መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያን ጨምሮ በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋ የመጣው ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት፣ አሁን ላይ የተሻሻለ የሕክምና አገልግሎት ቢኖርም ችግሩ አሁንም እንደሚስተዋል ተገልጿል። የዘንድሮውን የዓለም የሕሙማን ደህንነት ቀን ስናከብር ሕሙማኑ ደህንነት እንዲሰማቸውና እንዲፈወሱ ከልብ መስራትን ያካትታል ያሉት የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ቴዎድሮስ አቡሌ፤ ሆስፒታሉ ባለፈው 2018 ዓ.ም ለከ640 በላይ ታካሚዎች የተኝቶ ታካሚ ሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው ዓመት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ በትኩረት ለመስራት እስከ ክልል ድረስ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን አስረድተዋል፡፡ ለ8ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም የሕሙማን ደህንነት ቀን በኢትዮጵያ በዋናነት በደም ግፊት፣ በልብ ሕመም፣ በስኳር፣ በካንሰርና በሴቶች ላይ በሚከሰቱ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ እንደሚያተኩር አክለዋል። ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያስከትሉት ጉዳት በሀገሪቱ ምርታማነት ላይ ጫና ስለሚያሳድር ሚኒስቴሩ በትኩረት እንደሚሰራበትም ተመልክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ሰበር ዜና | ሩሲያ በታሪኳ ከፍተኛ የተባለለትን የዩክሬን ድሮን ጥቃት ማክሸፏን አስታወቀች፤ በአንድ ሌሊት 323 ድሮኖች ተመትተው ወድቀዋል!
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ክፍሎች በአንድ ሌሊት ብቻ ወደ ተለያዩ የሩሲያ ግዛቶች... read more
በትግራይ ክልል አሁን ላይ የተከለከለ የአደባባይ ሰልፍ የለም ተባለ
ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመቀለ ከተማ አጠቃላይ የአደባባይ ሰልፍ እንዳይደረግ የሚል ክልከላ ወጥቷል መባሉን ተከትሎ መናኸሪያ ሬዲዮ ስለ ጉዳዩ... read more
የአሜሪካ ውሳኔና የጤናው ዘርፍ እጣፋንታ
https://youtu.be/D48fnG0q9Dg
read more
ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ በሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ
ፍርድ ቤቱ ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የ14 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል፡፡
ፖሊስ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት... read more
በክልሉ በምሽትና በርቀት ተምረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 23 ሺህ 281 ተማሪዎች ውስጥ አንድም ተማሪ የማለፊያ ውጤት አለማምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በምሽትና በርቀት በግልና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ተከታትለው... read more
ከ’ኒያ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እሌኒ ዳምጠው ጋር የተደረገ ቆይታ
https://youtu.be/mGoRJ_xcaHE
read more
የትራፊክ መጨናነቅን የሚቀርፍ የቻይና ፈጠራ
👉ተለዋዋጭ የመንገድ መስመሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የከተማ ትራፊክ መጨናነቅ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ትላልቅ ከተሞች ዋነኛ ፈተና ከሆኑት... read more
መራጮችና ዕጩዎች በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበት ሶፍትዌር ተዘጋጀ
ሰኔ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ መራጮችና ዕጩዎች ካሉበት ሆነው በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበት... read more
በበየነ መረብ የሚሰጠው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና በሙከራ ፈተና ወቅት የሶፍትዌር ችግር ማጋጠሙ ተገለጸ
👉የትምህርት ፈተናዎችና ምዘና አገልግሎት በበኩሉ በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮምፒውተር ድጋፍ ሰጪ ቡድን አቋቁሞ ችግሩን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ገልጿል::
በሞዴል ፈተና ወቅት... read more
በሆቴልና መሰል ተቋማት የባለሙያዎችን አለባበስ በተመለከተ ከ50 ሺህ እስከ 1 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ደንብ ጸደቀ
ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል ተቋማት የባለሙያዎችን አለባበስ በተመለከተ ከ50 ሺሕ እስከ... read more
ምላሽ ይስጡ