መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ 5 ነባር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ቋንቋ የመጥፋት አደጋ ላይ በመሆኑ የመንግሥትን ትኩረት እንደሚሻ የአካባቢው ተወላጅና ፖለቲከኛው ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። እያንዳንዱ አርሶ አደር ቢያንስ አንድ ዲግሪ ያለው ልጅ ያለው መሆኑ የቦሮ ሺናሻን ማኅበረሰብ ልዩ ያደርገዋል የሚሉት ዶክተር መብራቱ፣ የብሔረሰቡ ምሁራን ቋንቋውን ለማስቀጠል የማስተዋወቅና የምርምር ሥራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። መንግሥት ለብሔር ብሔረሰቦች መብት፣ እኩልነትና ባህላቸውን ለማስተዋወቅ የሚያደርገው ድጋፍ አበረታች ቢሆንም፣ ባህል፣ ወግና ቋንቋቸው የመጥፋት አደጋ ለተጋረጠባቸው ብሔረሰቦች ልዩ ትኩረት በመስጠት ጥናት ማድረግ እንደሚገባው ፖለቲከኛው ገልጸዋል። በተለይ ከብሔረሰቡና ከክልሉ ውጪ ለሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች ቋንቋውን በማስተላለፍና በማስቀጠል ረገድ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ትኩረት እንደሚሻ ዶክተር መብራቱ ተናግረዋል። እንደ ማኅበረሰብ አናሳ ከሚባሉት መካከል የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ተጠቃሽ ቢሆንም አናሳነቱ በቁጥር እንጂ በባህል ሀብት አይደለም የሚሉት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የባህልና ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ኃላፊ አቶ በላይ አፋ ናቸው። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አሁን ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የብሔረሰቡን ቋንቋ የመጠበቅና የማስተዋወቅ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባው ገልጸዋል። ብሔር ብሔረሰቦች በመዲናዋ ባህላቸውንና የዘመን መለወጫ ሥርዓታቸውን እንዲያከብሩ ከመፍቀድና ከማገዝ በተጨማሪ ቋንቋና ባህላቸው የመጥፋት አደጋ ለተጋረጠባቸው በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ በመሥራት መጠበቅ እንደሚገባም ተመልክቷል። የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ከመስከረም 11 እስከ መስከረም 18 ባሉት ቀናት እየተከበረ ይውላል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ቻይና ሰው ሰራሽ የሰው ልጅ ጽንስን(ሽል) ወደ ጠፈር ጣቢያዋ በመላክ ታሪካዊ ሙከራ አደረገች
ግንቦት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰውን ልጅ ወደ ማርስ እና ጨረቃ ለማጓጓዝ እንዲሁም በህዋ ላይ በቋሚነት ለማስፈር ለሚደረገው ጥረት ትልቅ... read more
ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ተገለጸ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢ/ር ዋሊድ ቢን አብዱልከሪም ኤልኬሬጂ ጋር በጽ/ቤታቸው... read more
ድምፃዊ ዓምደ-ገብርኤል አድማሱ አዲሱን “ወሄነት” የሚል መጠሪያ ያለውን ሶስተኛ አልበሙን የፊታችን እሁድ ለሙዚቃ አፍቃርያን ሊያቀርብ ነው
ሰኔ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከአሁን በፊት "ሰበበር ኤነዌ" እና "ሟን ያትገፍሬ" በተሰኙት ሁለት የጉራጌኛ አልበሞቹ እንዲሁም በተለየ መልኩ "እያ ኧረሙድን... read more
የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ባለንብረቶች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆናቸውን ካላረጋገጡ መስራት እንደማይችሉ ተገለጸ
ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከዚህ ቀደም ባለንብረቶች ከተለያዩ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቀድመው ይጠቀሙበት በነበረው የሰሌዳ ቁጥር ይሰሩ... read more
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እየተከተለው ያለው ጠበቅ ያለ አሰራር ፓርቲዎችን ለቀጣዩ ምርጫ የሚያጠናክር ነው ተባለ
እግዱ የተጣለባቸው ፓርቲዎች ግን ውሳኔው ተገቢነት እና ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን እንደ አገር በቅርቡ ከሚጠብቋቸው ትልልቅ ብሔራዊ ጉዳዮች መካከል... read more
በአፍርካም ሆነ እንደ ኢትዮጵያ ስደትን ለመቀነስ እና ተመላሾችን ለማቋቋም ጠንካራ የፋይናስ አማራጭ መዘርጋት እንደሚገባ ተጠቆመ
ስደትን ለማስቆምና ከስደት ተመላሾችን ለማቋቋም አጋዥ አካላት እንደሚያስፈልጉ የካርቱም ፕሮሰስ በተሰኘ በስደትና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ የሚሰራ ተቋም ባዘጋጀዉ መድረክ ላይ... read more
ፊንላንድ የሐሰት ዜናን መለየትን ከ6 ዓመት ጀምሮ ማስተማር ጀመረች
👉በትምህርት ስርዓቱ አካታለች ነው የተባለው።
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሰፊው የሐሰት መረጃ መስፋፋት በፈጠረው የዲጂታል ዘመን፣ ፊንላንድ የሐሰት መረጃዎችንና... read more
ኮካ ኮላ የትራምፕን ግፊት ተከትሎ አዲስ ንጹህ ግብአት ያለው መጠጥ አስታወቀ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ትልቅ ድልን አከበረ። የኮካ ኮላ ኩባንያ ከሸንኮራ አገዳ የተሰራ አዲስ መጠጥ ለመልቀቅ... read more
ቆሻሻ ፕላስቲክን ከኮንክሪት የጠነከረ ጡብ ያደረገችው የኬንያዊት መሐንዲስ
ጥቅምት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ29 ዓመቷ ኬንያዊት የቁሳቁስ መሐንዲስ ንዛምቢ ማቴ ከስድስት ዓመታት በፊት በአካባቢ ላይ የፕላስቲክ ብክለትን ለመዋጋት ባላት... read more
ኢትዮጵያ የተቀቀሉ የሥጋ ምርቶችን ወደ ቻይና መላክ ልትጀምር መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የተቀቀሉ የሥጋ ምርቶች እና ተረፈ ምርቶችን ለቻይና ገበያ ልታቀርብ መሆኑን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የእንስሳት... read more
ምላሽ ይስጡ