደም ሲል ባርሴሎና ይጠቀምበት የነበረውን የገቢ ማግኛ መንገድ በመከተል የኦልድ ትራፎርድ ስታዲየሙን የሜዳ ሳር ለደጋፊዎች መሸጥ መጀመሩ ተዘግቧል። ክለቡ 7 ሴንቲሜትር ስፋት ያለውን የኦልድ ትራፎርድ የሜዳ ሳር በብርጭቆ ዕቃ (Turf Cube) ውስጥ አሽጎ በ125 ፓውንድ ለገበያ አቅርቦታል ተብሏል። በታዋቂው የስፖርት ዘጋቢ ፖል ሂርስት እና በታዋቂ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ መሠረት፣ ማንቸስተር ዩናይትድ የባርሴሎናን የካምፕ ኑ አሰራር በመከተል የታዋቂውን ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም የሜዳ ሳር ለአንደኛ ደረጃ የትኬት ባለቤቶች (Season-ticket holders) እና ለደጋፊዎች መቸርቸር ጀምሯል። ክለቡ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦልድ ትራፎርድን ሙሉ የሜዳ ሳር በአዲስ መቀየሩን ተከትሎ፣ በቅርቡ የፋይናንስ ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት እና የ47 ሚሊዮን ፓውንድ ዓመታዊ ከታክስ በፊት ኪሳራ ባጋጠመበት ወቅት ይህንን ማድረጉ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ መንገዶችን ለመፈለግ በሚያደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ተገልጿል። ክለቡ ጥቂት ግራም ሳር በ125 ፓውንድ ከፍተኛ ዋጋ መሸጡን ተከትሎ ጉዳዩ በእግር ኳስ ደጋፊዎችና በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ እና የቀልድ ርዕስ ሆኗል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ሞሀመድ ሳላህ ዘንድሮ ከሻምፒዮንስ ሊጉ ይበልጥ ፕሪሚየር ሊጉን ማሳካት እፈልጋለሁ ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል
ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ግብፃዊው ኮኮብ ፍርኦኑ ሞ ሳላህ ዘንድሮ አይቀመሴ አቋም ላይ ነው የሚገኘው። በወርሀ ታኅሳስ ብቻ በ7... read more
ከአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን የፊታችን ሃምሌ 22 እንደሚካሄድ ተገለፀ
ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ESCFE ይህ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌዴሬሽን በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአንድ... read more
ፊዮሬንቲና ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረቡ ተገለጸ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጣሊያኑ ክለብ ፊዮሬንቲና የ25 ዓመቱን የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም... read more
አርሰናል በሪዮ ንጎሞሀ ላይ የቅርብ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጥተዋል
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቲምቶክ ጸሐፊ ጋዜጠኛ አለን ኒክሰን እንዲሁም ሪለክተንት ኒኮ ያወጡት መረጃ፣ መድፈኞቹ ይህንን ተስፈኛ ወጣት ኮከብ... read more
የአርሰናል የተከላይ መስመር ተጫዋች የሆነው ዩሪየን ቲምበር ጉልበቱ ላይ የቀዶ ጥገና እንደሚያከናውን ተገልጿል
ተያይዞም ሌላው የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ዊሊያም ሳሊባ በበኩሉ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረጉለት ክለቡ አሳውቋል።
ዩሪየን ቲምበር ያለፉትን ወራቶች ከነጉዳቱ ሲጫወት... read more
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አንጋፋ ተጫዋች ጋሪ ኔቪል የቀድሞ የቡድን አጋሩ እና የአሁኑ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ላይ ከባድ ትችት ሰንዝሯል
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ እና የስፖርት ተንታኝ ጋሪ ኔቪል በፉልሃም ጨዋታ ወቅት በማይክል... read more
ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከለንደን ማራቶን ውጪ መሆኑን አሳወቀ
በአለም አትሌቲክስ ኤሊቴ ፕላቲኒየም ደረጃ ከተሰጣቸው የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የለንደን ማራቶን እንደሆነ ይታወቃል። ዘንድሮ ከ55 ሺሕ በላይ ሯጮች ይሳተፉበታል... read more
የሩበን አሞሪም የመጀመሪያው ፈራሚ ዲዬጎ ሊዮን እንደሚሆን ይገመታል
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ17 አመቱ ፓራጓዊ ዲዬጎ ሊዮን ክለቡን በመልቀቅ ሴሮ ፖርቴኖን በመልቀቅ ፊርማውን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለማስቀመጥ ወደ... read more
ያኒክ ሲነር ዌምብልደንን አሸነፈ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በAll england club አዘጋጅነት ሲከናወን የቆየው ተወዳጁ እና ትልቁ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ዌምብልደን ትላንት ሲጠነመቀቅ በወንዶች... read more
የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዳሰሳ
በየአመቱ ከሚከናወኑ እና የክለቦች ፉክክር ከሚደምቅበት እንዲሁም በአውሮፓ ውስጥ ሀያሉ ክለብ ለመባል የሚደረግ የክለቦች ትንቅንቅ በተለያዩ የአውሮፓ ግዙፍ ስቴዲየሞች በባውዛ... read more
ምላሽ ይስጡ