መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን (Tigray TV) ላይ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እገዳ መጣሉን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። ባለሥልጣኑ በመግለጫው እንዳስታወሰው፣ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሬቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ባደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነት መሠረት ቀደም ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ መመለሱ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የሰላም ግንባታና የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሚዲያው ወደ ሕገ-መንግሥታዊና ሙያዊ መስመር እንዲመለስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ቴሌቪዥን በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ እና የሙያ ሥነ-ምግባር አክብሮ አገልግሎት መስጠት ሲገባው፣ የሀገርንና የሕዝብን ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ እየተላለፉበት እንደሚገኝ በተደረገው የሚዲያ ይዘት ክትትልና ግምገማ ማረጋገጡን ባለሥልጣኑ ገልጻል። በመሆኑም በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ጣቢያው ላይ ይህንን እገዳ ለመጣል መወሰኑን አስታውቋል። በመጨረሻም ማንኛውም ዲጂታል፣ ብሮድካስትም ሆነ የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያው በሕገ-ወጥ መንገድ የሚያሰራጫቸውን ይዘቶች አሰራጭቶ ወይም አስተጋብቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳስቧል። ይህንን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም ሚዲያ ላይ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች የሚወስድ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ላሚን ያማል ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ተረጋገጠ
ሕዳር 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስፔን ብሔራዊ ቡድን እና የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ በላሚን ያማል ጉዳይ የገቡበት ውዝግብና አለመግባባት እንደቀጠለ... read more
የጥምቀት ኤክስፖ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ ነው ተባለ
ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በመዲናችን አዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚካሄደው ኤክስፖው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ፤ ከሙዚቃ እና ከአልኮል... read more
በጄምስ ዌብ የጠፈር ቴሌስኮፕ ሳንድ ክላውድስ ተገኘ
👉አዲሱ ግኝት በስነ ፈለክ ጥናት አለምን አስደምሟል!
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጄምስ ዌብ የጠፈር ቴሌስኮፕ (JWST) ባደረገው ታሪካዊ ምልከታ፣ በሩቅ... read more
በከተማዋ የሚገኙ ተማሪዎች የሰሯቸውን የሳይንስ እና የፈጠራ ውጤቶች ወደ ተግባር ለመቀየር በትኩረት ይሰራል ተባለ
በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘው የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን፣ በከታማዋ ያሉ ተማሪዎች ስራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ በርካታ የሳይንስ እና የፈጠራ ውጤቶችን ማቅረባቸውን... read more
ኢንተርኔት በብርሃን ፍጥነት፣ ጃፓን የዓለም ሪከርድን ሰበረች!
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የጃፓን ተመራማሪዎች ኢንተርኔት በብርሃን ፍጥነት ማስተላለፍ የሚያስችል አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል። ተመራማሪዎቹ በሴኮንድ 402... read more
በአንድ “እምቢታ” የጣሊያንን ሕግ የቀየረችው የ17 ዓመት ወጣት ድፍረት!
👉ክብርን ለመጠበቅ ደፋሪን ማግባት ግዴታ ነው የተባለችው ፍራንካ ቪዮላ ማን ናት?
ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዛሬ ዓመታት በፊት በጣልያን ሲሲሊ ክልል... read more
ቻይና በግንባታ ቦታ ላይ ግዙፍ በአየር የሚሞላ ጉልላት ዘረጋች
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለንጹህ የከተማ ኑሮ ዘመናዊ እርምጃ የወሰደችው የቻይናዋ ጂናን ከተማ፣ እየተካሄደ ያለውን የግንባታ ቦታ ሙሉ በሙሉ... read more
የሩበን አሞሪም የመጀመሪያው ፈራሚ ዲዬጎ ሊዮን እንደሚሆን ይገመታል
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ17 አመቱ ፓራጓዊ ዲዬጎ ሊዮን ክለቡን በመልቀቅ ሴሮ ፖርቴኖን በመልቀቅ ፊርማውን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለማስቀመጥ ወደ... read more
አፍሪካ ሆልዲንግ ቢዝነስ ግሩፕ ሞዴል ሀሴት ደረጀን የ“GODU Housing and smart real estate” ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ
መስከረም 21 ቀን 2019 (መናኸሪያ ሬዲዮ) — “የተትረፈረፈ ባለጸግነትን ለትውልድ እናወርሳለን” በሚል መሪ ቃል ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው አፍሪካ... read more
በዓይኖቹ ውስጥ ኮከቦችን ያቀፈው ምስኪኑ ጉጉት
ሰኔ 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በካሊፎርኒያ ግዛት በደረሰበት የድንገተኛ አደጋ ምክንያት በቋሚነት ለዓይነ ስውርነት የተዳረገው "ዙስ" (Zeus) የተባለው የጉጉት ዝርያ... read more
ምላሽ ይስጡ