ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) የአንጋፋዋ እና ታዋቂዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ በአምቦ ከተማ በሚገኘው መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በታላቅ ክብር ተፈጽሟል። በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአምቦ ከተማ ከንቲባ፣ የሥራ ባልደረቦቿ የሆኑ በርካታ አርቲስቶች፣ ወዳጅ ዘመዶቿ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በክብር ሽኘት ተደርጎላታል። አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ በኪነ-ጥበብ ሥራዎቿና በኦሮሞ ሕዝብ ትግል ውስጥ ከዳር እስከ ዳር ግንባር ቀደም ተሳትፎ በማድረግ ዘላቂ አሻራ ያሳረፈች የሕዝብ አርቲስት ነበረች።
__
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ