ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተቋሙ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 96.5 ቢሊዮን ብር ማትረፉን የሃይሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የዘንድሮው ትርፍ ካለፉት ዓመታት አንጻር የ23 በመቶ ልዩነት እንዳለውም ተገልጿል። ተቋሙ አሁን ላይ በጥቅሉ እስከ 9,730 ሜጋ ዋት ያህል የማመንጨት አቅም እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ አጠቃላይ የተቋሙ አፈጻጸም 92 በመቶ መድረሱንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። አሁን ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል 585 ቢሊዮን ብር ሀብት እንዳለውና መንግሥት አለኝ ከሚላቸው ተቋማት ግንባር ቀደሙ እንደሆነም ተናግረዋል። በያዝነው ዓመት ያልተሳኩትን ጨምሮ አዳዲስ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በቀጣይ 2019 ዓ.ም እንደሚያከናውንም የኤሌክትሪክ ሃይሉ አስታውቋል። በዚህም 121 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ 9,770 ሜጋ ዋት ለማመንጨት መታቀዱንም ኢንጂነር አሸብር ተናግረዋል።
__ ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ