ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፉት ሶስት ሳምንታት ሰፍኖ የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ፣ አሜሪካ በኢራን ደቡባዊ እና ምስራቃዊ ግዛቶች ላይ በሰነዘረችው አዲስ የአየር ድብደባ ምክንያት ቀጠናው ዳግም ወደ ከባድ ውጥረት ውስጥ ገብቷል። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) የአሜሪካ የባህር ኃይል አምስተኛ ፍሊት ዋና መነሻ በሆነችው ባህሬን የሚገኙ የነዳጅ ማከማቻዎችን፣ በኩዌት የሚገኘውን የፓትሪዮት የአየር መከላከያ ስርዓት እና በኳታር የሚገኝ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ሳተላይት መገናኛ ጣቢያን በድሮንና በሚሳኤል መምታቱን በይፋ አስታውቋል።
ይህ የኢራን ድንገተኛ የአጸፋ እርምጃ የተቀሰቀሰው አሜሪካ በኢራን የባህር ጠረፍ እና በምስራቅ ግዛቶች በሚገኙ ስትራቴጂካዊ ይዞታዎች ላይ ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ከፍተኛ የአየር ድብደባ መፈጸሟን ተከትሎ ነው። በአሜሪካ ድብደባ ምክንያት በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ ተደርሶ የነበረው ደካማ የተኩስ አቁም ስምምነት ሙሉ በሙሉ የፈረሰ ሲሆን፣ ዋሽንግተን ለጥቃቱ መነሻ ያደረገችው ኢራን በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ስምምነቱን ጥሳለች የሚል ክስ ነው።
በአሁኑ ሰዓት በኩዌት፣ ባህሬን እና ኳታር የሚገኙ የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ዘዴዎች ጥቃቱን ለማክሸፍ በከፍተኛ ሁኔታ ስራ ላይ መዋላቸው የተሰማ ሲሆን፣ ሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ እርምጃዎቻቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማስጠንቀቃቸው ቀውሱ ወደ መላው መካከለኛው ምስራቅ ሊስፋፋ እንደሚችል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ሲፈን ሀሰን በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረገው የሲድኒ ማራቶን የማሸነፍ ቅድሚያ ግምቱን አገኘች
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን በመጪው መስከረም ወር ላይ በሀገረ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ላይ በሚከናወነው... read more
ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መደገፍ የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ‘’ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለው’’ በሚል ሃሳብ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያና በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የተሰበሰበ ገቢ... read more
በጎረቤት ሀገራት ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ስደተኞች በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ተገለጸ
ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ለበርካታ ዓመታት የሚሰጡት የአጭር ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታና የሕይወት አድን... read more
በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉ ሴናተር በ11 ዓመት እስራት መቀጣታቸው ተነገረ
ጥር 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉ የቀድሞው የኒው ጀርዚ ሴናተር ቦብ... read more
ኢንዶኔዥያ ውስጥ የሌዎቶቢ እሳተ ገሞራ ፈነዳ
👉እሳተ ገሞራው ሲፈነዳ 6.8 ማይል ከፍታ ያለው አመድ ደመና መትፋቱ ተዘግቧል፡፡
ኢንዶኔዥያ ውስጥ የሚገኘው ሌዎቶቢ እሳተ ገሞራ (Lewotobi volcano) ትናንት በመፍንዳቱ፣... read more
ተጠባቂዎቹ ፍልሚያዎች በቀጣይ ወር ይከናወናሉ
የድብልድ ማርሻል አርት ክህሎት ያላቸው ተፋላሚዎች በየክብደት እርከናቸው ተከፋፍለው የሚያከናውኑት የፍልሚያ አለም በተለምዶ Professional fighters league ወይም PFl የፍልሚያ ጨዋታዎች... read more
“ሰማያዊው ሰው”፦ በደቂቃዎች ውስጥ ሆስፒታሉን ያተራመሰው አስደንጋጭ ክስተት
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በእንግሊዝ ደርቢሻየር የሚኖረው የ42 ዓመቱ ቶሚ ሊንች (Tommy Lynch) አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ መላ... read more
የባህሬን ወደብ፤የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ
የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል ንብረት የሆኑ ሁሉም የፊት መስመር መርከቦች ከባህሬን ቁልፍ ወደብ መውጣታቸውን የሳተላይት ምስሎች ማሳየታቸውን ኒውስዊክ ዘግቧል። ይህ... read more
ያለ ረዳት በሚሰሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም አሁንም ክፍተቱ እንዳለ ነው ተባለ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ "ሚኒባስ" ታክሲዎች ያለ ረዳት መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እና ተሳፋሪን... read more
በሳውላ ከተማ የ8ኛ ክፍል ፈተና ለተማሪ ሊፈተን የገባ መምህር እና ተማሪው በቁጥጥር ስር ዋሉ
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሳውላ ከተማ ኩስቲ ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ፈተና ለተማሪ ሊፈተን ከተማሪ ጋር ተመሳስሎ... read more
ምላሽ ይስጡ