መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በጥምረት ስም ወደ ተጨማሪ ግጭት የሚያመሩ ድርጊቶችን ለሀገር አንድነትና ሰላም ሲባል ማስቆም እንደሚገባ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ሃሳባቸውን ያሳፈሩ ፓርቲዎች ተናግረዋል። ምርጫ እና ምክክር ያደረገችው ኢትዮጵያ ሰላምና አንድነቷ ተጠብቆ ሊቆይ ይገባል ሲሉ የጉሙዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር መኮንን ጉላሳ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። ዛሬም ሆነ ወደፊት እንደ ሀገር የሚጠቅመው በውይይትና በሀገራዊ አንድነት መስራት ብቻ እንደሆነ ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። ሀገር በትጥቅ ትግል የምትለወጥበትና የምታተርፍበት ጊዜ አልፏል ያሉ ሲሆን፣ የጥምረት ሃይሎችን መንግስት ከህዝብ ጋር ሆኖ መቆጣጠርና ሰላምና የሀገርን አንድነት አስጠብቆ መዝለቅ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የጥምረቱ አካል ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያ የፓርቲያቸውን ስም ሲያነሱ የቆዩም እንዳሉ የጠቀሱት ስራ አስፈጻሚው ፓርቲያቸው ከመሰል እንቅስቃሴዎች የራቀ እና በህጋዊ መንገድ ተወዳድሮ ስልጣን አግኝቶ ህዝብን እያገለገለ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ይሁንና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ አንዳንድ ወጣቶችን አባብሎ የጥምረቱ አካል የማድረግ እንቅስቃሴዎች ሳይኖሩ እንዳልቀሩ ግምታቸዉን ገልጸዋል። ይከናወናል የተባለው ጥምረት ከገሃዱ እውነታ ጋር ሲታይ አንዳንዶቹ ፓርቲዎች እሳቤና የትግል ሃሳብ እርስ በእርሱ የሚቃረን መሆኑን ጠቁመዋል። አክለዉም የህዝብ ሰላም እንዳይነካ ሌሎች ፓርቲዎች ከፌደራል መንግስት ጎን ቆመው ሊሰሩ እንደሚገባም ስራ አስፈጻሚው አስገንዝበዋል። ህዝብ እንዲህ ባለው ያልተረጋገጠና መልክ ያልያዘ ትብብር ምክንያት ሊወሰድና የሃሳቡም ተቀባይ መሆን የለበትም ሲሉ ሃሳባቸውን የገለጹት ደግሞ የአፋር ሕዝብ ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አሕፍዲፓ) ስራ አስፈጻሚ አባል ሱመያ መሃመድ ናቸው። አክለዉም መንግስትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ሀገራዊ አንድነት ላይ ብቻ መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል። የታጣቂ ሃይሎችና መሰል አጎራባች ሃይሎች ጥምረት ዘለቄታዊም ህጋዊም መሰረት አለው ብለው እንደማያምኑም ጠቅሰዋል። በአፋር ክልል በኩል የጥምረቱ አካል ሆነው የቀረቡ ፓርቲዎች ስለመኖራቸው መረጃው እንደሌላቸውም አክለው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገራዊ ምክክር አድርጎ ሁለንተናዊ መፍትሄ በሚሽትበት ማግስት እንዲህ ያሉ አዋኪ ጥምረቶችን በመስማት እንዳይረበሽ መንግስትና ሀገራዊ አንድነት ላይ የሚሰሩ ፓርቲዎች ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ፓርቲዎች አመላክተዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
እንደ ሃገር የመሬት ሚኒስቴር ቢቋቋም የሚል ምክር ሃሳብ ቀረበ
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እሸቱ ተመስገን(ዶ/ር) እንደ ሀገር የመሬት... read more
“ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን እኩል የመጠቀም መብት አላት!”
👉
https://youtu.be/9k5xPB890Bg
read more
በአማራ ክልል በተያዘው መጋቢት ወር መጨረሻ የአጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚጀመር ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጋቢት ወር መጨረሻ ቀናት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
በመሆኑም የወረዳ... read more
ኮሚሽኑ ሕፃናትን የሚመለከቱ አጀንዳዎችን በቀጥታ በስም ባይጠቅስም በአጀንዳዎቹ ውስጥ ማካተቱን ገልጿል
ሰኔ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ውይይትና ምክክር ሲያደርግባቸው ከቆየባቸው አጀንዳዎች መካከል የሕፃናት ጉዳይ እንደሚገኝበት ቀደም ሲል... read more
ተደራራቢ የአካል ጉዳት ያለባቸውንና ዕድሜያቸው ለሥራ ሳይደርስ የቤተሰብ አስተዳዳሪ የሆኑትን ጨምሮ ለ94 ሺህ ዜጎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 06 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ)በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት እና ሥራ ፕሮጀክት አማካኝነት ተደራራቢ የአካል ጉዳት ያለባቸውን፣ በጽኑ ሕመም ምክንያት አልጋ ላይ... read more
በበጀት ዓመቱ 5 ወራት ከ47 ሺህ በላይ አዲስ ነጋዴዎች ወደ ንግድ ስርዓቱ ሲገቡ፤ ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከንግድ ስርዓቱ መውጣታቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሐምሌ ወር ጀምሮ በከተማዋ 15 ሺህ 99 ነጋዴዎች ከንግድ ስርዓቱ መውጣታቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ... read more
ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ሊደረግ ነው።
👉በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ... read more
በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ይቆማል የሚል ግምት እንደሌለ ተገለጸ
ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ላይ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ይቆማል የሚል ግምት እንደሌለ የገለጹት የዘርፉ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
መንቀጥቀጡ... read more
በኢትዮጵያ የአንበሳ ዝርያ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ
ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተለያየ ጊዜ በተደረገ ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የአንበሶች ቁጥር መቀነስ በዋነኝነት የመኖሪያ ቦታቸው መጥፋት እንደሆነ... read more
በኢራቅ የጠቅላይ ሚኒስትር አል-ሱዳኒ ጥምረት በፓርላማ ምርጫ አሸነፈ
ሕዳር 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሺዓ አል-ሱዳኒ ጥምር ፓርቲ በሀገሪቱ በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን... read more
ምላሽ ይስጡ