መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “ቦረዳ ወረዳ” የድንጋይ ከሰል ማምረትና ማጠብ ሥራ ላይ የተሰማራው ዮ ሆልዲንግ፣ አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን እየሠራ መሆኑን የዮ ሆልዲንግ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ መኮንን ዓለሙ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውና በጋምቤላና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በድንጋይ ከሰል ምርት የተሰማራው ዮ ሆልዲንግ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለኃይል ይጠቀሙበት የነበረውን የከሰል ግብዓት ከውጭ በውጭ ምንዛሬ ያስመጡ እንደነበር ተናግረዋል። የዮ ሆልዲንግ የድንጋይ ከሰል ማምረቻና ማጠቢያ አሁን ላይ ወደ 70 በመቶ ለሚሆኑ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርቱን እንደሚያቀርብ አቶ መኮንን ገልጸዋል። ዮ ሆልዲንግ በጋምቤላና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፋብሪካው በቀን ከ400 ቶን በላይ የሚያመርት ሲሆን፣ የማምረት አቅሙም በየዓመቱ እየጨመረ በመሄዱ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን አክለዋል። ፋብሪካው በዓመት ውስጥ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ያላነሰ የድንጋይ ከሰል ምርት የሚያመርት ሲሆን፣ በቀጣይ 2 ተመሳሳይ ፋብሪካዎችን ለመገንባት እንደታቀደና ከኬንያ ጀምሮ ወደ ጎረቤት ሀገራት ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። ዮ ሆልዲንግ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞችን ጨምሮ ከ500 እስከ 700 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል ተብሏል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ከሞት ከተለየ ሰው የሚደረገው የኩላሊት ልገሳ አዋጅ
https://youtu.be/_-03kS7GEa0
read more
ዕድሜያቸው ለትምህርት ደርሶ፣ ትምህርት ያልጀመሩ ዓይነ ስውራን ቁጥር አሁንም ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገሪቱ ከሚገኙ አካል ጉዳተኞች መካከል 11.8 በመቶ ያህሉ ብቻ የትምህርት ዕድል እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ... read more
ቻይና በ110 ቀናት ውስጥ የአለማችን ሰፊውን የውሃ ውስጥ ዋሻ በመገንባት ክብረወሰን አስመዘገበች
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቻይና በ110 ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የአለማችንን እጅግ ሰፊ የውሃ ውስጥ ዋሻ በመገንባት አዲስ ክብረወሰን... read more
በአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ ተደረጉ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል ከዋዜማው ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ... read more
‘’ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሊዮ አስራ አራተኛ በቫቲካን ተቀብለውናል። ውይይታችን በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ለዓለም ሰላም ያለንን የጋራ አቋምም ተወያይተናል። የትምህርት ተደራሽነትን የማስፋት አስፈላጊነትን በተመለከተም የጋራ ስምምነት ይዘናል።’’
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ(ዶ/ር)__
read more
በአሜሪካ ላሞች ላይ የVR መነጽር በማድረግ ጭንቀታቸው እንዲቀንስ እየተደረገ ነው ተባለ
👉መነጸሩ አረንጓዴ ሜዳዎችን እንዲያዩና ብዙ ወተት እንዲያመርቱ ያግዛቸዋል ነው የተባለው
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በሚገኙ አንዳንድ እርሻዎች ላሞች በረት... read more
የአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ለደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለጹ
የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን እየተደረገ ላለው ጥረት ያልተቆጠበ ድጋፋቸውን ማድረግ እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።
የደቡብ ሱዳን... read more
የታማ ጥብቅ ደን በዙሪያው ባሉ አራት ብሄረሰቦች መጠበቁ ከቱሪዝም ጠቀሜታ ባሻገር፣የማህበራዊ ቁርኝትን ይበልጥ ያጠናክራል ተባለ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች አዋሳኝ ያለው የታማ ማህበረሰብ ጠብቅ ደን፣ በዙሪያው ባሉ አራት ብሄረሰቦች እንዲጠበቅ፣ ከአንድ ወር... read more
በትግራይ ክልል የሜርኩሪ መርዛማ ኬሚካል በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ላይ በተደረገ ጥናት በአከባቢው የሜርኩሪ መርዛማ ኬሚካል አጠቃቀም ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ መሆኑን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት በትግራይ ክልል... read more
የአጂባደም የሕክምና ቡድን በአዲስ አበባ የሕክምና መረጃ ቢሮ ከፈተ
ታዋቂው የቱርክ የሕክምና ተቋም አጂባደም በኢትዮጵያ ለሚገኙ ታካሚዎች ቀጥተኛ የመረጃና የድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥበትን አዲስ የሕክምና መረጃ ቢሮ በአዲስ አበባ በይፋ... read more
ምላሽ ይስጡ