ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በክፍልዎ ግድግዳ ላይ ግዙፍ ሸረሪት ተንጠልጥሎ ሲያዩ የመጀመሪያ ምላሽዎ በጫማ መምታት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ይህ ግዙፍ ሸረሪት ሳያውቁት ትልቅ ውለታ እያደረገልዎ ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።
በሳይንሳዊ ስሙ Sparassidae በሚባል የሸረሪት ቤተሰብ ውስጥ የሚመደበው እና «ሃንትስማን» (Huntsman Spider) በመባል የሚታወቀው ይህ ፍጡር፣ በተለይም በሞቃታማ ሀገራት በብዛት በየመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ይገኛል። አስፈሪ በሚመስለው ግዙፍ አካሉ እና ረጅም እግሮቹ ቢታወቅም፣ ፍጡሩ ለሰው ልጅ አደገኛ ወራሪ ሳይሆን ፈጣን እና ደፋር የነፍሳት አዳኝ ነው።
ድር በማሰራት ሰለባቸውን ከሚጠብቁ ሌሎች ሸረሪቶች በተለየ መልኩ፣ የሃንትስማን ሸረሪቶች በምሽት በግድግዳዎች፣ በኮርኒሶች እና በጨለማ ማዕዘናት ላይ በመዘዋወር ጎጂ ነፍሳትን ያድናሉ። ከፍተኛ የዕይታ አቅማቸውን፣ ፍጥነታቸውን እና ቅጽበታዊ ጥቃታቸውን በመጠቀም በቤት ውስጥ የሚገኙ እንደ በረሮ፣ ትንኝ፣ ዝንብ፣ ክሪኬት እና ትናንሽ የቤት እንስሳትን (እንደ ቲክቲክ ያሉ) ከመስመጣቸው በፊት አድነው ይመገባሉ።
ይህ ሸረሪት መርዝ ቢኖረውም፣ መርዙ የሚያገለግለው የሚይዛቸውን ነፍሳት ለማደናዘዝ ብቻ በመሆኑ በሰው ልጅ ላይ የጎላ የጤና እክል አያደርስም። በተጨማሪም አደጋ ሲጋረጥበት ከማጥቃት ይልቅ የመሸሽ ባህሪ ስላለው የሰው ልጅን የመንከስ አጋጣሚው በጣም አነስተኛ ነው ተብሏል።
ወደ ቤትዎ የሚገባውም ቤትዎ ለነዚህ ሸረሪቶች የሚያስፈልጋቸውን መጠለያ፣ ሙቀት እና ያልተቋረጠ የነፍሳት ምግብ ስለሚያቀርብላቸው ነው። በቤትዎ ውስጥ በረሮዎች ወይም ሌሎች ነፍሳት ካሉ፣ እርስዎ ከማየትዎ በፊት ሸረሪቱ ቀድሞ አግኝቷቸዋል ማለት ነው።
ስለሆነም እነዚህን ሸረሪቶች ማጥፋት ተገቢ አይደለም የተባለ ሲሆን፤ ምክንያቱም ያለ ምንም ኬሚካል የቤት ውስጥ ተባዮችን የሚቀንሱ ጠቃሚ አዳኞች ናቸው። በማይፈልጉበት ቦታ ላይ ካገኟቸው በመምታት ከመግደል ይልቅ፣ በቆርቆሮ ወይም በወረቀት በጥንቃቄ በመያዝ ወደ ውጭ አውጥቶ መልቀቁ ተመራጭ ነው ተብሏል።
ቀጣይ ጊዜ በግድግዳዎ ላይ ግዙፍ ሸረሪት ሲያዩ እርስዎን ፍለጋ ሳይሆን ከካቢኔዎ ጀርባ የተደበቀውን በረሮ ለማደን እንደሆነ ያስታውሱ። አንዳንዴ አስፈሪ የሚመስለው የቤት ውስጥ እንግዳ፣ በስራው ላይ በጣም ትጉህ ዘበኛ ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በጦርነት አውድ አዲስ ታሪክ የጻፈው አስገራሚው የሚሳኤል ጥበብ፦ የሩሲያን የራዳር መከላከያ ሰብሮ የሚገባው የዩክሬኑ “ዳርት” (DART)
ሰኔ 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በወታደራዊ ሳይንስና በኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ የዓለምን ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ የሳበ አንድ አዲስ ወታደራዊ የቴክኖሎጂ... read more
በትግራይ ከሚካሄደዉ የምክክር ሂደት በፊት ልዩ ዉይይት ከወጣቶች ጋር እንደሚኖር ተጠቆመ
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ሂደት ከመጀመሩ አስቀድሞ ከክልሉ ወጣቶች ጋር ልዩ የውይይት... read more
የአፍጋኒስታን የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር ከ1,100 አለፈ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለሥልጣናት እንደገለጹት፣ በአፍጋኒስታን ከፓኪስታን ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ እሑድ ምሽት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች... read more
በክልሉ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ሂደት እንዳይካሄድ ለማደናቀፍ የሚሰሩ አካላት እኩይ ተግባራቸውን ቢቀጥሉም፤ ህዝቡ ጦርነትን እምቢ እንዲልና ከሰላም ፈላጊው ጎን እንዲቆም ጥሪ ቀረበ
ሐምሌ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ሐገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የሚካሄደውን የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ሂደት እንዳያከናውን እንቅፋት ለመሆን የሚሰሩ... read more
ኢትዮ ቴሌኮም የቀጣይ ሦስት ዓመታት አዲስ ስትራቴጂውን ይፋ አደረገ
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቀጣይ አድማስ (Next Horizon) በሚል ሃሳብ የሦስት ዓመታት ስትራቴጂ እቅዱን ተቋሙ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
ይህ... read more
በኢትዮጵያ በቅርቡ በተደረገ ጥናት 37 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተገለጸ
ሰኔ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በቅርቡ በተደረገ ጥናት እስካሁን ካለው የህዝብ ቁጥር የዜሮ አምፖል ተጠቃሚዎችን ጨምሮ 63 በመቶ የሚሆነው... read more
በማይናማር ታግተው የነበሩ 246 ዜጎችን በቀጣይ ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በማይናማር ታግተው የነበሩ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል... read more
በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የፌደራል አጀንዳ መረጣና ምክክር ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የፌደራል አጀንዳ መረጣና ምክክር ሊጀምር መሆኑን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
የ5ሜጋ ባይት ሃርድ ድራይቭ በ1956 በአይቢኤም ሲጓጓዝ የሚያሳየው ምስል ቅርምትን ፈጥሯል
ሐምሌ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዛሬ በኪሳችን ከምንይዛቸው ጥቃቅን የኮምፒዩተር ማከማቻ መሳሪያዎች ጋር ሲነጻጸር፣ ከ60 ዓመታት በፊት የነበረው ቴክኖሎጂ ምን... read more
የሰላም ካውንስሉ የክልሉን ቀውስ ለመፍታት የሄደበት ርቀት አመርቂ አለመሆኑ ተገለጸ
Conflict Management and African Politics በሚለው መጽሃፉ ላይ ቴረንስ ላዮንስ ሲጠቅስ ፡ የአመለካከት ልዩነት፣ መቃረን፣ አለመግባባት ወይም መረጋጋትና አንድነትን የሚያጠፋና ያጠፋ እንደሆነ... read more
ምላሽ ይስጡ