ነሐሴ 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በተካሄደ ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ የተመቱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ባስከተሉት ተደጋጋሚ የነዳጅ መፍሰስ ምክንያት፣ የኢራን የባህር ዳርቻዎች በተለይም በቀሽም (Qeshm) እና ላራክ (Larak) ደሴቶች አካባቢ በወፍራም የነዳጅ እና ታር (tar) ቆሻሻ መሸፈናቸው ተገለጸ።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የባህር ዳርቻዎቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ጥቁርነት መቀየራቸውንና የነዳጅ ቆሻሻው የባህር ውኃውን መሸፈኑን ያሳያሉ። ይህ የአካባቢ ጥበቃ ውድመት የጀመረው ከየካቲት 2026 ጀምሮ በቀጣናው በተቀሰቀሰው ግጭትና በንግድ መርከቦች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል።
ይህ የነዳጅ ብክለት ጥበቃ የሚደረግለት የሀራ ማንግሩቭ (Hara mangrove) ደን የመጨረሻ ክፍሎች የደረሰ ሲሆን፣ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ የውኃ ጥልቀት ማነስና አነስተኛ የውኃ እንቅስቃሴ አደጋውን አባብሶታል። ሁኔታው በኮራል ሪፎች፣ በባህር ህይወታውያን እና በአካባቢው አሳ አጥማጆች መኖሪያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
የኢራን አስቸኳይ ጊዜ ባለስልጣናት የብከላውን ስፋት አረጋግጠው የፅዳት ስራዎችን ያዘዙ ቢሆንም፣ አደጋው ከአንድ ነጠላ ክስተት ይልቅ ለወራት ከቀጠለው ወታደራዊ ግጭት የተከማቸ እንደሆነ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ከኦማን ዳርቻ አቅራቢያ ከሩሲያ የነዳጅ ጫኝ መርከብ የወጣ ሌላ የነዳጅ ብክለት የተስተዋለ ሲሆን፣ ይህም ክስተት ግጭቱ ካበቃ በኋላም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የአካባቢ ውድመት እንደሚያስከትል ስጋት ፈጥሯል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ተቅማጥና ትውከት በሽታ
በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን አራት ወረዳዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ተከሰተ
🔰በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ የዘጠኝ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 136... read more
ከሶቭየት ህብረት ዘመን የመጣው የሩሲያው ግዙፍ የሬዲዮ ቴሌስኮፕ
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በሩሲያ ምድር ውስጥ ጥልቀት ባለው ስፍራ የሚገኘው ግዙፉ ካሊያዚን አርቲ-64 (Kalyazin RT-64) የተባለ የሬዲዮ ቴሌስኮፕ፣... read more
የቱሪዝም ሚኒስቴር ለ38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በሚደረገው ቅድመ ዝግጅት በ15 ሆቴሎች የድንገተኛ ፍተሻ ማድረጉ ተገለጸ
ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የቱሪዝም... read more
የዓለም አእምሮ ጤና ቀን እየተከበረ ይገኛል
መስከረም 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለም አእምሮ ጤና ቀን በየዓመቱ መስከረም 30 በዓለም አቀፍ ደረጃ "በድንገተኛ አደጋዎችና ሰብአዊ ቀውስ ወቅት የአእምሮ... read more
በኢኳዶር ማቻላ እስር ቤት በተቀሰቀሰ ግርግር 31 ሰዎች ሞቱ
ህዳር 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢኳዶር ማቻላ ከተማ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ በተፈጠረው ግርግርና ግጭት ምክንያት 31 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ።... read more
ኢሚግሬሽን ውስጥ የሚታየው ብልሹ አሰራርና መፍትሄው
https://youtu.be/df_HeM5X-Ws
read more
የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ልዩ ትኩረት መሰጠቱን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም. የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን... read more
ከገንዘብ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ
እ.ኤ.አ ሜይ 25/2025 ሪፖርተር ጋዜጣ “እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር መድረሱ ተነገረ" በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር... read more
የማይክል ጃክሰን የኮንሰርት ካልሲ በ$9,000 ተሸጠ
ነሐሴ 07 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የፖፕ ንጉስ በመባል የሚታወቀው የሟቹ ታዋቂ አርቲስት ማይክል ጃክሰን በ1997ቱ የሂስትሪ ወርልድ ቱር (HIStory... read more
የቻይና አዲስ የስለላ ቴክኖሎጂ እስከ 1.6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ክፍት መጽሐፍትን ማንበብ እንደሚችል ተነገረ
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና እስከ 1.6 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ የሚገኙ ክፍት መጽሐፍትን ማንበብ የሚችል አዲስ የስለላ ቴክኖሎጂ... read more
ምላሽ ይስጡ