ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የመኪና ባለቤቶች እና አሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው ጎማ ሲገዙ ወይም ሲቀይሩ በጎማው ጎን (Sidewall) ላይ የተጻፉትን ቁጥሮች እና ፊደላት ትርጉም ማወቅ ለደህንነታቸው ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። እነዚህ ምልክቶች የጎማውን መጠን፣ የመሸከም አቅም፣ የፍጥነት ወሰን እና የተመረተበትን ጊዜ የሚገልጹ መረጃዎች ናቸው።
ለአብነት ያህል P205/55R16 91V የሚለውን የጎማ ላይ ምልክት ብንመለከት የመጀመሪያው ፊደል P ጎማው ለሰው ማጓጓዣ (Passenger Vehicle) የተሰራ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን LT ከሆነ ደግሞ ለቀላል ጭነት (Light Truck) የሚያገለግል ነው።
ቀጥሎ ያለው 205 የጎማውን ጎን ለጎን ስፋት በሚሊሜትር ይገልጻል፤ ቁጥር 55 ደግሞ የጎማው ቁመት ከስፋቱ ጋር ያለውን ንፅፅር በመቶኛ ያሳያል። R የሚለው ፊደል የውስጥ ሽቦዎቹ በክብ የተቀመጡበት (Radial) መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን ቁጥር 16 ደግሞ ጎማው የሚገጠምበት ሪም መጠን በኢንች ነው።
በመቀጠል የሚመጣው ቁጥር 91 ጎማው በነጠላ የመሸከም አቅሙን የሚያሳይ ኮድ ሲሆን ይህም እስከ 615 ኪሎ ግራም መሸከም እንደሚችል ያመለክታል። ከጎኑ ያለው V ፊደል ደግሞ ጎማው በደህና ሁኔታ መጓዝ የሚችለውን ከፍተኛ የፍጥነት ወሰን የሚያሳይ ሲሆን እስከ 240 km/h የሚያስኬድ መሆኑን ያብራራል። H (210 km/h) እና T (190 km/h) ሌሎች አብዛኛውን ጊዜ የሚታዩ የፍጥነት ወሰን ምልክቶች ናቸው።
በጎማው ላይ DOT ከሚለው ጽሁፍ መጨረሻ የሚገኘው ባለ 4 ዲጂት ቁጥር የተመረተበትን ሳምንት እና ዓመት ያሳያል። ለምሳሌ 1223 የሚለው ምልክት ጎማው በ2023 በ12ኛው ሳምንት የተመረተ መሆኑን ያመለክታል። ጎማ ምንም እንኳን ጥቅም ላይ ባይውል ከ5 እስከ 6 ዓመታት በላይ ከቆየ የመለጠጥ አቅሙ ስለሚቀንስ ለአደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል ባለሙያዎች ይመክራሉ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ለፖለቲካ ፓርቲዎች የማስጠንቀቂያ እግድ መነሳቱ ለቀጣዩ ምርጫ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገለጸ
ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከጠቅላላ ጉባዔ፣ ከኦዲትና በሴት አባላት ቁጥር አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር... read more
ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታደርገው ጥረት ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ስርዓት መገንባት እንዳለባት ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታደርገው ጥረት ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ስርዓት መገንባት እንደሚገባ ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት በንግድና... read more
ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በቅርቡ በቤርሙዳ ቲያትር ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ
ኅዳር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከተመሰረተ 88 ዓመታትን ያስቆጠረው ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በ2015 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ የዕድሳት መርሃ... read more
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የአይን ጤና ጉባኤ የላቀ ሽልማት ተበረከተላት፤ የ2 ሚሊዮን ዶላር አዲስ እቅድም ይፋ አደረገች
ጥቅምት 24 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) አንቲጓዋ እና ባርቡዳ ሴንት ጆንስ ከተማ በተካሄደው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የአይን ጤና ጉባኤ ላይ የተሳተፈችው... read more
በካይሮ በቴሌኮም ሕንፃ የእሳት አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 26 መቁሰላቸው ተሰማ
ሐምሌ 1 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ማዕከላዊ ክፍል በሚገኝ አንድ የቴሌኮም ኢጅፕት ሕንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት... read more
በፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ1ሺህ 5መቶ በላይ የእግር መዞር እክል የገጠማቸዉ ህፃናት መገኘታቸው ተገለፀ
የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከዚህ ቀደም ባልተደረገባቸው 10 ክልሎች የተካሄደ ሲሆን ከተቀመጠው እቅድ በላይ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት መከተባቸውን የኢትዮጵያ... read more
በኢትዮጵያ 90 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ በማገዶ፣ ኩበትና ከሰል ምግቡን ያዘጋጃል
ሰኔ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 90 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ማገዶ፣ ኩበት እና ከሰልን በመጠቀም የዕለት ምግቡን እንደሚያዘጋጅ የውሃና ኢነርጂ... read more
በኢትዮጵያ በኩላሊት በሽታ ላይ በቂ ጥናት እየተደረገ እንደማይገኝ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ተናገረ
ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) እንደ ሀገር በገዳይነቱ እየታወቀ የመጣው የኩላሊት በሽታ ትኩረት ተሰጥቶት በቂ ጥናት እየተደረገበት አለመሆኑን የኩላሊት... read more
ፓርቲው ከተሰረዘ በኋላ የሚያደረጋቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ኢ-ህገ መንግስታዊ እንደሚሆን ተገለጸ
አንድ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅናውን ካጣ በኋላ የሚያደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴ ኢ-ህገ መንግስታዊ ይሆናል ሲሉ የህግና የፌዴራሊዚም ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
ምክር ቤቱ የውሃ አካል ዳርቻ አወሳሰን፣ ልማት እና እንክብካቤ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የውሃ አካል ዳርቻ አወሳሰን፣ ልማት እና እንክብካቤ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ደምጽ አጽድቋል፡፡
የውሃ፣... read more
ምላሽ ይስጡ