መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ ዌስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ (Addis West Substation) ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አንዋር አብራር ገልጸዋል። በዚህ ድንገተኛ ብልሽት ሳቢያ በእህል በረንዳ፣ አውቶብስ ተራ፣ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ ገነሜ ትምህርት ቤት፣ አማኑኤል ቤተክርስትያን ፊትለፊት፣ አዲሱ ሚካኤል እና አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል። በተጨማሪም በመሳለሚያ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ኳስ ሜዳ፣ ግሩም ሆስፒታል፣ ታይዋን ገበያ ማዕከል እና አካባቢው እንዲሁም በአማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ሕንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ እና አካባቢው የኃይል መቋረጡ አጋጥሟል። በተመሳሳይ ሁኔታ በፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምፕሬሄንሲቭ ትምህርት ቤት፣ ኮልፌ 18 ማዞሪያ፣ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እና አካባቢው፣ በኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ (በከፊል)፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን እና አካባቢው አገልግሎቱ ተቋርጦ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስጅድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት እና አካባቢው፣ በሆላንድ ኤምባሲ፣ የሺ ደበሌ፣ ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ ቻይና ኤምባሲ፣ አውጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አባ ጅፋር መስጅድ እና አካባቢው እንዲሁም በወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ የቀድሞው ራሺያ ካምፕ፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ አውጉስታ፣ ወይብላ ማርያም፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብ እና አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ባለሙያዎች ብልሽቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማስተካከል አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ በትኩረት እየሠሩ ይገኛሉ። ተቋሙ ያጋጠመውን ድንገተኛ የኃይል መቋረጥ በማስመልከት ወቅታዊ መረጃዎችን በቀጣይ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ የሚያሳውቅ ሲሆን፣ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቹ በትዕግሥት እንዲጠባበቁ በአክብሮት ጠይቋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በኢትዮጵያ በቀን ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሊትር በላይ ቤንዚን እና ከ8 ሚሊየን ሊትር በላይ ናፍጣ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ተገለጸ
ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በየቀኑ ከ3 ሚሊየን ሊትር በላይ የቤንዚን ፍላጎት መኖሩን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሀገሪቱ የነዳጅ... read more
የብዝሃ ህይወት ሃብታችን ምን ፈየደልን?
👉
https://youtu.be/JeCarB-_2Jg
read more
የወንድ ብብት ላብ በሴቶች ሆርሞኖች እና ስሜት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አዲስ ጥናት አመለከተ
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርቡ በሳይንሳዊ ዘርፍ የተደረገ አንድ ጥናት አስገራሚ ግኝት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ ከወንዶች ብብት ላብ ውስጥ... read more
ሀማስ በአሜሪካ ለተደገፈው የጋዛ የተኩስ አቁም እቅድ ‘አዎንታዊ ምላሽ’ ሰጠ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሀማስ በአሜሪካ ለተደገፈው የጋዛ የተኩስ አቁም ሀሳብ ለአሸማጋዮች "አዎንታዊ ምላሽ" መስጠቱን አስታውቋል፤ ይህም ለ21 ወራት... read more
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ታላቅ ፍፃሜ፤ አርሰናል ከፓሪስ ሴንት ጄርሜን
ግንቦት 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በየዓመቱ ከሚከናወኑ እና የክለቦች ፉክክር ከሚደምቅበት እንዲሁም በአውሮፓ ውስጥ ሀያሉ ክለብ ለመባል የሚደረግ የክለቦች ትንቅንቅ... read more
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት 19ኙን ቅርጫፎች ዲጂታላይዝ ማድረጉን አስታወቀ
ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የተለያዩ ተቋማት የአሰራር ስርዓታቸውን ወደ ዲጂታል እየቀየሩ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎትም የመድሃኒት አቅርቦትን ለማሻሻል... read more
ቤተሰብን ለመደገፍ በሚሰራው ስራ የመዋቅርና የፖሊሲ ማዕቀፍ ችግር መኖሩ ተገለጸ
ቤተሰብን በመደገፍ ስራ ውስጥ የመዋቅርና የፖሊሲ ማዕቀፍ ችግር መኖሩን ለጣቢያችን የገለጸው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።
ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቤተሰብ ህጎችን... read more
ከሞት ከተለየ ሰው የሚደረገው የኩላሊት ልገሳ አዋጅ
https://youtu.be/_-03kS7GEa0
read more
በምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ተሰየሙ
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ27ኛ መደበኛ ስብሰባው በምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮችን ሰይሟል፡፡
አፈ ጉባኤ... read more
የከተማ አውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽት 4 ሰዓት መራዘሙ ተገለጸ
ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በእጅጉ እየፈተኑ ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል አንዱ የትራንስፖርት እጥረት መሆኑ ይታወቃል፡፡ መንግስት የትራንስፖርት... read more
ምላሽ ይስጡ