ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በክፍልዎ ግድግዳ ላይ ግዙፍ ሸረሪት ተንጠልጥሎ ሲያዩ የመጀመሪያ ምላሽዎ በጫማ መምታት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ይህ ግዙፍ ሸረሪት ሳያውቁት ትልቅ ውለታ እያደረገልዎ ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።
በሳይንሳዊ ስሙ Sparassidae በሚባል የሸረሪት ቤተሰብ ውስጥ የሚመደበው እና «ሃንትስማን» (Huntsman Spider) በመባል የሚታወቀው ይህ ፍጡር፣ በተለይም በሞቃታማ ሀገራት በብዛት በየመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ይገኛል። አስፈሪ በሚመስለው ግዙፍ አካሉ እና ረጅም እግሮቹ ቢታወቅም፣ ፍጡሩ ለሰው ልጅ አደገኛ ወራሪ ሳይሆን ፈጣን እና ደፋር የነፍሳት አዳኝ ነው።
ድር በማሰራት ሰለባቸውን ከሚጠብቁ ሌሎች ሸረሪቶች በተለየ መልኩ፣ የሃንትስማን ሸረሪቶች በምሽት በግድግዳዎች፣ በኮርኒሶች እና በጨለማ ማዕዘናት ላይ በመዘዋወር ጎጂ ነፍሳትን ያድናሉ። ከፍተኛ የዕይታ አቅማቸውን፣ ፍጥነታቸውን እና ቅጽበታዊ ጥቃታቸውን በመጠቀም በቤት ውስጥ የሚገኙ እንደ በረሮ፣ ትንኝ፣ ዝንብ፣ ክሪኬት እና ትናንሽ የቤት እንስሳትን (እንደ ቲክቲክ ያሉ) ከመስመጣቸው በፊት አድነው ይመገባሉ።
ይህ ሸረሪት መርዝ ቢኖረውም፣ መርዙ የሚያገለግለው የሚይዛቸውን ነፍሳት ለማደናዘዝ ብቻ በመሆኑ በሰው ልጅ ላይ የጎላ የጤና እክል አያደርስም። በተጨማሪም አደጋ ሲጋረጥበት ከማጥቃት ይልቅ የመሸሽ ባህሪ ስላለው የሰው ልጅን የመንከስ አጋጣሚው በጣም አነስተኛ ነው ተብሏል።
ወደ ቤትዎ የሚገባውም ቤትዎ ለነዚህ ሸረሪቶች የሚያስፈልጋቸውን መጠለያ፣ ሙቀት እና ያልተቋረጠ የነፍሳት ምግብ ስለሚያቀርብላቸው ነው። በቤትዎ ውስጥ በረሮዎች ወይም ሌሎች ነፍሳት ካሉ፣ እርስዎ ከማየትዎ በፊት ሸረሪቱ ቀድሞ አግኝቷቸዋል ማለት ነው።
ስለሆነም እነዚህን ሸረሪቶች ማጥፋት ተገቢ አይደለም የተባለ ሲሆን፤ ምክንያቱም ያለ ምንም ኬሚካል የቤት ውስጥ ተባዮችን የሚቀንሱ ጠቃሚ አዳኞች ናቸው። በማይፈልጉበት ቦታ ላይ ካገኟቸው በመምታት ከመግደል ይልቅ፣ በቆርቆሮ ወይም በወረቀት በጥንቃቄ በመያዝ ወደ ውጭ አውጥቶ መልቀቁ ተመራጭ ነው ተብሏል።
ቀጣይ ጊዜ በግድግዳዎ ላይ ግዙፍ ሸረሪት ሲያዩ እርስዎን ፍለጋ ሳይሆን ከካቢኔዎ ጀርባ የተደበቀውን በረሮ ለማደን እንደሆነ ያስታውሱ። አንዳንዴ አስፈሪ የሚመስለው የቤት ውስጥ እንግዳ፣ በስራው ላይ በጣም ትጉህ ዘበኛ ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
🔰ከጨለማ የተገኘ ብርሃን
👉የኳንተም ፊዚክስ አስገራሚ ግኝት
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሳይንስ ሊቃውንት ሙሉ በሙሉ ከሚመስል ጨለማ ውስጥ ብርሃን እንዴት እንደሚመጣ ማስመሰል... read more
የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭት ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ሊስፋፋ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭትን ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ለማስፋፋት ዝግጅት... read more
የኮርፖሬት ቦንድን ወደ ገበያ ለማስገባት እየተሰራ ነው ተባለ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ከመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ በተጨማሪ የኮርፖሬት ቦንድ ሽያጭ ገበያን ወደ... read more
በግማሽ ዓመቱ 74 አመራርና ባለሙያዎች በጥፋት መቀጣታቸው ተገለጸ
ጥር 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት 74 አመራርና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች... read more
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እየተከተለው ያለው ጠበቅ ያለ አሰራር ፓርቲዎችን ለቀጣዩ ምርጫ የሚያጠናክር ነው ተባለ፡፡
እግዱ የተጣለባቸው ፓርቲዎች ግን ውሳኔው ተገቢነት እና ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን እንደ አገር በቅርቡ ከሚጠብቋቸው ትልልቅ ብሔራዊ ጉዳዮች መካከል... read more
ለመጪው የመስቀል በዓል የትራንስፖርት እጥረት እንዳይከሰት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓሉን አስመልክቶ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ጉዞ የሚያደርጉ ተጓዦች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይገጥማቸው እየተሰራ መሆኑን... read more
አሌክሳንደር ኢሳክ ከ4 ወራት ቆይታ በኋላ ወደ ሜዳ መመለሱን ክለቡ አስታውቋል
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል በ125 ሚሊዮን ፓውንድ የእንግሊዝ የዝውውር ክብረ ወሰንን በመስበር ያስፈረመው፣ ትውልደ ኤርትራዊው ስዊድናዊ አጥቂ አሌክሳንደር... read more
በፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ1ሺህ 5መቶ በላይ የእግር መዞር እክል የገጠማቸዉ ህፃናት መገኘታቸው ተገለፀ
የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከዚህ ቀደም ባልተደረገባቸው 10 ክልሎች የተካሄደ ሲሆን ከተቀመጠው እቅድ በላይ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት መከተባቸውን የኢትዮጵያ... read more
የሴቶች ተሳትፎ ባልተረጋገጠበት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን እውን ማድረግ እንደማይቻል ተገለጸ
መጋቢት 14 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው “ጉሚ በላል” የሃሳብ መድረክ... read more
በመዲናዋ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ከ200 ማለፋቸው ተገለጸ
በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደረውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ያለበትን የኑሮ ጫና ለማቅለል በመንግስት የተቋቋሙት የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ከ200 ማለፋቸውን የአዲስ አበባ... read more
ምላሽ ይስጡ