መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገሪቱ ከሚገኙ አካል ጉዳተኞች መካከል 11.8 በመቶ ያህሉ ብቻ የትምህርት ዕድል እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማኅበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብሬ ተሾመ ተናግረዋል። የትምህርት ዕድል ያላገኙ ሕፃናትና አካል ጉዳተኞች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነና ሽፋኑ አሁንም ዝቅተኛ መሆኑን ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩም ገልጸዋል። ወላጆች አካል ጉዳተኛ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ ከመላክ አንጻር ክፍተት እንዳለባቸው የተናገሩት ኃላፊው፤ ወላጆች ይህንን ችግራቸውን በመቅረፍ ልጆቻቸውን የማስተማር ቀዳሚ ኃላፊነት እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም ብለዋል። የትምህርት ዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም በሚያካሂዱት የቅኝትና የቁጥጥር ሥራ ወቅት፤ በየአካባቢው ካሉ አካል ጉዳተኞች ምን ያህሉ ትምህርት ቤት እንደገቡ ሊከታተሉና አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከአማራ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር ያሳተማቸውን የብሬል መጻሕፍት ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ተደራሽ ቢያደርግም በቂ እንዳልሆነ የሚናገሩት አቶ ገብሬ፤ የማኅበሩ ግዴታ መንግሥት ይህንን እንዲያሟላ መጠየቅ ቢሆንም፣ አንዳንድ የመንግሥት አካላት ሳይቀሩ ማኅበሩ እንዲያሟላ ሲጠይቁ ይስተዋላል ብለዋል። የትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት ግብዓቶችን በሚፈለገው ልክ ማቅረብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የአካል ጉዳተኞችና የመምህራን ማኅበራትን ጨምሮ ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት፣ አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ዜጋ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የ12 ዓመቷ ታዳጊ የፈጠራ ስራ የዓለምን ትኩረት ሳበ፤ ለትምህርት ቤቶች የሚሆን 11.5 ሚሊዮን ዶላር በጀትም አስገኘ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በትምህርት ቤቶች ውስጥ የአየር ጥራትን ለማሻሻልና የአየር ወለድ ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ የሚረዳ ዝቅተኛ ወጪ የሚጠይቅ የአየር... read more
ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሹመዋል
ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ለአንድ ዓመት የስራ ዘመን በኃላፊነት እንደሚቆዩም ተገልጿል።
ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ... read more
ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመር በመውደቁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኃይል አቅርቦት ተቋረጠ
ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከመንዲ ወደ ጊዳሚና እና አሶሳ የተዘረጋው የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ትናንት ማታ ሁለት ሰዓት ሰዓት... read more
በአዲስ አበባ ከተማ የእብድ ዉሻ በሽታ የተገኘባቸዉን ዉሾች የማስወገዱ ስራ በመደኛ ሁኔታ መቀጠሉ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ የሺዳኛ በላይሁን የእብድ... read more
ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦችን እንዳስወገደ የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ
ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ 6 ሚሊየን 44ሺህ 402 ብር የሚያወጣ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦች ናቸው... read more
የዓለም ኃያላን በንፅፅር፡ ቻይና ወይስ ዩኤስ? (በጀት፣ አውሮፕላን እና ኑክሌር)
ሕዳር 10 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለምን ጂኦፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምህዳር የሚመሩት ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ያላቸው ብቃት... read more
ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነዋል
ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት... read more
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ያለማንም የውጭ ገንዘብ ድጋፍ እና ብድር በኢትዮጵያዉያን የተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ታላቁ የአኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ በማህበረሰቡ ተሳትፎ እንጂ የየትኛውም አለም ሀገራት ገንዘብ ያልተካተተበት መሆኑን የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ... read more
በዘንድሮ በጀት ዓመት ለማዳበሪያ ግዢ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር መመደቡን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ
አገልግሎቱ ይህን ያለው ትላንት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ ለዘንድሮ የምርት ዘመን የሚገዛው የማዳበሪያ መጠን ካለፈው ዓመት አንጻር የ4... read more
ደረጃ የወጣላቸው ምርቶች ብሔራዊ የደረጃ ምልክት መጠቀም እንዳለባቸው ተገለጸ
አስገዳጅ ደረጃ የወጣላቸው ሁሉም ምርቶች ብሔራዊ የደረጃ ምልክት መጠቀም እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ ብሩክ ሀብቴ... read more
ምላሽ ይስጡ