መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ ዌስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ (Addis West Substation) ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አንዋር አብራር ገልጸዋል። በዚህ ድንገተኛ ብልሽት ሳቢያ በእህል በረንዳ፣ አውቶብስ ተራ፣ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ ገነሜ ትምህርት ቤት፣ አማኑኤል ቤተክርስትያን ፊትለፊት፣ አዲሱ ሚካኤል እና አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል። በተጨማሪም በመሳለሚያ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ኳስ ሜዳ፣ ግሩም ሆስፒታል፣ ታይዋን ገበያ ማዕከል እና አካባቢው እንዲሁም በአማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ሕንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ እና አካባቢው የኃይል መቋረጡ አጋጥሟል። በተመሳሳይ ሁኔታ በፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምፕሬሄንሲቭ ትምህርት ቤት፣ ኮልፌ 18 ማዞሪያ፣ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እና አካባቢው፣ በኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ (በከፊል)፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን እና አካባቢው አገልግሎቱ ተቋርጦ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስጅድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት እና አካባቢው፣ በሆላንድ ኤምባሲ፣ የሺ ደበሌ፣ ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ ቻይና ኤምባሲ፣ አውጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አባ ጅፋር መስጅድ እና አካባቢው እንዲሁም በወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ የቀድሞው ራሺያ ካምፕ፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ አውጉስታ፣ ወይብላ ማርያም፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብ እና አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ባለሙያዎች ብልሽቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማስተካከል አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ በትኩረት እየሠሩ ይገኛሉ። ተቋሙ ያጋጠመውን ድንገተኛ የኃይል መቋረጥ በማስመልከት ወቅታዊ መረጃዎችን በቀጣይ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ የሚያሳውቅ ሲሆን፣ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቹ በትዕግሥት እንዲጠባበቁ በአክብሮት ጠይቋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ኢትዮጵያ ከነበረችበት የእዳ ጥገኝነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉዋላዊነት መቀየር የቻለችበት ሁኔታ እንዳለ ተገለጸ
መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በዛሬው ዕለት 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ... read more
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገቡ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ በደረሱበት ወቅት በፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር... read more
“ብቻሽን ልትቀሪ ትችያለሽ!” 👉 ዶናልድ ትራምፕ
ትራምፕ ለእስራኤል ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ተሰማ
ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጠንከር ያለ... read more
ጊፍት ሪል እስቴት 2 ሺሕ ቤቶችን ለመሸጥ የሚያስችለውን የሽያጭ መርሃ ግብር በይፋ አስጀመረ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጊፍት ሪል እስቴት በለገሀር ሳይቱ 2 ሺሕ ቤቶችን ለሽያጭ ማቅረቡን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ከ2ሺህ ቤቶቹ... read more
አጀንዳቸውን ለሚያቀርብ የታጠቁ ሃይሎች ኮሚሽኑ ሙሉ ዋስትናን ማቅረብ እንደሚችል ተገለጸ
ጥቅምት 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለታጠቁ ሃይሎች በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም አብዛኛዎቹ ጥሪውን እንዳልተቀበሉ ኮሚሽኑ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ... read more
81 በመቶ የሚሆኑ የንግድ ባንክ ደንበኞች የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ዲጂታል ፋይናንስን ለማስፋፋት ካቀደው እቅድ ቀድሞ ማሳካት መቻሉን አመላክቷል፡፡
የዲጂታል ስርዓቱ መስፋፋት በአገልግሎት አሰጣጥ ሒደት... read more
42ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች
🔰የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 42ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1.በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ የአደጋ... read more
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የለም ተባለ
ኅዳር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) “ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል” በሚል በተለያዩ የማህበራዊ... read more
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ አልተጠቀመም ሲሉ የምክር ቤት አባላት ገለፁ
በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ3 ዓመት የስራ... read more
ምላሽ ይስጡ