መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጪው መስከረም 16 ቀን 2019 የሚከበረው የደመራ እንዲሁም የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ቢሮው የሰላምና ፀጥታ ሥራውን እየሠራ እንደሚገኝ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሥሐ ጥበቡ፤ በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አስቀድሞ ከማህበረሰቡ ጋር በቂ ውይይት መደረጉን የተናገሩት አቶ ፍሥሐ፤ የኢትዮጵያን ገጽታ ሊገነባ በሚችል ደረጃ በዓሉ እንዲከበር ከፀጥታ አኳያ ተገቢው ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል። ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የሃይማኖት አባቶች በሚያስቀምጡት ሥርዓት መሠረት በዓሉ እንዲከበር ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ አሳስበዋል። ከፀጥታ ጎን ለጎን በየሰፈሩ በሚካሄደው የደመራ ማብራት ሥርዓት ላይ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይከሰት ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በዚህ በዓል ላይ በርካታ የሀገር ውስጥ እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ቱሪስቶች የሚገኙ በመሆኑ፣ የፀጥታ አካላት አስቀድመው ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ የፍተሻ እና የቅኝት ሥራዎችን እንደሚያደርጉ አመላክተዋል። መስቀል እንዲሁም በቀጣይ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የመሰረተ- ልማት መኖር ለዜጎች ከሚያመጣው የኢኮኖሚ እድገት ባለፈ የዜጎችን አኗናር ለማዘመን ይረዳል ተባለ
መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ይህ የተነገረው 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ... read more
የኃይል ሥርቆት በፈጸሙ 111 ደንበኞች ላይ ክስ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና... read more
የበርገር ኪንግ ሰራተኛ ለ27 አመታት ባለመቅረቱ ከ400 ሺህ ዶላር በላይ የገንዘብ እርዳታ ተሰጠው
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ላስ ቬጋስ ውስጥ በርገር ኪንግ ውስጥ ለ27 አመታት አንድም ቀን ሳይቀር የሰራ አንድ ሰራተኛ በሰራው ታማኝነት... read more
ወረቀትን ከሣር ማምረት ተጀመረ
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ወረቀትን ለማምረት ዛፎችን መቁረጥን የሚተካ አዲስ የዘላቂነት ፈጠራ ይፋ ተደርጓል። ተመራማሪዎች ሣርን ዋና ጥሬ እቃ... read more
ዝምተኛው ማዕበል በሚል የሚጠራው የፀረ- ተዋሲያን በጀርሞች መለመድ በሰዎች ላይ ያስከተለው ውስብስብ ችግር 👉
https://youtu.be/LRBdqWz6Eio
read more
ምክር ቤቱ 582 ቢሊየን ብር ተጨማሪ የፌደራል መንግስት በጀት አድርጎ አፀደቀ
ኅዳር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባው... read more
23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመጣው ከቡናማ ላሞች ነው ብለው ያምናሉ ተባለ
ሐምሌ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመነጨው ከቡናማ ቀለም ካላቸው ላሞች ነው ብለው እንደሚያምኑ ተገለጸ። ይህ መረጃ... read more
በ2025 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የአለም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ በ29 በመቶ ጨምሯል ተባለ
ሚያዚያ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና እና አሜሪካ መካከል የተስተዋለው ቀጣይነት ያለው ቀረጥ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ ላይ የተወሰነ ተጽዕኖ... read more
የአድዋ ገድልን በዲፕሎማሲያዊው መስክ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላት እውቅና የጨመረው እና የአውሮፓ ሀያላን ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር በእኩልነት መንፈስ መደራደራቸውን የቀጠሉት ከአድዋ ማግስት መሆኑ... read more
አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የባህር ላይ እገዳ እና የቻይና ጠንከር ያለ ምላሽ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ ከኢራን ጋር ያደረገችው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ በኢራን ወደቦች ላይ ጥብቅ የባህር ላይ... read more
ምላሽ ይስጡ