መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ሴቶች በግጭት ወቅት ጉዳት እንዳይደርስባቸው የመጠበቅና በሰላምና ደህንነት ዙሪያ ያላቸውን ሚና የማጉላት ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (NEWA) “ብሔራዊ የሴቶች፣ ሰላምና ደህንነት ፎረም” በሚል ባዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጿል። የቅንጅቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገብረመድህን የሴቶች ሰላምና ደህንነት አጀንዳ በሴቶች የሰላም ድርድር ተሳትፎ ብቻ ሳይወሰን ከግጭት በመከላከል፣ በጥበቃ እና በአካቶ መተግበር አለበት ብለዋል። በተለይ ግጭት በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ሴቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ተናግረው፤ ከግጭቱ በኋላ ለማገገም የሚያስችሏቸው መሠረተ ልማቶችና አገልግሎቶች መጠናከር እንዳለባቸውም አብራርተዋል። በውሳኔ ሰጪ ሂደቶች የሴቶች ዝቅተኛ ተሳትፎ በግጭት ወቅት የበለጠ ሊጎለብቱ የሚችል መሆኑን ጠቅሰው፤ በማኅበረሰብ ደረጃ ሴቶች እያደረጉት ያለው የሰላም እንቅስቃሴ፣ የሴቶች ድርጅቶች የሚያከናውኑት የጥበቃና የድጋፍ ሥራ እንዲሁም ለግጭት ተጎጂዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ታውቀውና ተመዝግበው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል። በተለይም በዚህ ላይ የሚሠሩ የሴቶች ማኅበራት ጥረቶችንም መደገፍ፣ እነዚህን ጥረቶች ማስተባበር እና ግጭትን ከመከላከል ጀምሮ በሰላም ማስፈን ሂደት ሴቶች የሚኖራቸውን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ አመላክተዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
🚨 ሰበር ዜና፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ከሞሮኮ ወደ ስፔን ሴኡታ ዘለቁ — አውሮፓ በሌላ አዲስ የድንበር ቀውስ ተናጋች!
ሐምሌ 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሕይወታቸውን በምንም ነገር ላይ ለመወራረድ የቆረጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ከሞሮኮ የባሕር ዳርቻ ተነስተው በዋና ወደ... read more
የአባይ ግድብ ምረቃ እና ዓለም አቀፍ ዘገባዎች
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ በመጪው የመስከረም ወር የአባይ ወንዝ ታላቁን ህዳሴ ግድብ (GERD) ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ስትሆን፣ ይህ ሜጋ... read more
የኩላሊት ታማሚዎችን እንግልት የሚቀንስና አጭበርባሪዎችን ለመከላከል የሚያስችል የድጋፍ መስጪያ የአጭር የጽሁፍ መቀበያ ቁጥር መዘጋጀቱ ተገለጸ
ነሐሴ 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሁኑ ሰዓት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አዳጊ ሀገር በከፍተኛ ሁኔታ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች እንዳሉ... read more
ከ20 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት የቱሪዝም ሳምንት ሊካሄድ ነው
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን፣ ገበያዎችን፣ ንግዶችን፣ ባለሀብቶችን፣ ቴክኖሎጂን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን ለማስተዋወቅ የሚያስችል ዓመታዊ... read more
ጡረታ የወጡ አረጋውያን ተደራጅተው በሙያቸው አመቺ በሆነ የስራ መስክ እንዲሰማሩ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እድሜያቸው ከ60 አመት በላይ የሆኑና ጡረታ የወጡ ነገር ግን የመስራት አቅም ያላቸው አረጋውያን በሙያቸው ተሰማርተው... read more
ኮንዶም ላይ ተጥሎ የነበረው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲነሳ መወሰኑ ተገለጸ
ኅዳር 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሃገራችን የኮንዶም አቅርቦት እጥረት መኖሩን ተከትሎ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት እየጨመረ እንዳለ ይገለጻል።
የኤች አይ... read more
💻 በላፕቶፕ እና ስልክ ቻርጀር ገመዶች ላይ የሚገኘው ያበጠው ሲሊንደር ሚስጥር፤ ለጌጥ ወይስ ለደህንነት? 🔌
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በላፕቶፕ እና ስልክ ቻርጀር ገመዶች ላይ ወደ ጫፉ አካባቢ ያበጠ ክብ ሲሊንደር ነገር አስተውለው ያውቃሉ?... read more
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የብስክሌት ትራንስፖርትን ለማስፋፋት የአሰራር ደንብ እንዲፀድቅ ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የብስክሌት ትራንስፖርት ለማስፋፋት የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ... read more
በቢንቢ ፣ በትንኝ፣ በወባ ትንኝና በመሰል ነገሮች የቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር መተላለፍያ መንገዶች እንደሆኑ የጤና ባለሙያዎች እየተናገሩ ይግኛሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ Hemorrhagic Fever (ሄሞራጂክ ፊቨር) መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል እኛም ይህ... read more
የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭት ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ሊስፋፋ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭትን ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ለማስፋፋት ዝግጅት... read more
ምላሽ ይስጡ