ሰኔ 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የኤድዋርድስ የአየር ኃይል እዝ ውስጥ እጅግ አስከፊ የአየር አደጋ ተከስቷል። የአሜሪካ አየር ኃይል ኩራት እና ስትራቴጂካዊው ግዙፉ የቢ-52 (B-52 Stratofortress) ቦምብ ጣይ አውሮፕላን የሙከራ በረራ እያደረገ ባለበት ወቅት በድንገት ተከስክሶ የሰምንት ሰዎች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አልፏል። ወታደራዊ ባለስልጣናት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ስምንት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን በይፋ አረጋግጠዋል።
አደጋው የደረሰው ሰኞ ጠዋት በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ሲሆን፣ ቦታው ከሎስ አንጀለስ በስተሰሜን በሚገኘው ታዋቂው የኤድዋርድስ አየር ኃይል ማረፊያ ማኮብኮቢያ አቅራቢያ ነው። በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩትና ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች ድብልቅ የሆኑ የወታደራዊ አባላት፣ የኮንትራት ሰራተኞች እና የቦይንግ ኩባንያ ባለሙያዎች እንደነበሩ ተገልጿል።
አውሮፕላኑ አዲስ የተገጠመለትን የራዳር ማዘመኛ ሲስተም ለመፈተሽ መደበኛ የሙከራ በረራ እያደረገ የነበረ ሲሆን፣ ልክ እንደተነሳ ወዲያውኑ ተከስክሶ በእሳት ተውጧል። ከአደጋው የተረፈ ምንም ነገር እንደሌለና ከአካባቢው እጅግ ግዙፍ ጥቁር ጭስ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንደነበር የአየር ላይ ምስሎች አሳይተዋል።
የኤድዋርድስ አየር ኃይል እዝ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጄምስ ሄይስ በሰጡት መግለጫ አደጋው ማንም ሊተርፍበት የማይችል አይነት እጅግ አሰቃቂ እንደነበር ገልጸው፣ ስምንት ታላላቅ አሜሪካውያንን በማጣታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው ሃሳባቸውና ጸሎታቸው ከሟች ቤተሰቦች ጋር መሆኑን አስታውቀዋል።
የአቪዬሽን ደህንነት ባለሙያዎች አውሮፕላኑ እንደተነሳ ወዲያውኑ መከስከሱ የቁጥጥር ስርአት ብልሽት ሊሆን እንደሚችል ቢገምቱም፣ የአሜሪካ አየር ኃይል ለአደጋው መንስኤ የሚሆን እስካሁን ያገኘው ፍንጭ እንደሌለና ጥልቅ ምርመራ ለማድረግ እስከ ስድስት ወር ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቋል።
ቦይንግ ቢ-52 ከ1950ዎቹ ጀምሮ በአሜሪካ የጦር ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ ያለ፣ ሁለቱንም የተለመዱና የኑክሌር መሣሪያዎችን መሸከም የሚችል ግዙፍና ረጅም ርቀት ተጓዥ ስትራቴጂካዊ የጦር አውሮፕላን ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር በማሻገር ተሰማርቶ የተገኘ ግለሰብ በ15 ዓመት ፅኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር ተቀጣ
በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ 4 ሰዎችን በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ ከሀገር ለማስወጣት ሲንቀሳቀስ የተገኘ ግለሰብ... read more
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለመጀመሪያ ጊዜ 39.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተቋሙ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 96.5 ቢሊዮን ብር ማትረፉን የሃይሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ... read more
በከተማ ለስላሳ ነፋስ 10 ኪሎዋት ኃይል የሚያመነጨው የፈረንሳይ ‘የነፋስ ዛፍ’
ጥቅምት 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፈረንሳይ በከተማ አካባቢ ለስላሳ ነፋስን ወደ ንፁህ ኃይል በመለወጥ ረገድ አዲስ ምዕራፍ የከፈተችውን ፈጠራ ይፋ አደረገች።
የነፋስ... read more
ፓርቲዎች በሚፈለገው ልክ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረግን አይደለም ሲሉ ገለጹ
ሚያዚያ 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምርጫ ቅስቀሳ በይፋ የጀመሩት "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" እና "ሠላም ለኢትዮጵያ ጥምረት" በተለያዩ ምክንያቶች በሚፈለገው ልክ... read more
ወላጆች በትምህርት ቤቶች አካባቢ ተሽርካሪ ባለመቆም የትራፊክ ፍሰቱ ላይ ጫና እንዳይፈጠር ትብብር እንዲያደርጉ ተጠየቀ
መስከረም 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ማንኛውንም ተሸከርካሪ ባለማቆም ወላጆች ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ትራፊክ... read more
አውሮፖ ህብረት ለኢትዮጵያ 240 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ
የአውሮፖ ህብረት በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህንና የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂነት ለማጎልበት 240 ሚሊዮን ዩሮ (32 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር) ድጋፍ አድርጓል።
የገንዘብ ሚኒስትር... read more
በሀገር ውስጥ ታክሞ መዳን ለምን አስቸጋሪ ሆነ?
👉
https://youtu.be/67lTpwIJ3X0
read more
የኢትዮ-ሶማሊያ የሁለትዮሽ ስምምነት ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ መልኩ በጥንቃቄ የተሞላ ሊሆን እንደሚገባው ተገለጸ
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አደራዳሪነት ያደረጉት ስምምነት አፈፃፀሙ ውጤታማ እንዲሆን በጥንቃቄ መያዝ እና መመራት እንዳለበት... read more
ኢትዮጵያን ወደ AUSSOM ለመመለስ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው ተባለ
ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያና ሶማሊያ አልሻባብን በጋራ ለመዋጋት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ኢትዮጵያና ሶማሊያ ባለፉት ጥቂት... read more
በበቆጂ አቅራቢያ በሚገኘው የጋለማ ደን የተነሳዉን እሳት ለማጥፋት መሳሪያ ቢጠየቅም ማግኘት አልተቻለም ተባለ
ለአንድ ሳምንት ያህል በአርሲ የሚገኘው የጋለማ ደን በእሳት ውስጥ እንደሚገኝ ያስታወቀው የአርሲ ተራራሮች ብሄራዊ ፓርክ ነው፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የፓርኩ ሃላፊ... read more
ምላሽ ይስጡ