በዶክተር መዝገብ ገደፌ የተደረሰው ይህ መጽሐፍ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱን በቤልኤር አካባቢ በሚገኘው ራስ አምባ ሆቴል አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የድርጅት ባለቤቶች፣ የማህበረሰብ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም የደራሲው ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተውበታል፡፡
በመድረኩ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ፣ ፓስተር ቸርነት በላይ (ፓስተር ቸሬ)፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ አቶ በኃይሉ ገብረመድሕን እና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች በመጽሐፉ ይዘትና በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ ጥሁረት ያደረጉ ሃሳቦችን እንደሚያካፍሉ ተጠቅሷል።
በዲጂታል ዘመን የልጆች አዕምሯዊና ስነ-ልቦናዊ ዕድገት ከፍተኛ ፈተና ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ ልጆች ከሚነገራቸው ቃል ይልቅ የወላጆቻቸውንና የአካባቢያቸውን ድርጊት አርአያ የማድረግ ባህሪያቸው የጎላ በመሆኑ፣ ህፃናትን በአወንታዊ መልኩ የማነፅ ጉዳይ አጣዳፊ ማህበረሰባዊ አጀንዳ መሆን እንዳለበት ተገልጻልል።
በተለይም በዲጂታል ዘመን የቴክኖሎጂና የማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት የልጆችን የትኩረት አቅም በመበታተን፣ ከቤተሰብ ጋር ያላቸውን የቀረቤታ በመቀነስና የባህሪ መቃወዝ ችግሮችን በማብዛት ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ ፈተና ደቅኗል።
ህጻናት የሚማሩት ከሚነገራቸው የቃል መመሪያ ይልቅ ከወላጆቻቸው ድርጊትና የዕለት ተዕለት ባህሪ በሚቀስሙት አርአያነት በመሆኑ፣ የወላጆች አዎንታዊ ስነ-ምግባርና ራስን የማረም ልምድ ለትውልዱ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት፣ ለራስ መተማመን ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጻል።
በተጨማሪም “ልጅን የማሳደግ ኃላፊነት የነጠላ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው ማህበረሰብ ነው” የሚለውን እሴት በመመለስ፤ ትምህርት ቤቶች፣ የሃይማኖት ተቋማትና ሚዲያው የተቀናጀ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸው በመጽሐፉ ይዘት ተመልክቷል።
የልጆች አስተዳደግ እንደማንኛውም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖሊሲ በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ሀገራዊ መዋዕለ-ንዋይ መሆኑን በማንሳት፣ ባለድርሻ አካላት ቀጣይነት ያለው ውይይት እንዲፈጥሩበት ጥሪ ተላልፏል።
ምላሽ ይስጡ